Bakusa National Park

Call Contact the organization

Bakusa National Park To protect the biodiversity wild life management

➧እንኳን ደስ አለህ!! ክብር ለሁሉም ሬንጀሮቻችን🙏
04/08/2026

➧እንኳን ደስ አለህ!! ክብር ለሁሉም ሬንጀሮቻችን🙏

01/08/2026
01/08/2026
ሁሉንም ከሆኑት የዱር ሕይወት ሬንጀሮች ጋር እሆናለሁ።World Ranger Day እያከበርን ነው። የዱር ሕይወት ሬንጀሮች ሁሉንም ናቸው። እንደ መምህር ማኅበረሰብን ስለ ዱር እንስሳት ያስተም...
30/07/2026

ሁሉንም ከሆኑት የዱር ሕይወት ሬንጀሮች ጋር እሆናለሁ።
World Ranger Day እያከበርን ነው። የዱር ሕይወት ሬንጀሮች ሁሉንም ናቸው። እንደ መምህር ማኅበረሰብን ስለ ዱር እንስሳት ያስተምራሉ። ደግሞ የደህንነት ኦፊሰር ናቸው። የዱር ሕይወቱንም የፓርክ ጎብኚዎችንም ከአደጋ ይጠብቃሉ። ሐኪም ናቸው። የዱር ሕይወት ህመምን ይለያሉ። የዱር እንስሳትን በሽታዎችን ይመረምራሉ፤ ወላጅ አልባ ዱር እንስሳትን ይንከባከባሉ። ሳይንቲስት መሆናቸውን እነግራችኋለሁ። በዱር እንስሳት ጥበቃ ላይ ለሚገጥሙ ችግሮች ከሥነ-ምህዳር ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ሳይንሳዊ ምርምር ያደርጋሉ። በፓርኩ ውስጥ ስለሚከሰቱ የተፈጥሮ ክስተቶች ያጠናሉ፣ ማስታወሻ ይይዛሉ፤ ሪፖርት ያደርጋሉ። እንደ መሐንዲስ መንገድ ጠግነው፣ አጥር ሰርተው፣ የውሃ እና የአፈር መሸርሸር ተከላክለው ይሰራሉ። እንደ የሕዝብ ግንኙነት በሰዎች እና በዱር እንስሳት መካከል ሰላማዊ አብሮ መኖር ላይ ይሰራሉ። በየዓመቱ ሐምሌ 24 ቀን በመላው ዓለም የእነኚህን ጀግኖች ቀን እናከብራለን። የዘንድሮው መሪ ቃል “Rangers: Guardians of a Changing Planet,” የሚል ነው። አንድም ብዙም ለሆኑት ጀግኖች ክብር እየሰጠን ቀኑን ማክበራችንን እንቀጥላለን።
We stand with the world's rangers.
Ethiopian Wildlife Rangers Association
International Ranger Federation
Game Rangers International
Game Rangers Association of Africa


Henok syoum /ተጓዡ ጋዜጠኛ/

13/07/2026

የሀገራችን የተፈጥሮ ኩራት ዋልያን ለማዳን የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ በእጅጉ ወሳኝ ነው።

ሐምሌ 5/2018 ዓ.ም
ኢዱጥባ

የኢትዮጵያ ብርቅዬ እና የተፈጥሮ ምልክት የሆነው ዋልያ አይቤክስ (Walia Ibex) የህልውና አደጋ ውስጥ መግባቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለዓለም የተፈጥሮ ቅርስ ጥበቃ ትልቅ ስጋት ፈጥሯል።

በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ ብርቅዬ ፍጥረት ከጥፋት ለመታደግ የአካባቢው መስተዳደር እና ማህበረሰብ፣ አጋር ድርጅቶች፣ የምርምር ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማትና ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀና የተጠናከረ ርብርብ ማድረግ ወሳኝ ነው።

የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በ1978 ዓ.ም. በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ከተመዘገቡ የመጀመሪያዎቹ ቅርሶች አንዱ ነው። ለዚህ የቅርስነት እውቅና ዋልያ በፓርኩ መገኘቱ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከቱ ይታወቃል።
ዋልያን መጠበቅ የአንድ የዱር እንስሳ ጥበቃ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የአገራችንን የተፈጥሮ ቅርስ፣ የብዝሃ ሕይወት እና የቱሪዝም እሴት መጠበቅ ጭምር ነው።

