የወራቤ ከተማ አስተዳደር ግብርና ልማት ጽሕፈት ቤት-Werabe City Agricultural Development

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የወራቤ ከተማ አስተዳደር ግብርና ልማት ጽሕፈት ቤት-Werabe City Agricultural Development

የወራቤ ከተማ አስተዳደር ግብርና ልማት ጽሕፈት ቤት-Werabe City Agricultural Development ​"የወራቤ ከተማ አስተዳደር ግብርና ልማት ጽሕፈት ቤት።
ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ፣ አምራችነትን በማሳደግ እና አርሶ አደሩን በመደገፍ የከተማዋን እና የአካባቢዋን የግብርና ልማት ለማፋጠን እንሰራለን!"

በወራቤ ከተማ የጃክ ፍሩት ተከላ ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ!የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የአረንጓዴ ልማትን ለማፋጠን ታላቅ ተስፋ የተጣለበት እንዲሁም አዲስ እንሼቲቭ የሆነዉና የፍራፍሬ ንጉስ...
06/06/2026

በወራቤ ከተማ የጃክ ፍሩት ተከላ ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ!

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የአረንጓዴ ልማትን ለማፋጠን ታላቅ ተስፋ የተጣለበት እንዲሁም አዲስ እንሼቲቭ የሆነዉና የፍራፍሬ ንጉስ በመባል የሚታወቀዉ ጃክ ፍሩት(jackfruit) ተከላ ንቅናቄ በወራቤ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።

ይህ የልማት እርምጃ በከተማዋ የፍራፍሬ ምርትን ለማሳደግና በየጓሮው አዳዲስ የገቢ ምንጮችን ለመፍጠር ያለመ ነው።

የወራቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ያሲን ከሊል በዚህ ወቅት እንዳሉት ከፍተኛ ምርት በመስጠት ዘርፈ ብዙ እኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚሰጥ መሆኑን በመጥቀስ በዞናችን እየተስፋፋ የሚገኝ አዲስ የፍራፍሬ አይነት መሆኑን ተናግረዋል።

በመንገድና በሌሎችም መሰረት ልማቶች ምክንያት በማይነሳበት አግባብ መትከል እና በቋሚነት መጠበቅ እንደሚገባም አቶ ያሲን ከሊል አመላክተዋል።

በከተማው ዙሪያ የሚገኙ አርሶአደሮች ይህንን ጠቃሚ የልማት ተግባር በመቀበል በየጓሮአቸው የጃክ ፍሩት ችግኞችን እንዲተክሉና ተገቢዉን እንክብካቤ እንዲያደርጉ ከንቲባው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዕለቱም በአቶ ሪድዋን ኣደም ጥምር ግብርና ማሳ ላይ የሙዝና የመኖ ተከላ ተከናውኗል።

በአረንጓዴ ልማት ላይ አዲስ አሻራ ለማሳረፍ የተጀመረው ይህ ንቅናቄ፤ በከተማዋ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች፣በከተማው በሚገኙ ክፍት ቦታዎች እና በአርሶአደሮች ጓሮ ላይ በስፋት ይተገበራል ተብሏል።

አካባቢን ከአየር ንብረት መዛባት ከመጠበቅ ባለፈ በከተማ ግብርና የነዋሪዎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እምቅ አቅም እንደሚሆን ተመላክቷል።

የወራቤ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ናስር ቡሽራ፣የከተማዉ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ነስሬ አማን፣የወራቤ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጃፈር ጃቢር ፣የከተማዉ ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ስመኝ ገዛኸኝ፣የግብርና ባለሙያዎች እና ሌሎችም በተከላ መርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ግንቦት 29፣2018[ወራቤ ኮሙኒኬሽን]

ከስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ የተላለፈ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት ለሁሉም የዞናችን አካባቢዎች፦እንደሀገራችን ብሎም በዞናችን በተለያዩ ጊዜያት የአየር ንብረት ለዉጥን ተከትሎ በርካታ የሰብል ...
06/06/2026

ከስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ የተላለፈ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት ለሁሉም የዞናችን አካባቢዎች፦

እንደሀገራችን ብሎም በዞናችን በተለያዩ ጊዜያት የአየር ንብረት ለዉጥን ተከትሎ በርካታ የሰብል በሽታና ተባዮች እየተከሰቱ በሰብል ላይ ጉዳት እያደረሱ ሲሆን ይህንንም በተደራጀ መልኩ ለመከላከል እየተሰራ ይገኛል።

ከነዚህ ተባዮች መካከል በአሁኑ ወቅት በዞናችን በሳንኩራ ወረዳ በሁለት ቀበሌያት (ረግዲና ቆሬ እና ኩሉፎ ሻግዳር) መደበኛ ተምች (African army worm) ተከስቶ በበልግ ወቅት በለሙ ሰብሎች ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ተለይቶ ለመከላከል ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡

