13/03/2023
አባቴ ጎበዝ ገበሬ ነበር። ምርቱም የሰመረለት እንበል። ችግሩ እሱ ብዙ ምርት ሰብስቤያለሁ እያለ ቢያወራም ልጆቹ እና ሚስቱ ግን በጠኔ ልናልቅ ሆነ።
ይሄ ጉዳይ ያስጨነቀው ሀብታሙ ጎረቤታችን እነ እዚህ ሰዎች በረሀብ ሲያልቁ ዝም ብዬ አላይም ብሎ ቀለብ ልግዛላቸው ይላል።
ይሄን የሰማው አባቴም፣ ሀሳብህ ድንቅ ነው፣ ፈጣሪም ይወደዋል። ግን እህሉን ከሌላ ቦታ ከምትገዛ ከእኔ ግዛኝ እና ለቤተሰቦቼ ስጣቸው።
በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መታህ ማለት ነው አለ እራሱን እንደ ብልህ እየቆጠረ።
አይ አባቴ!
Tewodros semere