Libo Kemkem Woreda Court/ሊቦ ከምከም ወረዳ ፍርድ ቤት

Libo Kemkem Woreda Court/ሊቦ ከምከም ወረዳ ፍርድ ቤት "Our vision is excelling to become a model judiciary in Ethiopia!"
"ራዕያችን በአገር አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት የሆነ ፍርድ ቤት መገንባት ነው!

02/04/2026

ዜና ችሎተ
ከባድ ስርቆት እና መሸሸግ ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች በ3 ዓመት ከ 9 ወር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል
ከሳሸ አቃቢ ህግ
ተከሳሽ 1 ቻሌ ሞላ አሰሜ
2. ሲሳይ አለምነው እምሬ አድራሻቸዉ በለሳ ወረዳ ዋርካ ቀበሌ የሆኑት ግለሰቦች በ1996 ዓ/ም ተደንግጎ የወጣዉን የኢፌደድሪ የወንጀል ህግ ድንጋጌ አንቀፀ 32/1/ /ሀ/እና 669 /3/ /ለ/ ን በመተላለፍ ተገቢ ያልሆነ ሃብት ለማግኘት በማሰብ አንድ ካልተታዘ ግለሰብ ጋር በመሆን በቀን 18 /06 /2018 ዓ ም ከሌሊቱ 7 00 ስዓት ሲሆን በአዲስ ዘመን ከተማ ቀበሌ 03 ልዪ ቦታዉ ፍተሻ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታ የግል ተበዳይ የአቶ ጌታቸዉ በእዉቀትን የኮንቲነር ሱቅ ሰብረዉ በመግባት የተለያዪ የሱቅ እቃዎችን የወሰዱ በመሆኑ በፈፀሙት ስርቆት ወንጀል ተከሰዋል ተከሳሾችም በተባለዉ ቀንና ስዓት ድርጊቱን አልፈፀምነም ብለዉ ክደዉ ተከራክረዋል ፍ/ቤቱም አቃቢ ህግ ምስክሮችን እንዲያቀርብ ብይን ተሰጥቶ የአቃቢ ህግ ምስክሮችም እንደክሱ አስረድተዋል፡፡ ተከሳሾችም የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርቡ ቢጠየቁም ክሱን ማስተባበል አልቻሉም ፡፡ ፍርድ ቤቱም በ10 /7/2018ዓ.ም ይዞት በዋለው ችሎት ጥፋተኞችን ያርማል ያስተምራል መሰል የማሀበረሰብ ክፍሎችንም ያስጠነቅቃል በሚል በ3 ዓመት ከ 9 ወር እንዲቀጡ ፍረድ ቤቱ ወስኗል

