ብልፅግና ወጣቶች ክንፍ - አዲስ አበባ ቅርንጫፍ

  • Home
  • Ethiopia
  • Adis
  • ብልፅግና ወጣቶች ክንፍ - አዲስ አበባ ቅርንጫፍ

ብልፅግና ወጣቶች ክንፍ - አዲስ አበባ ቅርንጫፍ Creating democrat, vibrant and front line youth that has accepted and ready to implement programs and objectives of prosperity party

ወጣቶች እየመረጡ ነው፡፡ በድምፃቸው ብሩህ ነገአቸውን እያፀኑ ነው!
01/06/2026

ወጣቶች እየመረጡ ነው፡፡ በድምፃቸው ብሩህ ነገአቸውን እያፀኑ ነው!

ዛሬ ማልዳችሁ ወደ መስቀል አደባባይ የተመማችሁ የከተማችን ነዋሪዎች፣ ይህ ብልጽግናን ከመደገፍ ያለፈ ዴሞክራሲያዊ ሥርአትን የማፅናት የጀግንነት አውድ ነው። “በምርጫ ብቻ!” የሚለውን ታላቅ ...
26/05/2026

ዛሬ ማልዳችሁ ወደ መስቀል አደባባይ የተመማችሁ የከተማችን ነዋሪዎች፣ ይህ ብልጽግናን ከመደገፍ ያለፈ ዴሞክራሲያዊ ሥርአትን የማፅናት የጀግንነት አውድ ነው።
“በምርጫ ብቻ!” የሚለውን ታላቅ መልዕክት ለዓለም አስተላልፋችኋል፤ የሁል ጊዜ የአብሮነታችሁ መልዕክት ሀገር ማፅናት ነው፤ እናመስግናለን፤ ፅኑ ህዝቦች !!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ክብርት ከንቲባ አደነች አቤቤ

Har'a ganamaan gara Addabaabaayii Masqala kan yaatan jiraattonni magaalaa keenyaa, kuni badhaadhina deeggaruu irra dabree gootummaa sirna dimookiraasii cimsuuti.
Ergaa guddaa "Filannoo Qofaan!" jedhu addunyaaf dabarsitanii jirtu, ergaan keessan yeroo hunda waliin biyya cimsuudha; galatoomaa; uummata jabaa!

Waaqni Itoophiyaa fi Uummata Ishee Haa Eebbisu!
kabajamtu kantibaa Adanech Abebe

.ወጣት ይምረጥ፤ ኢትዮጵያ ትጽና!ወጣትነት ነገን ዛሬ የመገንባት የማይበገር ፅናት!ብልፅግና ፓርቲ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች፣ 7ኛውን ሀገራዊና...
25/05/2026

.ወጣት ይምረጥ፤ ኢትዮጵያ ትጽና!
ወጣትነት ነገን ዛሬ የመገንባት የማይበገር ፅናት!

ብልፅግና ፓርቲ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች፣ 7ኛውን ሀገራዊና ከተማ አቀፍ ምርጫ በማስመልከት በታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ በጉብኝት የታጀበ የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሂደዋል።

ባለፉት 5 አመታት ታላላቅ ፕሮጀክቶች እና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች የከተማችንን ገፅታ በእጅጉ ቀይረዋል።

ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!
ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌተ_ሀገር!


#ምርጫ2018


"ወጣት ይምረጥ ኢትዮጵያ ትፅና!"በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ክፍለ ከተማ ወጣት ክንፍ በዛሬው ዕለት 7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫን አስመልክቶ የፓናል ውይይትና የምረጡኝ የምርጫ ቅስቀሳ መረሃ-...
25/05/2026

"ወጣት ይምረጥ ኢትዮጵያ ትፅና!"

በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ክፍለ ከተማ ወጣት ክንፍ በዛሬው ዕለት 7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫን አስመልክቶ የፓናል ውይይትና የምረጡኝ የምርጫ ቅስቀሳ መረሃ-ግብር በደማቅ ሁኔታ አካሄዷል።

በላቀ ጥራት እና ቅልጥፍና እየተገነቡ ለህዝባችን አገልግሎት በሚሰጡ ፕሮጀክቶች ላይ የወጣቶች ሚና ጉልህ ሲሆን ተጠቃሚነታቸውም በዚያው ልክ የተረጋገጠ ነው፡፡

ሸበየህዝባችን የዘመናት ቁጭት ወደ ድል በተለወጠበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና የአዲስ አበባን ተምሳሌታዊ ጉዞ ከፍ ባደረገው የኮሪደር ልማት እንዲሁም የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች ወጣቶች በጉልበታቸው፣ በእውቀታቸው፣ በገንዘባቸው ታሪካዊ አሻራቸውን ያሳረፉባቸው ሲሆን ሰፊ የስራ ዕድል ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

ነገን ዛሬ እየገነባ፣ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ የሚገኘውን ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ!

የመደመር፣ የትብብር እና የአንድነት መገለጫ የሆነው የስንዴ ነዶ ምልክታችን ነው!

