Addis MESOB - One Center Digital Government Service

Addis MESOB - One Center Digital Government Service Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis MESOB - One Center Digital Government Service, Public & Government Service, Adwa Street, Arada SC, Addis Ababa.

Addis MESOB is a public office for one-stop service center designed to serve the residents of Addis Ababa with multiple public services under one roof making government services faster, more efficient, and citizen-focused.

 #የትጋት አሻራ የማንሰራራት ህያው ምስክር - አዲስ መሶብ!
07/09/2026

#የትጋት አሻራ የማንሰራራት ህያው ምስክር - አዲስ መሶብ!

የአዲስ መሶብ አመራሮችና ሠራተኞች የአራዳ ፓርክን ጎበኙ።Addis MESOB: ጳጉሜን 02/2018 ዓ.ምጳጉሜን 2 የማንሠራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ የአዲስ መሶብ ዲጂታል አንድ ማዕከል የ...
07/09/2026

የአዲስ መሶብ አመራሮችና ሠራተኞች የአራዳ ፓርክን ጎበኙ።

Addis MESOB: ጳጉሜን 02/2018 ዓ.ም

ጳጉሜን 2 የማንሠራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ የአዲስ መሶብ ዲጂታል አንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች የአራዳ ፓርክን ጎብኝተዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ተግዳሮቶቿን እያሸነፈች ሪፎርም በማካሄፍ ዘርፈ ብዙ ድሎችን አስመዝግባ በተጨባጭ የታዩ በርካታ ድሎችን በማስመዝገብ በድህነት የተደፉ አንገቶች ቀና ብለው እንዲሄዱ ለማስቻልና ለቀጣዩ ትውልድ ምቹና የበለጸገች ሀገር ለማስተላለፍ በርካታ ስራዎችን በመሥራት የማንሠራራት ምዕራፍ ላይ ደርሳለች።

ይህ ሀገራዊ ማንሠራራት በበርካታ ዘርፎች ላይ የታየ ተጨባጭ እውነታ ነው። ከዚህ ውስጥ ከተማችን አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ጽዱና ውብ እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ከዜጎች አልፎ ዓለም አቀፍ አድናቆትን ያተረፈ ተግባር ነው።

በዛሬው ዕለትም ጻጉሜን 2 የማንሰራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ ከተማችንን ከማስዋብ አኳያ ከተከናወኑ ታላላቅ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ በሆነው በአራዳ ፓርክ በአገልግሎት አሰጣጥ ስብራትን በመጠገን የበርካታ ዘመናትን የአገልግሎት ጥያቄ የፈታው የአዲስ መሶብ ዲጂታል አንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች ጉብኝት አድርገዋል።

Addis MESOB

The New Horizon of Service !

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website: addis.mesobcenter.et

Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን

አዲስ መሶብ :  የለውጥ ስኬቶችን በሚያሳይ ልዩ ዶክመንተሪ የማንሰራራት ቀንን ዘከረAddis MESOB: ጷግሜ 2/2018 ዓ.ም.የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ስር...
07/09/2026

አዲስ መሶብ : የለውጥ ስኬቶችን በሚያሳይ ልዩ ዶክመንተሪ የማንሰራራት ቀንን ዘከረ

Addis MESOB: ጷግሜ 2/2018 ዓ.ም.

የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ስር የሚገኙ ሁሉም ማዕከላት የዛሬውን "የማንሰራራት ቀን" በማስመልከት ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ የተመዘገቡ አበይት የልማት ምዕራፎችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስኬቶችንና የማህበረሰብ ህያው ምስክርነቶችን አጉልቶ የሚያሳይ ዶክመንተሪ አቅርበዋል::

በቀረበው ዶክመንተሪ ላይ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ላይ የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያዎች እና ከአገልግሎት ፈላጊዎች የተሰበሰቡ አስተያየቶች በስፋት ተዳሰዋል:: በተለይም ህዝብን ማዕከል ያደረገ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አገልግሎት የመስጠት ህልም እንዴት ወደ ተጨባጭ እውነታ እንደተቀየረ የሚያስረዱ ምስሎችና መረጃዎች ተካተውበታል::

ይህ የማንሰራራት ቀን አከባበር ተቋሙ የጀመረውን የማዘመንና የመልካም አስተዳደርን የማረጋገጥ ጉዞ ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት ያሳየ ሲሆን የመላው አመራርና ሰራተኛን ተነሳሽነት የበለጠ በመጨመር በቀጣይም በላቀ ትጋትና ውጤት ለመስራት አዲስ መነሳሳትን የፈጠረ ነው::

Addis MESOB

The New Horizon of Service!

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website: addis.mesobcenter.et
Telegram:

https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!

"የማንሠራራት ቀንከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ...
07/09/2026

"የማንሠራራት ቀን

ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!
ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል። ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Addis MESOB

The New Horizon of Service !

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website: addis.mesobcenter.et

Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!