31/03/2026

የ/ሊ/ከ/ወ/ ፍ/ቤት የዳኞች የህግ ውይይት
7ኛ ዙር
ቅድመ ሙግት (pre trial}
ቅድመ ሙግት በፍትሐብሔር ክርክር ሂደት ጭብጥ ተይዞ ማስረጃ ማሰማት ከመጀመሩ በፊት ያለውን ሂደት የያዘ ሲሆን በዋነኛነት ክስና ማስረጃ ማቅረብን፤ መጥሪያ ማድረስን፤ መልስና ማስረጃ ማቅረብን፤የቃል ክርክርንና የክስ መቃወሚያ ላይ መወሰንን ያካትታል፡፡
የመወያያ ሀሳብ አንድ፡- በፍትሐብሔር ክርክር የክስ መጣመር እና መነጠል(joinder and mis joinder}
ማለትም በአንድ ክስ ውስጥ ብዙ ከሳሾች፤ብዙ ተከሳሾች፤አንድ አይነት የክስ ምክንያቶች፤የተለያዩ የክስ ምክንያቶች እና የሶስተኛ ወገኖች በክሱ መካፈል(መጣመር)የያዘ ሲሆን አላማውም ክርክርን አጭር፤ግልጽ፤ጊዜና ወጭ ቆጣቢ በሆነ መንገድ መምራት፤ ተቃራኒ ውሳኔዎችን መከላከል፤ እና ፍትሀዊ መፍትሔ መስጠት ነው፡፡ይህም በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ /35-43 የተቀመጠ ነው፡፡በዚህም አግባብ መጣመር የሌለባቸው ተከራካሪዎች ተጣምረው ክስ ሲያቀርቡ ወይም መጣመር የሌለባቸው የክስ ምክንያቶች ተጣምረው ሲቀርቡ ልክ እንደማያስከስስ ምክንያት ወይም የስረ ነገር ስልጣን ሳይኖር እንደቀረበ ክስ መጥሪያ መላክ ሳያስፈልግ ተነጣጥለው ያቅርቡ ወይም ተነጣጥሎ ይቅረብ ተብሎ ፋይል ይዘጋል፡፡ ነገር ግን የግድ ተጣምረው መክስስ ያለባቸው ሢሆን ወይም ክሱ ተጠቃሎ መቅረብ ያለበት ሲሆን ለምሳሌ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ216 እናሌሎች ባስቀመጡት አግባባ የውርስ ወይም የባልና ሚስት ጉዳይ ሲሆን እና ከዚህ ክርክር ላይ ጣልቃ የሚገቡ ወይም በክርክሩ የሚጣመሩ ተከራካሪዎች የክሰ ምክንያታቸው የተለያየ ሆኖ አቤቱታው በአንድ ላይ ቢቀርብ አቤቱታቸሁን ነጣጥላችሁ አቅርቡ ማለት ይቻላል ወይ? ክስን ነጣጥሎ ማቅረብ ከሚያሳካው አላማ አንፃር እንዴት ይታያል? የአቤቱታው መጣመር ሆነ መነጣጠል ክርክርን ከማሳለጥ አንጻር በውጤት ደረጃ የተለየ ሊሆን ይቸላል ወይ?
የመወያያ ሀሳብ ሁለት፡-በፍትሀብሔር ክርክር የሰነድ(የጽሁፍ) ማስረጃዎች
ሙሉ ክርክሩን መስማትና ምስክሮችን መመርመር ከመጀመሩ በፊት እነዚህ ማስረጃዎች ተጠቃለው መቅረብ እና የመዝገቡ አካል መሆን አለባቸው(የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ/234)፡፡እንዲሁም ዳኛ በራሱ ተነሳሽነት ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት ከፍርድ በፊት በማንኛውም ጊዜ አንዲቀርብ ትእዛዝ ለመስጠት ይችላል(የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ/264) ነገር ግን በተከራካሪ ወገኖች ጠያቂነት የሚቀርቡ የሰነድ(የፅሁፍ) ማስረጃዎች መቸና በምን ሁኔታ ሊቀርቡ ይችላሉ? የፍርድ ቤታችን አሰራርስ በምን አግባብ እና ሁኔታ እያስተናገድናቸው ነው? የአሰራር ክፍተት ካለ በምን አግባብና በህግ አግባብ እንዴት ይስተካከል?
ለምሳሌ1ኛ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ/137መዝገቡ ለቃል ክርክር ከተቀጠረበት ቀን ቀድሞ ወይም በተቀጠረበት ቀን ቀርበው ከመዝገቡ ጋር ይያያዛሉ፤ክርክርም ይደረግባቸዋል፤ በሚል የተቀመጠው ምን አይነት ማስረጃዎች እንዲያያዙ ለመፍቀድ የተቀመጠ ነው? በምንስ አግባብ ከመዝገቡጋር ሲያያዙ ነው የቃል ክርክር የሚደረግባቸው?
2ኛ .በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ145 መሰረት በፍርድ ቤት ትእዛዝ የሚቀርቡ ማስረጃዎችን ፍ/ቤቱ እንዲቀርቡ የሚያዘው በምን ሁኔታ የሚገኙ ማስረጃወችን ነው? እንዲቀርቡ መታዘዝ ያለበት መቸ ነው?
3ኛ .በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ/256 መሰረት ከባድ እና በቂ በሆነ ምክንያት ከክሱ ወይም ከመልሱ ጋር ያልተያያዙ ወይም በቃል ክርክር ወቅት ያልቀረቡ ቢሆንም ማስረጃው እንዲያያዝ ሊፈቀድ እንደሚችል የተቀመጠው ምን አይነት ማስረጀዎችን ለማካተትና እንዲያያዙ ለመፍቀድ ነዉ?ማስረጃዉ የተገኘዉ /የተፈጠረዉ/ ክስ ከተመሰረተ ወይም ክርክር ከተደረገበት በኋላ ቢሆንስ እንዲያያዝና እንዲመረመር ይፈቅዳል ወይ?