ዛሬ "ወጣት ይምረጥ ኢትዮጵያ ትጽና” በሚል መሪ ቃል  የብልጽግና አሻራ በተቀመጠበት ገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ከመላ ከተማችን ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ ...
23/05/2026

ዛሬ "ወጣት ይምረጥ ኢትዮጵያ ትጽና” በሚል መሪ ቃል የብልጽግና አሻራ በተቀመጠበት ገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ከመላ ከተማችን ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም አካሂደናል ።

ስለ ወጣቱ ተጠቃሚነት ችግርን እያወራን ሳይሆን 24/7 እየሰራን ለችግሩ ተግባራዊ ምላሽ ከሰጠንባቸው እና ተጠቃሚነቱን ካረጋገጥንባቸው ስፍራዎች አንዱ በሆነው በገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ70 ሺህ በላይ ከሆኑ የከተማችን ወጣቶች ጋር በስፓርታዊ እንቅስቃሴ የምርጫ ቅስቀሳ አድርገናል።

ባለፉት 5 ዓመታት የሰራናቸው የልማት አሻራዎች የኢትዮጵያን ብልፅግና አይቀሬነት ይመሰክራሉ። ከማንም በላይ ሀገር እየተገነባች ያለችው ለወጣቶቻችን በመሆኑ የብልፅግናዋ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ።

የከተማችን ወጣቶች የፓርቲያችንን ራዕይና የወደፊት አሻራ ሁለንተናዊ እድገት ሰንቃችሁ፥ ተስፋ ተጋርታችሁ ማልዳችሁ ከአራቱም አቅጣጫዎች በመትመም ድጋፋቸሁን ስለገለፃችሁልን በራሴ እና በፓርቲዬ ብልፅግና ስም ከልብ አመሰግናለሁ።

መንገዳችን መደመር፤ መዳረሻችን ብልፅግና ነው!

ኢትዮዽያን ወደ ተምሳሌት አገር !

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

23/05/2026
ወጣት የሀገር መከታ፣ የትውልድ ጋሻ ፣ የብልፅግና ትውልድ ነውብልፅግና ፓርቲ  በቦሌ ከተማ ወጣቶች ክንፍ 7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ አስመልክቶ  የምረጡኝ የኪነጥበብ ዜማ ምሽት በማዘጋጀ...
22/05/2026

ወጣት የሀገር መከታ፣ የትውልድ ጋሻ ፣ የብልፅግና ትውልድ ነው

ብልፅግና ፓርቲ በቦሌ ከተማ ወጣቶች ክንፍ 7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ አስመልክቶ የምረጡኝ የኪነጥበብ ዜማ ምሽት በማዘጋጀት በደማቅ ቅስቀሳ አካሄዷል።

ተምሳሌታዊወጣትለተምሳሌት ሀገር
ብልፅግናን ይምረጥ!!

ምልክታችን የስንዴ ነዶ!
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!


#ምርጫ2018

"ወጣት ይምረጥ ኢትዮጵያ ትፅና"በብልፅግና ፓርቲ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ በዛሬው ዕለት የሰባተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫን አስመልክቶ የእግር ጉዞ በማድረግ የምረጡኝ ...
21/05/2026

"ወጣት ይምረጥ ኢትዮጵያ ትፅና"

በብልፅግና ፓርቲ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ በዛሬው ዕለት የሰባተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫን አስመልክቶ የእግር ጉዞ በማድረግ የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሂዷል።

በተካሄደው የእግር ጉዞ የምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ በየደረጃው ያሉ የወጣት ክንፍ አመራሮች፣አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ለሀገር ብልፅግና ዋነኛ መሠረቶች ወጣቶች ናቸው ብሎ የሚያምን ፓርቲ በመሆኑ ባለፉት አምስት አመታት በወጣቶች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል።

በዚህም ወጣቱን ሁለንተናዊ ተሳተፊና ተጠቃሚ እንዲሆን በማስቻል በርካታ ለውጦችን ማስመዝገብ ችሏል።

የኢትዮጵያ ብልፅግና እንዲረጋገጥ ወጣቶች በቀጣዩ ምርጫ ድምፃችሁን ለብልፅግና ፓርቲ ስጡ።

#ምርጫ2018


ድምፃችን ለልማት፣ ዋስትናችን ለሰላም፦  የወጣቶች የምክክር መድረክ በአቃቂ ቃሊቲ!!በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ወጣቶችና የወጣት አደረጃጀቶች፣ 7ኛው ሀገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ ሰላማ...
21/05/2026

ድምፃችን ለልማት፣ ዋስትናችን ለሰላም፦ የወጣቶች የምክክር መድረክ በአቃቂ ቃሊቲ!!

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ወጣቶችና የወጣት አደረጃጀቶች፣ 7ኛው ሀገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ገለልተኛ፣ ሁሉን አካታችና በሕዝብ ዘንድ እምነት የሚጣልበት እንዲሆን የወጣቶች ሚና የጎላ መሆኑ በውይይቱ ላይ ተነስቷል። ወጣቶቹም የምርጫው ሂደት ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ እንዲሆን የበኩላቸውን የላቀ አስተዋፅኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

#ምርጫ2018

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር !የብልፅግና ፓርቲ በቂርቆስ  ክፍለ ከተማ ወጣት ክንፍ  የ7ኛውን አገራዊና ከተማ አቀፍ ምርጫ በማስመልከት ደማቅ  የአደባባይ የ“ምረጡኝ” ቅስቀሳ መርሃ-ግብር...
20/05/2026

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር !

የብልፅግና ፓርቲ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣት ክንፍ የ7ኛውን አገራዊና ከተማ አቀፍ ምርጫ በማስመልከት ደማቅ የአደባባይ የ“ምረጡኝ” ቅስቀሳ መርሃ-ግብር አካሂዷል።

በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩ እጩዎች፣ እንዲሁም የክፍለ ከተማዉ አመራሮች፣ የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ተሳትፈዋል።

ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!
ለሀገር ከፍታ - ብልፅግናን ይምረጡ!

#ምርጫ2018


Address

Adis

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ብልፅግና ወጣቶች ክንፍ - አዲስ አበባ ቅርንጫፍ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share