KSC Woreda 07 Islamic Affairs Council

KSC Woreda 07 Islamic Affairs Council Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from KSC Woreda 07 Islamic Affairs Council, Public Service, kirkos Woreda 07, Addis Ababa.

09/04/2026
15/02/2026
በቂርቆስ ክፍል ከተማ የወረዳ 07 እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ  !ጥሪ 23/2018 .. በቂርቆስ ክፍል ከተማ የወረዳ 07 እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት በዛሬው እለ...
31/01/2026

በቂርቆስ ክፍል ከተማ የወረዳ 07 እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ !

ጥሪ 23/2018 ..
በቂርቆስ ክፍል ከተማ የወረዳ 07 እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት በዛሬው እለት ጥሪ 23/2018 አንደኛ መደበኛ አካሄደዋል ።..
ባካሄደዉ የአንደኛ መደበኛ የጠቅላላ ጉባኤ እስከዛሬ የሰራቸውን ስራዎች ለጠቅላላ ጉባኤው ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን የ2018 የበጀት አመት ሊሰራቸው ያሰባቸውን እቅዶችና በጀቱን በጠቅላላ ጉባኤው አፅድቋል።..
በጉባኤው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መጅሊስ አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መታደማቸው ተገልጿል።

የቶፊቅ መስጂድ ጊዜያዊ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።ዜና፣መጅሊስ፣ጥር 8/2018 ዓ.ል. አ.አ.በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና በአዲስ አበባ መጅሊስ ትብብር የሚገነባው ቶፊቅ ...
17/01/2026

የቶፊቅ መስጂድ ጊዜያዊ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ዜና፣መጅሊስ፣ጥር 8/2018 ዓ.ል. አ.አ.

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና በአዲስ አበባ መጅሊስ ትብብር የሚገነባው ቶፊቅ መስጂድ የዋና መስጂድ ግንባታው እስኪጠናቀቅ የሚያገለግለው ጊዜያዊ መስጂድ ተጠናቆ ዛሬ የሰላት አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

የዛሬውን ሰላት ያሰገዱት የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ ባደረጉት ኹጥባ መስጂድ የአላህ ልቅና የሚጎላበት፤ አላህ በብቸኝነት የሚመለክበት ቦታ መሆኑን አስታውሰዋል።

የዚህ ጊዜያዊ መስጂድ አምሮ መገንባት ብቻውን በቂ ባለመሆኑ ሙዕሚኖች መስጂዱን በዒባዳ የበለጠ ልናሳምረው ይገባል ብለዋል።

መስጂዶች የአላህ ስም ከፍ የሚልበት ቦታ መሆኑን በስፋት ያነሱት ፕሬዝደንቱ መስጂዶች ከአምልኮ በተጨማሪ የሰዎች መልካም ስብዕና የሚገነባበት በመሆኑ ልዩ ቦታ አላቸው በማለት ተናግረዋል።

ጊዜያዊ መስጂዱ እንዲገነባ፤ ወደፊትም ከተማችን አይታው የማታውቀውን ውብ መስጂድ ለሚገነቡት ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ ዓላሙዲን እና ይህ ትልቅ ምኞት ዕውን እንዲሆንና የተሳካ ስራ እንዲሠራ ምክንያት ለሆኑት አቶ ጀማል አሕመድ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዚህ አጋጣሚ አዲስ አበባ መጅሊስ ከማንኛውም መልካም ሰሪዎች ጋር በቅንነትና በትብብር ለመሥራት ሁሌም ዝግጁ መሆኑን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በከተማችን የሚገኙ ቦታዎች ላይ አቅም ያላችሁ ወንድም እህቶች ለተመሳሳይ መልካም ስራ እገዛ እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

ቶፊቅ መስጂድ ሲጠናቀቅ ከሁሉም ዓይነት ኸይር ስራዎች የሚከወንበት፤ መልካም ትውልድ የሚታነፅበት ይሆናል።

በኹጥባው ላይ አሁን ያለንበት የሐጅ ወቅት እንደመሆኑ ዘንድሮ ሐጅ ለማድረግ ንያ ያላቸው ሙስሊሞች ከጥር 18/2018 ወዲህ እንዲመዘገቡ መልዕክት ተላልፏል።

09/01/2026
በግዜያዊነት የተገነባው ቶፊቅ መስጂድ የፊታችን ጁምዓ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አማካኝነት የኢስላምን እሴት የሚገልፅና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተገንብቶ ለከተ...
07/01/2026

