አቃቂ ቃሊቲ የሚሰሩ እጆች

አቃቂ ቃሊቲ የሚሰሩ እጆች የአቃቂ ቃሊቲ ሰራና ክህሎት ጽ/ቤት ተልኮ ብቁ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ የሰው ሃይል በማፍራት ለኢንተርፕራይዞች ድጋፍ በማድረግ አማራች ሀይል እንዲሆኑ ማስቻል።

ለሴፍትኔት ተጠቃሚዎች የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በሁሉም ወረዳዎች ተካሄደ።22/10/5018ዓ.ምአቃቂ ቃሊቲ====================================በአቃቂ ቃሊቲ ክፍ...
29/06/2026

ለሴፍትኔት ተጠቃሚዎች የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በሁሉም ወረዳዎች ተካሄደ።

22/10/5018ዓ.ም
አቃቂ ቃሊቲ
====================================
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት በምግብ ዋስትና ሴፍትኔት ቡድን በ2017 ዓ.ም ጀምሮ ተመልምለው የሴፍትኔት ተጠቃሚ የሆኑ GMF እና RHISN ተጠቃሚዎች ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ ለማሻሻገር የተለያዩ የድጋፍ ማዕቀፎችን ሲወስዱ የቆዩ ስሆን ከዚህ የድጋፍ ማዕቀፍ ውስጥ የስጦታ ገንዘብ (ግራንት ) አንዱ ሲሆን ስራ ለማስጀመር በዛሬው እለት 80% ለግራንት ብቁ የሆኑ GMF እና RHISN ተጠቃሚዎች አጠቃላይ በድምሩ ለ4574 ተጠቃሚዎች 80% ግራንት ለጠቃሚዎች ለማስተላለፍ የቃል ኪዳን ፎርም የሞሉ ሲሆን እንዲሁም ገንዘቡን ባዘጋጁት የንግድ ዕቅድ መስረት ተግባር ላይ ማዋል እና እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው በተጨማሪም ይህንን ገንዘብ በትክክለኛ ተግባር ላይ ካላዋሉ ቀሪ 20% ለግራንት የማይለቀቅላቸው እንደሆነ እና እንደሚያስጠይቃቸው ጭምር በ12ቱም ወረዳ ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡

"ተስፋን እንትከል" የችግኝ ጉድጓድ ዝግጅት ተካሄደ!!22/10/2018ዓ.ምአቃቂ ቃሊቲ==================================="ተስፋን እንትከል" በሚል መርህ በሀገር አቀፍ ደ...
29/06/2026

"ተስፋን እንትከል" የችግኝ ጉድጓድ ዝግጅት ተካሄደ!!

22/10/2018ዓ.ም
አቃቂ ቃሊቲ
===================================
"ተስፋን እንትከል" በሚል መርህ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች የችግኝ መትከያ ጉድጓድ ቆፍረው አዘጋጅተዋል። በስራው ላይ የክፍለከተማ አመራሮች የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም የክፍለከተማውና የወረዳ የዘርፉ ባለሙያዎችና አመራሮች፣ የምግብ ዋስትና ተጠቃሚዎች የተሳተፉ ሲሆን የጉድጓድ ዝግጅቱም በወረዳ3 ወንዝ ዳርቻ የተከናወነ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም በንቅናቄም የችግኝ ተከላው የሚከናወን ይሆናል።

የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ከአጋር ተቋማት ጋር በመሆን ማዕድ አጋራ።19/10/2018ዓ.ም====================================የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት...
26/06/2026

የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ከአጋር ተቋማት ጋር በመሆን ማዕድ አጋራ።

19/10/2018ዓ.ም
====================================
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ከአጋር ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን የማዕድ ማጋራት ስራ አከናውኗል። ጽ/ቤቱ ከቪዥን ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በመተባበር በየጊዜው እንደሚያደርገው በበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤትና በሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ለተለዩ ነዋሪዎች የመሰረታዊ ፍጆታ ድጋፍ አድርጓል።በዝግጅቱ ላይ ሃሳባቸውን የሰጡት የጽ/ቤቱ ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘነበ ወዬሳ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሁልጊዜም ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ግንበር ቀደም መሆኑን አንስተው የዛሬው ዝግጅትም የዚሁ አካል መሆኑን አብራርተዋል። ጽ/ቤቱ ከዚህም ውጪ በየወሩ ከሰራተኞች በሚሰበሰብ መዋጮ በየወሩ ገንዘብ እየከፈለ የሚያሳድጋቸው ህፃናት እንዳሉ እንስተዋል።
በመጨረሻም ይህን ድጋፍ በጽ/ቤታችን ስም ላደረጉልን የቪዥን ማይክሮ ፋይናንስ የስራ ኃላፊዎችና የስራ ባልደረቦች ምስጋና አቅርበዋል።

24/06/2026
የስራና ክህሎት ጽ/ቤት የጀነራል ካውንስል አባላት የበጀት ዓመቱን ማጠቃልያ የስራ ግምገማ አካሂዷል።=====================================ቀን17/10/2018 ዓ.ምየአቃቂ...
24/06/2026

