23/05/2026
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ-05 ጽዳት እና ውበት አስ/ጽ/ቤት "ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ አደጋ ስጋት ሊሆን አይገባም!" በሚል መሪ ቃል በወረዳ ደረጃ ሳምንታዊ የተቋም የአንድ ማዕከል የጽዳት ንቅናቄ በኒዉ ኢራ ት/ቤት የተደረገ ሲሆን በዚህ ንቅናቄ ወቅት በደረቅ ቆሻሻ ልየታ እንዲሁም የተቋም እና የብሎክ ጽዳት ንቅናቄ ዙሪያ በማዕከል ደረጃ ግንዛቤ የተሰጠ ሲሆን በሁሉም ት/ቤቶች እና ተቋማት የጽዳት ንቅናቄ ስራዎች እና ግንዛቤ የመስጠት ስራዎች ተሰርቷል።