ተምቹ ተዛማች በመሆኑ በቀላሉ ወደ ሌሎች የዞናችን አካባቢዎች ጭምር ሊስፋፋ ስለሚችል ሁሉም ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን የባለሙያ ምክረ-ሃሳብ በመከተል የአሰሳ፣የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ ማከናወን እንደሚገባ የዞኑ ግብርና መምሪያ የጥንቀቄ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የመከላከያ ዘዴዎችን በተመለከተ

የአፍሪካ አርሚ ወርም ምልክቶች
· ብዙ እጮች በአንድ ጊዜ በመንጋ ይንቀሳቀሳሉ።
· ቅጠሎችን በፍጥነት ይበላሉ፣ አንዳንድ ጊዜ ሙሉ ማሳ ሊጎዳ ይችላል።
· በቀን ብዙውን ጊዜ በአፈር ወይም በተክል ስር ይደበቃሉ።

ባህላዊ የመከላከያ ዘዴዎች ማስቀደም ነገር ግን ክስተቱ ከፍተኛ ከሆነ ኬሚካል ርጭት በማድረግ መከላከያ ዘዴ ጥቅም ላይ ይዉላል፡፡

ባህላዊ መከላከያ ዘዴዎች
• እጮቹ በመንጋ ሲጓዙ በፊታቸው ጉድጓድ መቆፈር እና ወደ ጉድጓዱ እንድገቡ ማድረግና ማጥፋት።
• በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እጮቹን በእጅ መሰብሰብ፣
• እሾክ በለያቸዉ ላይ መጎተት፣
• በእንስሳት መስረገጥ፣
• አረምን በፍጥነት ማስወገድ።
• ወፎች እንዲመጡ ሁኔታ መፍጠር።

በኬሚካል ዘዴ ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውሉ አግሮ-ኬሚካሎች
• Lambda-cyhalothrin
• Deltamethrin
• Cypermethrin
• Emamectin Benzoate

መረጃው የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ ነው

03/06/2026
25/05/2026
በወራቤ ከተማ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 53 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በቁጥጥር ሥር ዋለ​ወራቤ፤ ግንቦት 09/2018 (የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ)​በወራቤ ከተማ አስተዳደር በሕገ-...
17/05/2026

በወራቤ ከተማ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 53 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በቁጥጥር ሥር ዋለ

​ወራቤ፤ ግንቦት 09/2018 (የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ)

​በወራቤ ከተማ አስተዳደር በሕገ-ወጥ መንገድ ተጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረ 53 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የከተማው አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ማዳበሪያው ሊያዝ የቻለው ግንቦት 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 5:00 ሰዓት ገደማ፣ መነሻውን «ፉጌ» ቀበሌ ልዩ ስፍራው «ሰንዳቦ (ሻማ) ሜዳ» ከተባለ አካባቢ አድርጎ ሲንቀሳቀስ ከኅብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሠረት በተደረገ ጥብቅ ክትትል እንደሆነ ተገልጿል። ኮድ 3 - 08673 የሰሌዳ ቁጥር በሆነ አይሱዙ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ላይ ተጭኖ ለማምለጥ ሲሞክርም በዕለቱ በሥራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ከፍተኛ ጥረት በቁጥጥር ሥር ሊውል ችሏል።

የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ ዋና ሳጅን ነስረዲን ሰይድ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ድርጊቱን በፈጣን ጥቆማ ለደገፈው ማኅበረሰብ እና ለፖሊስ አባላት ምስጋና አቅርበዋል። ይህ ሕገ-ወጥ ማዳበሪያ ሊያዝ የቻለው በሕዝብና በፖሊስ የጋራ ቅንጅት መሆኑን የገለጹት ዋና ሳጅን ነስረዲን፤ በተለይም ለአርሶ አደሩ የሚቀርቡ የግብርና ግብዓቶችን ለግል ጥቅም በሕገ-ወጥ መንገድ ለማዘዋወር በሚሞክሩ አካላት ላይ ፖሊስ ጥብቅ እርምጃ መውሰዱን እንደሚቀጥል አስጠንቅቀዋል። ኅብረተሰቡም ጥቆማ የመስጠት ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።


በነጅሙዲን ናስር (ረ/ኢንስፔክተር)

08/05/2026
08/05/2026
05/05/2026
05/05/2026
05/05/2026

Address

Central
Addis Ababa
NO

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:30
Tuesday 08:00 - 17:30
Wednesday 08:00 - 17:30
Thursday 08:00 - 17:30
Friday 08:00 - 17:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የወራቤ ከተማ አስተዳደር ግብርና ልማት ጽሕፈት ቤት-Werabe City Agricultural Development posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share