ውድ ተገልጋዬቻችን የአከራይና ተከራይ ውል እድሳት ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም መራዘሙን ተከትሎ የአዲስ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ከሐምሌ 1 ቀን 201...
06/09/2026

ውድ ተገልጋዬቻችን

የአከራይና ተከራይ ውል እድሳት ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም መራዘሙን ተከትሎ የአዲስ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት

ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የአከራይና ተከራይ ውል ምዝገባና እድሳት አገልግሎት እስከ ጳጉሜ 5/ 2018 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እንገልፃለን።

የአከራይና ተከራይ ውል እድሳት ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር አስታውቋል፡፡

በመሆኑም እስከ ዛሬ ውላቸውን ያላደሱ ሁሉም አከራዮችና ተከራዮች ይህንን የመጨረሻ እድል በመጠቀም በሁሉም የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከላት በተዘጋጁ ቦታዎች በመቅረብ ውላችሁን እንድታድሱ ጥሪያችንን እናስተላልፍለን።

Addis MESOB

The New Horizon of Service!

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website: addis.mesobcenter.et
Telegram:

https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!

የእምርታ ቀን በመላው ሀገሪቱ ተከበረጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም “ “የእምርታ ቀን  ”በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ ተከበረ። ቀኑ ኢትዮጵያ ከተረጂነት ወደ አምራችነት በምታደርገው ሽግግር የተመ...
06/09/2026

የእምርታ ቀን በመላው ሀገሪቱ ተከበረ

ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም “ “የእምርታ ቀን ”በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ ተከበረ። ቀኑ ኢትዮጵያ ከተረጂነት ወደ አምራችነት በምታደርገው ሽግግር የተመዘገቡ የኢኮኖሚ፣ የምግብ ሉዓላዊነትና የሀገር ውስጥ ምርት ውጤቶች የሚዘክር ሆኗል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተተገበረው የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተወሰዱ የተቀናጁ ኢኮኖሚያዊ ርምጃዎች ለግል ዘርፉ መነቃቃት፣ ለገቢ እድገትና በስራ ዕድል ፈጠራ ረገድ በተመዘገቡ ድሎች የያየውን እመርታ የሚያዘክር ሆኗ ተከብሯል።

የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ረገድም በከተማ ግብርና፣ በዶሮ፣ በወተትና በማር ምርት በተለይም በስንዴ ምርት ከራስ አልፎ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የተከናወኑ ተግባራት ሀገራዊ ለውጡን ወደ ፊት በማራመድ ረገድ ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል።

በተጨማሪም “ኢትዮጵያ ታምርት” እና “አዲስ አበባ ታምርት” ንቅናቄዎች የሀገር ውስጥ አምራችነትን በማጠናከር የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የተለያዩ ስራዎችን አስችለዋል። በዚህም ስራ ያቆሙ ፋብሪካዎችን ወደ ምርት መመለስ፣ የሀገር ውስጥ ምርትን ማሳደግና የውጭ ምንዛሬን ከማዳን አንፃር አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

“የእምርታ ቀን ” የተመዘገቡ ውጤቶችን ከመዘከር ባለፈ፣ በስራ ባህል፣ በፈጠራ፣ በእውቀትና በሀገር በቀል አቅም በመጠቀም ኢትዮጵያን የበለጠ ወደ አምራችነትና ዘላቂ እድገት ለማሸጋገር የጋራ ተሳትፎን ለማድረግ የጋራ ቃልኪዳን የሚገባበት ቀን መሆን ይገባዋል።

Addis MESOB

The New Horizon of Service !

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website: addis.mesobcenter.et

Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን

03/09/2026

💡 ወደ አዲስ መሶብ ከመምጣትዎ በፊት እነዚህን 3 ነገሮች ያውቃሉ?

Addis MESOB: ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም

ጊዜዎን እና ጉልበትዎን ለመቆጠብ ወደ ማዕከላችን ከመምጣትዎ በፊት የሚከተሉትን ነጥቦች ማስተዋልዎን ያረጋግጡ፦

1️⃣ ማስረጃዎችዎን ያሟሉ፦ ለሚፈልጉት የአገልግሎት ዓይነት የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ሰነዶችንና ፎቶኮፒዎችን አስቀድመው ያዘጋጁ።
2️⃣ ዲጂታል ክፍያ፦ አገልግሎቶቻችን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ክፍያ (ቴሌብር እና በባንክ አፕሊኬሽኖች) ስለተሳሰሩ ጥሬ ገንዘብ መያዝ አይጠበቅብዎትም።
3️⃣ የወረፋ ቁጥር ይያዙ፦ ማዕከላችን እንደገቡ ዲጂታል የወረፋ ቁጥርዎን በመያዝ በጥሩ ሁኔታ በተዘጋጁ የመጠባበቂያ ስፍራዎች ተራዎን በምቾት ይከታተሉ።

አዲስ መሶብ — አገልግሎታችን ለዕረፍትዎ እና ለጊዜዎ ይመቻል፡፡

Addis MESOB

The New Horizon of Service !

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website: addis.mesobcenter.et

Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!

03/09/2026

Addis MESOB

The New Horizon of Service !

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website: addis.mesobcenter.et

Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!