በግዜያዊነት የተገነባው ቶፊቅ መስጂድ የፊታችን ጁምዓ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አማካኝነት የኢስላምን እሴት የሚገልፅና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተገንብቶ ለከተማዋም ተጨማሪ ውበትን ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀው የቶፊቅ (ፍልውሀ) መስጂድ ግንባታውን ሊጀምር የመጨረሻ ምእራፍ ላይ ይገኛል::

የመስጂዱ ዋና ግንባታ ከመጀመሩ በፊት በግዜያዊነት ለመስገጃ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ ጊዜያዊው መስጂድ በተፋጠነ መልኩ ተገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።

በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ እና ሌሎች የከፍተኛ ምክር ቤቱ አመራሮች የግዜአዊ መስጂዱ የግንባታ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ በቦታው በመገኘት ምልከታ አድርገዋል።

ግዜያዊው መስጂድ ከጥቂት ስራዎች በስተቀር ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ መጠናቀቁን የግንባታው አስተባባሪ ለአመራሮቹ የገለፁ ሲሆን የፊታችን ጁምዓም ግዜያዊ መስጂዱ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አብራርተዋል።

ቶፊቅ መስጂድ ተገንብቶ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ይህ አሁን ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነው ግዜያዊ መስጂድ ዋናው መስጂድ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር በግዜያዊ መስጂድነት የተገነባው ፈርሶ ቦታው ለሌላ ተግባር እንደሚውል ተገልጿል።

የቶፊቅ (ፍልውሀ) መስጂድ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በትብብር ለመስራት ከዚህ በፊት ስምምነት ላይ መድረሳቸው የሚታወቅ ነው።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት

ነባራዊ ሁኔታችንን መረዳት ለዕቅዳችን መሳካት ወሳኝ ነው ተባለ።ዜና፣መጅሊስ፣ታህሳስ 19/2018 ዓ.ል. አ.አ.የቂርቆስ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለወረዳ አመራሮች የግንዛቤ ማ...
28/12/2025

ነባራዊ ሁኔታችንን መረዳት ለዕቅዳችን መሳካት ወሳኝ ነው ተባለ።

ዜና፣መጅሊስ፣ታህሳስ 19/2018 ዓ.ል. አ.አ.

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለወረዳ አመራሮች የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠና ዛሬ ተሰጥቷል።

በስልጠና መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ መጅሊስ የስራ አስፈጻሚ አባልና የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ተጠሪ ኡስታዝ ሳላሃዲን መለስ፤ የክፍለ ከተማው መጅሊስ ምክትል ስራ አስፈጻሚ ኡስታዝ ባሐሩ ዑመር፤ ዋና ፀሐፊው ኢንጂነር ኢስሐቅ አብዱልዓዚዝ፤ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ኢማሞችና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

ክፍለ ከተማችን ከሰው ኃብትና ከሌሎች ጉዳዮች አንፃር የታደለውን ፀጋ በማስተባበር የተሻለ ስራ መስራት ይቻላል የሚለውን ሀሳብ ዋና ፀሐፊው ኢንጂነር ኢስሐቅ አብዱልዓዚዝ ገልፀዋል። በመሆኑም የወረዳ አመራሮች በየወረዳችሁ ያለውን መልካም ዕድል በመጠቀም የላይኛውን መዋቅር ሳትጠብቁ የአካባቢያችሁን ሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሔ መስጠት ይገባችኋል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

መጅሊስ ከረጅም ትግል በኋላ በሕዝብ ይሁንታ ተመርጦ የተለያዩ ተግባራትን መስራት የጀመረ መህኑን ምክትል ስራ አስፈጻሚ ኡስታዝ ባሐሩ ዑመር የገለፁ ሲሆን ክፍለ ከተማውም በዚሁ ሂደት ላይ መሆኑን አብራርተዋል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መጅሊስ ከወረዳና ክፍለ ከተሞች አመራሮች፤ ከዑለማዎች፣ ከሴቶችና ከወጣቶች ጋር በመገናኘት በክፍለ ከተማው መሠራት ስላለባቸው ተግባራት መግባቢት ላይ ተደርሶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በስካሁኑ ሂደት ከስራ ባሻገር የተጓደሉ አመራሮችን በመተካትና ጉዳዮች የጋራ የማድረግ ተግባርም ሲከናወን እንደነበር አንስተዋል።

በስራ ሂደታችን የገጠሙንንና በቀጣይ የምንሰራቸውን ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ የዛሬው ስልጠና አስፈላጊ መሆኑኔም ጨምረው ገልፀዋል።