የሊቦ ከምከም  ወረዳ  ፍ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና የኮምንኬሽን ባለሙያ ለተገልጋዪ /ለባለጉዪ/ ስለአገልግሎት አሰጣጡ ትምህርት ሲሰጥ---
12/03/2026

የሊቦ ከምከም ወረዳ ፍ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና የኮምንኬሽን ባለሙያ ለተገልጋዪ /ለባለጉዪ/ ስለአገልግሎት አሰጣጡ ትምህርት ሲሰጥ---

04/03/2026

ቀን 20/06/2018ዓ/ም
የሊቦ ከምከም ወረዳ ፍ/ቤት የዳኞች
የህግ ውይይት
የመወያያ ዕርስ
1. ተገዶ የመያዝን ህጋዊነት ለማጥራት/አካልን ነጻ ማውጣት /application for habeas corpus/
አቤቱታን በተመለከተ
2. ማህበራትን / cooperatives/ጉዳይ በተመለከተ
3. አክሲዮኖች / shares በባልና ሚስት ክርክር ፍችን ተከትሎ የሚመጣው ውጤት ክፍፍል ሲጠየቅ እና በውርስ ማጣራት ጥያቄ ላይ ፍ/ቤቱ ሊከተለው የሚገባው ስነ ስርአት ምንድን ነው? እንዴትስ ነው በኛ ፍ/ቤት እየተሰራ ያለው? ተመሳሳይነት አለ ወይ ?
 ለምሳሌ አማራ ባንክ አክስዮን ብር10000/10 እጣ/በባል ስም የተመዘገበ ቢሆን እና ሚስት ለመካፈል ብትጠይቅ ሂደቱ ምን ይሆናል?
 ወራሽ የሆነ ወላጆች ልጃቸው በአማራ ባንክ 10000 /10 እጣ /ቢኖረው እና በውርስ ማጣራት ሪፖርት ተጣርቶ ቢቀርብ ፍ/ቤቱ እንዴት ነው የሚያፀድቀው?