በ2016/17 የበጀት ዓመት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን፣ የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ እና ከአፍሪካን ዋይልድ ላይፍ ፋውንዴሽን (AWF) የተውጣጡ የጥናትና ምርምር ባለሙያዎች በመተባበር “Walia Ibex Decline Root Cause Assessment” የተሰኘውን ጥናት አካሂደዋል ።

የጥናቱ ውጤትም ከሰሜኑ ጦርነት ጋር ተያይዞ በዋልያ ህልውና ላይ የደረሱ አሉታዊ ተጽእኖዎችን፣ የመኖሪያ ቦታ መራቆትን፣ ህገ-ወጥ አደንን እና ሌሎች ሰው ሰራሽ ተግዳሮቶችን ለይቶ አሳይቷል።

ይህን ጥናት መነሻ በማድረግ ዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ጥበቃ ህብረት (IUCN) የዋልያ አይቤክስን ከነበረበት “ለአደጋ የተጋለጠ” (Vulnerable) ደረጃ ወደ “በእጅጉ ለጥፋት የተጋለጠ” (Critically Endangered) ደረጃ መመደቡን አስታውቋል።

ይህ ምደባ ዋልያ አይቤክስ ከመቼውም ጊዜ በላይ አፋጣኝ እና የተጠናከረ የጥበቃ እርምጃ እንደሚያስፈልገው የዓለም አቀፍ ጥሪ ነው።

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ከአጋር ተቋማት፣ ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአካባቢው መስተዳደር እና ማህበረሰብ እንዲሁም በፓርኩ ውስጥ ከሚሰሩ ፕሮጀክቶች ጋር በመቀናጀት የተለያዩ የጥበቃ እርምጃዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል። ከእነዚህም መካከል፦
• በዋና ዋና የዋልያ መኖሪያ ቦታዎች የተጠናከረ የፓትሮል ሥራ ማከናወን፤
• ከሃይማኖት አባቶች ጋር በመቀናጀት ህገ-ወጥ አደንን ለመከላከል ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ማካሄድ፤
• በቴክኖሎጂ የታገዘ የጥበቃ ክትትል (EarthRanger) ስርዓትን መተግበር፤
• የዋልያ አምባሳደሮችን በማቋቋም የመረጃ ስብሰባና የክትትል ሥራዎችን ማጠናከር፤
• ዋልያን ለመታደግ የ10 ዓመት ብሔራዊ የተግባር ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ማስገባት ተጠቃሾች ናቸው።

ይሁን እንጂ የዋልያ ህልውና ጉዳይ የአንድ ተቋም ኃላፊነት ብቻ አይደለም። አሁን ያለው ሁኔታ የሁሉንም ኢትዮጵያውያን የጋራ ጥረትና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ነው።

በተለይም የአካባቢው ማህበረሰብ ዋልያ የአገራችን የተፈጥሮ ኩራት መሆኑን በመገንዘብ በጥበቃው ውስጥ ያለውን ተሳትፎ የበለጠ ማጠናከር ይገባል።

ዋልያ የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ማህበረሰብ ሀብት ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያና የዓለም የተፈጥሮ ቅርስ ነው።

ስለዚህ ይህን ብርቅዬ ፍጥረት ከጥፋት ለመታደግ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተጨማሪ የአካባቢው መስተዳደር፣ አጋር ድርጅቶች፣ የምርምር ተቋማት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአካባቢ ማህበረሰብ እና ሁሉም ኢትዮጵያውያን የተቀናጀና ቀጣይነት ያለው ርብርብ ማድረግ ይገባቸዋል።

የዋልያ ህልውናን መታደግ የአንድ የዱር እንስሳ ህልውናን መታደግ ብቻ ሳይሆን ለመጪው ትውልድ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ኩራትና የዓለም ቅርስ ጠብቆ ማስረከብ ነው።

21/06/2026

ተስፋን መትከል የነገን ብሩህ ታሪክ ዛሬ መጽሐፍ ነው ።

ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

➧እንጅባራ ዩኒቨርስቲን እናመሰግናለን🙏
14/05/2026

➧እንጅባራ ዩኒቨርስቲን እናመሰግናለን🙏

05/12/2025

Address

Addis Ababa
JAWIWORDAFENDIKATOWN

Telephone

+251913440039

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bakusa National Park posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Bakusa National Park:

Shortcuts

Share