"የቴክኖሎጂና የትጋት ቅንጅት፣ የአርቆ ማሰብና አልቆ መፈጸም ህያው ምስክር"- አዲስ መሶብ!Addis MESOB: ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም.ራዕይን ወደ ተግባር፣ ውጥንን ወደ ውጤት በመቀየር ረ...
02/09/2026

"የቴክኖሎጂና የትጋት ቅንጅት፣ የአርቆ ማሰብና አልቆ መፈጸም ህያው ምስክር"- አዲስ መሶብ!

Addis MESOB: ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም.

ራዕይን ወደ ተግባር፣ ውጥንን ወደ ውጤት በመቀየር ረገድ ዲጂታል ቴክኖሎጂና የተቀናጀ ትጋት ያመጡት ለውጥ በግልጽ እየታየ ይገኛል። አዲስ መሶብ የአሰራር ዘመናዊነትን ከከፍተኛ የስራ አክብሮት ጋር በማዋሃድ የነገውን ህልም ዛሬውኑ በተግባር እውን ማድረጉን ቀጥሏል።

አዲስ አበባ - የበርካታ ህልሞችና የተስፋዎች ማደሪያ - ዛሬ ላይ ጽዱ፣ ውብ እና ለሁሉም ምቹ የሆነች ተምሳሌታዊ ከተማ የመሆን የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ትገኛለች። ይህን ታላቅ ግብ መሬት ለማስረገጥ ደግሞ አርቆ ማሰብ ብቻ ሳይሆን የታሰበውን እቅድ እስከ መጨረሻው ጥግ ድረስ አልቆ መፈጸም ይጠይቃል።

መሶብ - የኢትዮጵያውያን የፍቅር፣ የአንድነትና የበረከት ምልክት እንደመሆኑ መጠን "አዲስ መሶብ" ደግሞ የተቋማዊ ብቃትና የዜጎች ክብር ማዕከል ሆኖ በስራ ላይ ይገኛል።

ሰዓታትንና ቀናትን በሚወስዱ ረጅም ሰልፎችና እንግልት የተወሳሰበውን ነባር አሰራር በዲጂታል ስርዓት በመተካት የተጀመረውን የአገልግሎት ጉዞ በጥራት፣ በፈጣን አሰራርና በበሰለ የትጋት ባህል ዳር እያደረሰ እንዲሁም ዜጎች ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን በመቆጠብ የመንግስት አገልግሎትን በግልጽነትና በፍትሃዊነት በአንድ ቦታ እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል።

በአጠቃላይ "አዲስ መሶብ" የአገልግሎት ማዕከል ብቻ ሳይሆን የቀልጣፋ አሰራር አዲስ ምዕራፍ፣ የከተማችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሪ እና የዜጎችን እንግልት ያስቀረ የዘመናዊነት ተምሳሌት ነው። የቴክኖሎጂን አቅም ከሰው ልጅ ሰብአዊ አክብሮት ጋር አዋህዶ የመጪው ዘመን ህያው ምስክር ሆኖ ይቀጥላል።

Addis MESOB:

The New Horizon of Service!

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website :addis.mesobcenter.et

Telegram :https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!

በመዲናዋ 20 ተጨማሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ። Addis MESOB: ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም.በተያዘው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ 20 አዳዲስ መሶብ የአንድ ማዕከ...
01/09/2026

በመዲናዋ 20 ተጨማሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ።

Addis MESOB: ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም.

በተያዘው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ 20 አዳዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀጣይ አምስት ዓመትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል።

ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት ÷ በምርጫ ለሕዝብ የገባነውን ቃል ለመፈጸም 24/7 በትጋት በመስራት አዲስ አበባን ተምሳሌታዊ ከተማ እናደርጋታለን ብለዋል።

ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የመዲናዋ ስትራቴጂክ ዕቅድ ከሀገራዊ ርዕይ፣ ፖሊሲና ስትራቴጂ አንጻር የተቃኘ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም ጠንካራ የተቋም ግንባታ፣ የተቀናጀ ጥራት ያለውና ሰፊ የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ አይበገሬ አረንጓዴ ኢኮኖሚ መፍጠር፣ የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር እንዲሁም ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

አሁን ላይ በከተማ አስተዳደሩ 11 የመሶብ ማዕከላት መኖራቸውን ጠቁመው ÷ በ2019 በጀት ዓመት ተጨማሪ 20 ማዕከላት እንደሚከፈቱ ተናግረዋል፡፡

ማዕከላቱ የሚከፈቱት ወረዳዎችን በክላስተር በማደራጀት እንደሆነና በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት 66 መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን ለመክፈት መታቀዱን አመልክተዋል።

በሁሉም ዘርፍ የተሳለጠ እና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከንቲባዋ አረጋግጠዋል፡፡

Addis MESOB

The New Horizon of Service !

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website: addis.mesobcenter.et

Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!

Address

Adwa Street, Arada SC
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 21:00
Tuesday 08:00 - 21:00
Wednesday 08:00 - 21:00
Thursday 08:00 - 21:00
Friday 08:00 - 21:00
Saturday 08:00 - 21:00
Sunday 08:00 - 21:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis MESOB - One Center Digital Government Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share