የስራና ክህሎት ጽ/ቤት የጀነራል ካውንስል አባላት የበጀት ዓመቱን ማጠቃልያ የስራ ግምገማ አካሂዷል።
=====================================
ቀን17/10/2018 ዓ.ም
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት የጀነራል ካውንስል አባላት የ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመቱ የስራ ማጠቃለያን በተመለከተ ካውንስሉ በዛሬው ዕለት ገምግሟል። በግምገማ መድረኩ በውስጥ የሱፐርቪዥን አባላት ያደረጉትን ምልከታ እንደመነሻ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
በተጨማሪም በትናንትናው ዕለት የሪፎርም ኮሚቴ አባላት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ በጥንካሬ እና በድክመት የተነሱ ሃሳቦች በኮውንስሉ መድረክ ላይ ቀርበው ተገምግመዋል። በመድረኩም መሻሻል ያለባቸው ተግባራት ተለይተው እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል።
መድረኩን የመሩት ጽ/ቤቱ ም/ኃላፈ አቶ ዘነበ ወዬሳ የተሰሩ ስራዎች ጠንካራና ውጤታማ መሆናቸውነሰ አንስተው መስተካከልና መጠናቀቅ ያለባቸው ተግባራት በጊዜውና በሰዓቱ እንዲጨርሱ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የጽ/ቤቱ የሪፎርም ቲም አባላት የስራ አፈፃፀም  ግምገማ መድረክ ተካሄደ።12/10/2018ዓ.ምየአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት የሪፎርም ኮሚቴ አባላት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ...
19/06/2026

የጽ/ቤቱ የሪፎርም ቲም አባላት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሄደ።

12/10/2018ዓ.ም

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት የሪፎርም ኮሚቴ አባላት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ በሁሉም የሪፎርም ኮሚቴ አባላት የበጀት ዓመት አፈፃፀማችውን በየዘርፋቸው ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ አስተያየት ተሰጥቶበታል። የግምገማ መድረኩን የመሩት የጽ/ቤቱ ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘነበ ወዬሳ የበጀት ዓመቱ ተግባራት በጥናቀቅ ላይ መሆናቸውን አንስተው ወቅቱ ልክ እንደ ገበሬ የዘራነውን አዝመራ የምንሰበስብበትና ወደ ጎተራ የምንከትበት ስለሆነ የተንጠባጠቡ ስራዎችን እየለቀምን ማጠናቀቅ እንደሚገባ አንስተው የሪፎርም ኮሚቴ አባላት በዝርዝር የተሰጣችሁትን ስራዎች ለመጠናቀቅ የምታደርጉትን ጥረት እያመሰገንን የቀሩ ስራዎችን በአጭር ቀናት ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚገባ የስራ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። የኮሚቴው አባላትም የተሰጣቸውን የስራ አቅጣጫ መቀበላቸውን ገልፀዋል።

የአራተኛ ሩብ ዓመት የወረዳዎች ድጋፍና ክትትል ግብረመልስ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።===============================25/9/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲየአቃቂ ቃሊቲ የስራና ክህሎ...
04/06/2026

የአራተኛ ሩብ ዓመት የወረዳዎች ድጋፍና ክትትል ግብረመልስ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
===============================
25/9/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ
የአቃቂ ቃሊቲ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት በስሩ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የአራተኛ ሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በተገኙ ውጤቶችና መስተካከል ባለባቸው ግብረመልሶች ዙሪያ ከወረዳዎች የዘርፉ ብድን መሪዎችና አስተባባሪዎች ጋር የጋራ መድረክ አካሂዷል። በውይይት መድረኩ የተለዩ ክፍተቶችና በጥንካሬ የሚወሰዱ ግኝቶች ተጠምረው የቀረቡ ሲሆን በመድረኩ አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል። በውይይት መድረኩ የተገኙት የጽ/ቤቱ ም/ኃላፊ አቶ ዘነበ ወዬሳ ይህ ኦዲት መሰል ድጋፍና ክትትል ሁሉም ወረዳ ያለበትን ቁመና በግልፅ ያመላከተ መሆኑን ገልፀው የዓመቱ መጨረሻ ላይ የምንገኝ እንደመሆናችን በክፍተት የታዩ ስራዎች በከፍተኛ ተኩረት በቀናት ውስጥ ተጠናቀው መቀረብ ያለባቸው መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል። በመጨረሻም የዚህ ዓመት አፈጻጸማችን እንደ ከዚህ ቀደሙ ቀዳሚ በመሆን በውጤት እንደሚደመደመ መግባባት ላይ ተደርሷል።

የስራና ክህሎት ጽ/ቤት በ9 ወራት ውስጥ የወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ከ37 ሺ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች የስራ ዕድሎችን መፍጠሩን ገለፀ።ግንቦት 12/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲየአቃ...
20/05/2026