23/02/2026

አገራዊ እራያችን
የወረዳዉ ህብረተሰብ እየገነባ ባለዉ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እኩል ተጠቃሚ እንዲሆን መልካም አስተዳደርና ማህበራዊ ፍትህ ሰፍኖ ለክልላችን ብሎም ለሃገራችን ልማት መሳለጥ የፍርድ ስርዓቱን አጋዥ እንዲሆን ማድረግ ፣
 የሊ/ከ/ወ/ፍ/ቤት
ራዕይ፡-በወረዳዉ የህግ የበላይነት ተረጋገጦ ፍትህ ሰፍኖ ማየት
ተልዕኮ ፡-በወረዳዉ ፍትህን ለማሰፈን ዲሞክራሲያን መልካም አስተዳደርን ለመመስረት ፈጣን ወጭን ያገናዘበና ሚዛናዊ ዳኝነት መስጠት
የሊቦ ከምከም ወረዳ ፍ/ቤት በሁለት ዋና የስራ ሂደት ያሉት በዉስጡ 12 ወንድ ዳኛ 3 ሴት ዳኛ የሸሪ ዳኛ 1 ሪጅስትራር 1 ድጋፍ ሰጭ ሰራተኛ ወንድ 19 ሴት 27 በድምሩ 63 ሰራተኛ አሉት ፡፡
በ2018 ዓ/ም የመጀመሪያዉ 6 ወር በፍትሃብሔርና በወንጀል ዉሳኔ ለመስጠት የተያዘ እቅድ 1458 መዝገብ ሲሆን የተከናወነዉ 1157መዝገብ ወይም የእቅዱን 79.4% ነዉ፡፡ ይህ አፈፃፀም ለስራ ከቀረበዉ ጠቅላላ 1519 መዝገብ አንጻር ሲታይ 76.2% ይሆናል ፡፡
• በተናጥል ሲታይ ፦
የወንጀል ጉዳይ ፦
በ2018 ዓ/ም የመጀመሪያ 6 ወር ዉሳኔ ለመስጠት የተያዘ እቅድ 111 መዝገብ ሲሆን የተከናወነ 105 መዝገብ ወይም የእቅዱን 95.0 % ነዉ፡፡ይህ አፈፃፀም ለመስራት /ለመታየት ከቀረበዉ ጠቅላላ 111 መዝገብ አንፃር ሲታይ 91.0% ነዉ፡፡
 የፍትሐብሄር ጉዳይ ፦በ2018 ዓ/ም የመጀመሪያዉ 6 ወር ዉሳኔ ለመስጠት የተያዘ እቅድ1347 መዝገብ ሲሆን የተከናወነዉ 1052 መዝገብ ወይም የእቅዱን 78.1 % ነዉ፡፡ ይህ አፈጻፀም ለስራ ከቀረበዉ ጠቅላላ 1347 መዝገብ አንፃር ሲታይ 75.0 ነዉ፡፡
 በእርቅ የተዘጉ መዝገቦች
በዚህም መሰረት በ2018 ዓ/ም የመጀመሪያዉ 6 ወር ዉስጥ 28 መዝገቦች ቀርበዉ ሙሉ በሙሉ በእርቅ ተዘግተዋል ፡፡
በሸሪዓ /የቃዲ ችሎትን በተመለከተ
በወረዳችን ከመደበኛ ችሎቶች ዉጭ የእስልምና ጉዳዮች ስለሚታዪ በዚሁ ችሎት 7 መዝገቦች ቀርበዉ ሁሉም በ6 ወር ዉስጥ ዉሳኔ አግኝተዋል፡፡
በዳኝነት ስራ ለመንግስት ገቢ የተደረገ ገንዘብን በተመለከተ
ፍ/በቱ የዳኝነት ስራ በሚያከናዉንበት ጊዜ ወይም አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት ከዳኝነት ክፍያ እና ከመቀጫ ገቢዎችን ይሰበስባል፡፡በዚህም መሰረት በ2018 ዓ/ም የመጀመሪያዉ 6 ወር ዉስጥ የተገኘ ገቢ ብር 973‚652.40/ዘጠኝ መቶ ሰባ ሶስት ሽ ስድስት መቶ ሃምሳ ሁለት ብር ከአርባ ሳንቲም በመሰብሰብ ለወረዳዉ ግንዘብና ኢ/ል/ጽ/ቤት ገቢ ያደረገ ነዉ፡፡
በቅሬታ አገልግሎት ላይ በተመለከተ
 የዳሰሳ ጥናት ተካሂዷል የእርካታ ደረጃዉ 64.0%ደርሷል
 በአስተያየት መስጫ የተሰጡ አስተያየቶችን ግብረ መልሰ መለጠፍ
 ቀጠሮ የጠፋባቸዉን ባለጉዳዮች ማስተናገድ
 በህዝብ ግንኙነትና በኮምንኬሽን ባለሙያ
 አስተማሪ የሆኑ የወንጀል ቅጣቶችን ለሌሎች ትምህርት
 እንዲሆኑ ለኮምንኬሽ ጽ/ቤት እና ለሌሎች ተቋሞችም እየተላከ ይገኛል፡፡
 ባለጉዳዮች የሚገለገሉባቸዉን ፎርሞች በመጠቀም ባለጉዳዮችን ከወጭ አድነናል
 ባለጉዳዮች በፍርድ ቤቱ ላይ አመኔታ እንዲኖራቸዉ ጥዋት ጥዋት ትምህርት ይሰጣል፡፡
 የፍትህን ተደራሽነት ለማስፋት ይፋግ ከተማ የምክከር መድረክ ተካሂዷል፡፡
 በቋሙ ድረ-ገጽ ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን እንለቃለን፡፡
 የሰዉ ሃይልንበተመለከተ
በፍርድ ቤቱ ያሉ መደቦች 52
በሰዉ ሃይል የተሸፈነ 46 መደብ በጀት ያላቸዉ መደቦች 2 በጀት የሌላቸዉ መደቦች 4
በአጠቃላይ የሚመጡ መመሪያዎች ተግባር ላይ ይዉላሉ፡፡ የሊቦ ከምከም ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አበዛሽ አድማሱ ከዳኞችና ከሰራተኞች ጋር ስለ ስራ ዉይይት ሲያካሂዱ በወረዳችን አንፃራዊ ሰላም በመምጣቱ በርካታ የባለጉዳይ ፍሰት ስላለ ስዓትን በማክበር በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል እንዳለባቸዉ ውይይት አደረጉ፡፡ እንዲሁም የዳኞችና የሙየያተኛ አለመመጣጠን ክፍተት እንዳይፈጠር ባለጉዳዮችን እያስተናገዱ ይገኛሉ፡፡

የሊቦ ከምከም ወረዳ ፍ/ቤት የህዝብ ግንኙነትእና የኮምንኬሽን  ባለሙያ ለባለጉዳዪ ስለ አገልግሎት አሰጣጡ ትምህርት ሲሰጥ /////
19/02/2026

የሊቦ ከምከም ወረዳ ፍ/ቤት የህዝብ ግንኙነትእና የኮምንኬሽን ባለሙያ ለባለጉዳዪ ስለ አገልግሎት አሰጣጡ ትምህርት ሲሰጥ /////