ይህ ስልጠና ከዘጠና ቀናት ዕቅድ ውስጥ አንዱ መሆኑን የገለፁት ኡስታዝ ባሕሩ የተሰጠንን አደራ ለመወጣት የዚህ ዓይነት የግንዛቤ ማስጨበጫ አጋጣሚ ሲገኝ መጠቀም እንደሚያስፈልግም ተብራርቷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ መጅሊስ የስራ አስፈጻሚ አባልና የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ተጠሪ ኡስታዝ ሳላሃዲን መለስ ለሁለንተናዊ ተግባሮቻችን ስኬት አስፈላጊ በመሆኑ የአቅም ማሳደጊያ ስልጠናው ይቀጥላል ብለዋል።
ወደ ኃላፊነት የመጣንበት መንገድ በሕዝብ ምርጫ በመሆኑ የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን በብቃትና በአመራር ጥበብ ማለፍ ይገባል፤ ለዚህም መሠል ስልጠናዎች ያስፈልጋሉ ብለዋል።

ስልጠናውን የሰጡት በከፍተኛ ትምህርት ተቋም መምህርነት፤ በተቋማት ምስረታ፣ ስልጠናና ማማከር ላይ ከፍተኛ ዕውቀትና ልምድ ያላቸው ዶ/ር ደስታ ሙሉጌታ ናቸው።

ዶክተር ደስታ የመጅሊስ አመራሮች የማሕበረሰቡን ፍላጎት ለማሳካት ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ተቋም የተናበበ፤ በግል የሚታወቅና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የተጋራ ራዕይ መያዝ ያስፈልጋል ብለዋል። ሁላችንም የየድርሻችንን እንወጣ፤ የዲን ትምህርቶቻችን ውጤታማና አንድነትን የሚያስጠብቁ ይሁኑ ሲሉ ገለፃ አድርገዋል።

መሪነት ዕውቀት፤ አስተዋይነት፣ አዋጭ ድፍረት፣ የስሜት ብልጠትንና ሌሎች መገለጫዎችን የያዘ ሲሆን እነዚህን ከነባራዊ ዕውነታው ጋር አጣጥሞ መምራት ይጠበቅብናል ሲሉ ዶክተር ደስታ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሰልጣኞች አሳታፊ በነበረው ቆይታ ጠቃሚና ለስራቸው አጋዥ የሆኑ ነጥቦች ስለማግኘታቸው ተናግረዋል። ይሁንና የተሻለ ውጤታማ ለመሆን በቀጣይም መሠል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች እንዲኖሩ ተጠይቋል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት

18/12/2025

በግል ትኬት ለሚጓዙ ሑጃጆች ከ176 ሺህ ብር በላይ ቅናሽ ተደረገ።

740 ሺህ ብር ለዘንድሮ የሐጅ አገልግሎት ክፍያ የተተመነ የብር መጠን ሲሆን በግል ትኬት ለሚጓዙ ሑጃጆች ደግሞ የ176 ሺህ 420 ብር ቅናሽ ተደርጓል።

በዚሁ መሠረት ትኬታቸውን በግል የሚያዘጋጁ ሑጃጆች መጅሊስ መጥተው ምዝገባ ካደረጉ በኋላ የሚከፍሉት ክፍያ 563 ሺህ 580 ብር ይሆናል ማለት ነው።

የሐገር ውስጥ የሐጅ መስተንግዶ ሲገባደድ ወደ ሳውዲ የሚደረገው በረራ ሚያዝያ ወር ማለቂያ ላይ ይጀምራል።

በዚሁ መሠረት ሚያዝያ 24/2018 ወይም May 2/2026 የመጀመሪያው በረራ ይሆናል።

ግንቦት 13/2018 ወይም May 21/2026 ወደ ሳውዲ (ከአዲስ አበባ መዲና) የሚደረገው በረራ የመጨረሻው ቀን ይሆናል።

መመለሻን በተመለከተ(ከጅዳ ወደ አዲስ አበባ)፦

ግንቦት 25/2018 ወይም June 2/2026 ወደ ሀገር ቤት መመለስ የሚጀምርበት ነው።
የመመለሻ የመጨረሻው ቀን ሰኔ 8/2018 ወይም June 15/2026 ይሆናል።

በመሆኑም የግል ትኬት የምትጠቀሙ የአራህማን እንግዶች ትኬታችሁን በእነዚህ የተጠቀሱ ቀናት ውስጥ እንድታመቻቹ እናሳውቃለን።

ሑጃጆች የተቀመጡ የሕክምና ማስረጃ ዶክመንቶችን እንዲያሟሉ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ክፍል ኃላፊ ኢስሐቅ አብዱልዓዚዝ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

Address

Kirkos Woreda 07
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when KSC Woreda 07 Islamic Affairs Council posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category