Sifra Daqaarak xiinissoh kutbeh buxa ጭፍራ ወረዳ መስተዳድር ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Afar
  • Sifra Daqaarak xiinissoh kutbeh buxa ጭፍራ ወረዳ መስተዳድር ጽ/ቤት

Sifra Daqaarak xiinissoh kutbeh buxa ጭፍራ ወረዳ መስተዳድር ጽ/ቤት Local service

08/08/2025
23/07/2025
የአፋር ክልል የ2018 በጀት 18 ነጥብ 715 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር ክልል የ2018 በጀት 18 ነጥብ 715 ቢሊየን ብር በላይ ሆ...
23/07/2025

የአፋር ክልል የ2018 በጀት 18 ነጥብ 715 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር ክልል የ2018 በጀት 18 ነጥብ 715 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ ጸድቋል ፡፡

የአፋር ክልል ም/ቤት እያካሄደ በሚገኘው 6ኛ ዙር 4ኛ የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባዔ የክልሉን የ2018 በጀት 18 ነጥብ 715 ቢሊየን ብር አድርጎ አጽድቋል፡፡

Rakaakyak 2018 Liggidih Mizaaniyyat 18, Biliyoon 715 Miliyoon Abak Faaticisen.

Samara,Diteli-Alsak 16,2017,(AFMMA)

Qafar Rakaakyak 2018 Liggidih Mizaaniyyat 18, Biliyoon 715 Miliyoon 776 Boolih Alfi kah Yakkennah Mala Buxal Xayyoosak Inki Xongolol Faaticisen.

Tama Mizaaniyyat Rakaakayak Maaliyyah Biirok Naharsi Saqal Gifta Acmad Macammad Boddaaya Mala Buxal Xayyoose .

09/04/2025
09/04/2025

አዲስ የሽግግር ባህል

ዛሬ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲያዊ ጉዞዋ ሌላ ጉልህ ምዕራፍ ላይ ደርሳለች። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የስልጣን ሽግግሩን እና የስልጣን ርክክብን በይፋ እና በሰላማዊ መንገድ ለማስኬድ በሚገባ የተዋቀረ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ተከናውኗል:: ባለፋት ሁለት አመታት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የመሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አዲስ ለተሰየሙት ጀነራል ታደሰ ወረደ ስልጣናቸውን አስረክበዋል።

ይህ የአመራር ለውጥ ብቻ ሳይሆን በተቋማዊ ታማኝነት፣ በመከባበር እና በአገራዊ አንድነት ላይ የተመሰረተ አዲስ የፖለቲካ ባህል ማደጉን ያሳያል።

የብልፅግና ፓርቲ ይህንን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ህዝባችን ቁርጠኛ የሆነበት የዴሞክራሲያዊ እሴት ማሳያ አድርጎ ነው የሚመለከተው። ይህ ክስተት የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እና የህዝቦቿ ፖለቲካዊ ብስለቶች ማሳያ ነው።

አጋጣሚው መንግስት ዴሞክራሲን በማጠናከር፣ ሁሉን አቀፍነትን እና መልካም አስተዳደርን በማጎልበት ያለውን ተግባራዊ ተሞክሮ ያስረዳል።

የዚህ ስኬት አስኳል በትግራይ ክልል የነበረውን ህይወት ገባሪ ግጭት ያስቆመው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ነው። ስምምነቱ ግጭቶችን ከማስቆም ባለፈ በውይይት፣ በህገ መንግስታዊ ስርዓት እና በብሄራዊ መግባባት ላይ ለተገነባው የወደፊት ጉዞ መሰረት ጥሏል። የብልፅግና ፓርቲ ይህን ሂደት ለማስቀጠል ሰላም የየትኛውም የዘላቂ ዴሞክራሲ መሰረት መሆኑን በማጠናከር ወሳኝ ሚና ተጫውቷል።

ከፕሪቶሪያ መንፈስ ጋር በመጣመር በትግራይ ዘላቂ ሰላምና ልማት ግንባታ ላይ ተጨባጭ እርምጃዎች ተወስደዋል። መንግስት የሰላም ስምምነቱ በተሟላ መልኩ እንዲተገበር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ በመቀጠል መሰረታዊ አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት መመለስ፣ ደህንነትን ማረጋገጥ እና ፍትህና ተጠያቂነትን ማስፈን ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

በተጨማሪም የፌደራል መንግስት ለትግራይ ክልል መልሶ ማቋቋምና ለህዝቦቿ ልማት ያለውን ጠንካራ ቁርጠኝነት አረጋግጧል። ይህም መሠረተ ልማትን መልሶ መገንባት፣ የክልሉን ኢኮኖሚ ማነቃቃት፣ ሰብዓዊ አቅርቦትን ማረጋገጥ እና በጤና፣ በትምህርት እና በወጣቶች ማብቃት ላይ ኢንቨስት ማድረግን ይጨምራል።

የፌደራል መንግስት ከክልል ባለስልጣናት፣ ከአለም አቀፍ አጋሮች እና ከአካባቢው ማህበረሰቦች ጋር በቅርበት በመስራት ይህ ማገገም ሁሉን አቀፍ፣ ግልፅ እና ቀጣይነት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ እየሰራ ነው።

ዛሬ የተካሄደው ሰላማዊ የስልጣን ርክክብ የአዲስ የፖለቲካ ባህል ነጸብራቅ ነው። የወደፊቷ ኢትዮጵያ የተቋማት እንጂ የግለሰቦች እንዳልሆነች እና የፖለቲካ አመራር የአገልጋይነት እንጂ የመብት ጥያቄ እንዳልሆነ ግልጽ መልእክት ያስተላልፋል።

በብዙ ጥረት የተገኘውን ሰላም ለማስጠበቅ፣ ዴሞክራሲያችንን ለማሳደግ እና የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያን አዲስ የእድገት ምዕራፍ ተካፋይ እንዲሆን በጋራ መስራት ይጠበቃል።

05/04/2025

Address

Afar
Afar
1234

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sifra Daqaarak xiinissoh kutbeh buxa ጭፍራ ወረዳ መስተዳድር ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Sifra Daqaarak xiinissoh kutbeh buxa ጭፍራ ወረዳ መስተዳድር ጽ/ቤት:

Share