16/02/2026
የሊቦ ከምከም ወረዳ ፍ/ ቤት ከባለጉዳዮች ጋር በይፋግ ከተማ የተዘጋጀ የምክክር መድረክየካቲት 01/06/2018ዓ/ም          ይፋግየሊቦ ከምከም ወረዳ ፍ/ቤት የካቲት 1/06/2018 ዓ...
10/02/2026

የሊቦ ከምከም ወረዳ ፍ/ ቤት ከባለጉዳዮች ጋር በይፋግ ከተማ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ
የካቲት 01/06/2018ዓ/ም
ይፋግ
የሊቦ ከምከም ወረዳ ፍ/ቤት የካቲት 1/06/2018 ዓ/ም ይፋግ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል ባጠቃላይ የዚህ የምክክር መድረክ ዋና አላማው የፍ/ቤቱን ራዕይና ተልዕኮ ግንዛቤ በመፍጠር ስለ ፍ/ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በርካታ የግዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ገለፃ ተደርጎ የፍርድ ቤቱን ራዕይና ተልኮ በማስፈፀም መልካም አስተዳደርን መሰረት አድርጎ ፈጣን ቀልጣፋና ከአድሎ የፀዳ ከሙስና ነፃ የሆነ ዳኝነት በመስጠት ህብረተሰቡን ቀጥተኛ ፍትህ እንዲያገኝ ማድረግና በፍትህ አሰጣጡ ዙሪያ ሊሻሻሉ የሚገባቸውን አሰራሮችና ክፍተቶች/ድክመቶች/ እንዲሁም ለፍ/ቤቱ ግብዓት ይሆኑት ዘንድ ከምክክር መድረኩ ተሳታፊወች ጋር በመወያያት ገንቢ አስተያየቶችን ከማህበረሰቡ በመቀበል ለፍ/ቤቱ እንደ ግብዓት ለመጠቀምና ለወደፊቱ ያሉትን የአሰራር ችግሮችና ድክመቶችን ለመለየትና ለማሻሻል የተደረገ የውይይት መድረክ ነው፡፡ ባጠቃላይ የዚህ የውይይት መድረክ ትልቁና ዋና አላማው የተገልጋዮችን ማህበረሰብ የፍትህ ተደራሽነትን በማስፈን የፍ/ቤቱን ራዕይና ተልዕኮ ማስፈፀም ነው፡፡

የሊቦ ከምከም ወረዳ ፍ/ቤት  በቀን 29/05/2018 ዓ/ም   5ኛ ዙር የዳኞች የህግ ዉይይት አካሄዱ1.አባትነት ይረጋገጥልኝ  ጥያቄ  እናት ሞግዚትነት ሳታሳዉጅ መጠየቅ ትችላለች ወይ ? አ...
09/02/2026

የሊቦ ከምከም ወረዳ ፍ/ቤት
በቀን 29/05/2018 ዓ/ም
5ኛ ዙር የዳኞች የህግ ዉይይት አካሄዱ
1.አባትነት ይረጋገጥልኝ ጥያቄ እናት ሞግዚትነት ሳታሳዉጅ መጠየቅ ትችላለች ወይ ? አባትነት ይረጋገጥልኝ ጥያቄ በማን ነዉ የሚቀርበዉ?እናት ሞግዚትነት ሳታሳዉጅ ያረጋገጠችዉ አባትነት ለልጁ ማስረጃ ይሆናል ? ወይ
2.የፍ/ህ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቅ 358 ለሁሉም ጉዳዮች ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ወይስ exception አለዉ
3.ተከሳሽ በሌለበት በተባለበት ክርክር በአንደኛዉ ቀጠሮ ላይ ከሳሽ ቢቀርና መዝገቡ ቢዘጋ እና መዝገቡ ቢንቀሳቀስ ለተከሳሽ መጥሪያ ይላካል እና ተከሳሽ ቀርቦ የሚከተለዉን ሂደት ወይም የሚያስጠብቀዉ መብት አለ ?

የህዝብ ግንኙነትና የኮምንከሽን ባለሙያ ለባለጉዳዪች ስለ አገልግሎት አሰጣጡ ትምህርት ሲሰጥ ፡-
06/02/2026

የህዝብ ግንኙነትና የኮምንከሽን ባለሙያ ለባለጉዳዪች ስለ አገልግሎት አሰጣጡ ትምህርት ሲሰጥ ፡-

Address

Amhara, South Gondar, Addis Zemen
Addis Zemen

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Libo Kemkem Woreda Court/ሊቦ ከምከም ወረዳ ፍርድ ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share