የስራና ክህሎት ጽ/ቤት በ9 ወራት ውስጥ የወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ከ37 ሺ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች የስራ ዕድሎችን መፍጠሩን ገለፀ።

ግንቦት 12/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ክህሎት መር የሆነና ውጤት ተኮር የሥልጠና ሥርዓትን በመዘርጋት ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል የማፍራት ተልዕኮውን በስኬት እየተወጣ ይገኛል።

ጽ/ቤቱ በተለይም የወጣቶችንና የሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥን ዋነኛ ግቡ ያደረገው ይህ ተቋም አምራች ዜጎችን ወደ ሥራ በማስገባት ለሀገር ዕድገት የድርሻውን እያበረከተ ነው።

በ2017 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች አንደኛ በመውጣት ተሸላሚ የነበረው ጽ/ቤቱ በ2018 በጀት ዓመትም ይህንኑ የላቀ ድል ለማስቀጠል የሚያስችሉ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል። የሥራ ዕድል ፈጠራው ከዕለት ጉርስ ባለፈ ቋሚ የሥራ አጥነትን ችግር ለመቅረፍ ያለመ ሲሆን ፣ ክፍለ ከተማው ያሉትን ጸጋዎች በመለየት ለዜጎች ዘላቂና ጊዜያዊ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ውጤታማ የሥራ ስምሪት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በበጀት ዓመቱ በ9 ወራት ውስጥ ለማህበረሰብ በግንዛቤ ፈጠራ ረገድ ሰፊ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን፣ ለ91 ሺህ 772 ነዋሪዎች እንዲሁም በሥራ ባህልና ምርታማነት ዙሪያ ለ71 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተደርጓል። በተጨማሪም ለ45 ሺህ ሥራ ፈላጊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠትና ለ37 ሺህ ሰልጣኞች የክህሎት ሥልጠና በማመቻቸት ለሥራ ዝግጁ እንዲሆኑ ተደርጓል። ይህም ጽሕፈት ቤቱ ከዕቅዱ በላይ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ አስችሎታል።

የሥራ ዕድል ፈጠራንና የኢንተርፕራይዝ አደረጃጀትን በተመለከተ፣ ለ36 ሺህ 995 ዜጎች ሥራ ለመፍጠር ታቅዶ ለ37 ሺህ 090 ሥራ ፈላጊዎች ዕድሉ የተመቻቸ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ 32 በመቶው በመደበኛ ዘርፍ የተፈጠሩ ናቸው። በተመሳሳይ 1 ሺህ 594 ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀትና 43 ሺህ 721 የሥራ ዕድል መፍጠሪያ ጸጋዎችን በማጥናት ለሥራ ፈላጊዎች አዳዲስ አማራጮችን ማሳየት ተችሏል። ይህም ዜጎች የሥራ ፈጣሪነት መንፈስን እንዲያዳብሩ ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሯል።

ኢንተርፕራይዞችን ከማጠናከር አንጻር ለ510 ኢንተርፕራይዞች የ204 ሚሊዮን ብር የብድር አቅርቦት የተመቻቸ ሲሆን፣ 150 የሚሆኑት ደግሞ የመሣሪያ ሊዝ ድጋፍ አግኝተዋል። የቁጠባ ባህልን በማሳደግ በኩልም 1 ሺህ 475 ኢንተርፕራይዞች ከ327 ሚሊዮን ብር በላይ በፍቃደኝነት መቆጠብ የቻሉ ሲሆን፣ 544 ኢንተርፕራይዞች ከጀማሪ ወደ አንስተኛ ደረጃ እንዲሸጋገሩ ተደርጓል። ይህ ስኬታማ ጉዞ 58 ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን በማፍራት ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተሞክሮ ተመዝግቧል።

14/05/2026

!
ከአዲስ ሚዲያ ጋር በመተባበር!
አርብ ረፋድ 4:00 ይጠብቁን።

ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ መሠረታዊ የሕይወት ክህሎት ስልጠና ተጀመረ !፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨  ግንቦት 5/2018 ዓ.ም ለተከታታይ 12 ቀናት የሚቆይ የብቃት የወጣቶች...
13/05/2026

ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ መሠረታዊ የሕይወት ክህሎት ስልጠና ተጀመረ !
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ግንቦት 5/2018 ዓ.ም
ለተከታታይ 12 ቀናት የሚቆይ የብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ መሠረታዊ የሕይወት ክህሎት ስልጠና ዛሬ በአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተጀመረ።

ስልጠናው ወጣቶች በሥራ ቦታ የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለመቋቋም፣ የግንኙነት፣ የቡድን ሥራ፣ የችግር አፈታት እና የውሳኔ አሰጣጥ ክህሎቶችን ለማሳደግ ያለመ እንደሆነ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሬጅስትራል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ጥላሁን ገልፀዋል ።

ፈቃድ ያላቸው በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ስርአጥ ስደተኞች ስራ እድል እንዲፈጠርላቸው ና ባሉ ድርጅቶች በሚመርጡት ዘርፍ የስራ ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ አላማ ያደረገ ስልጠና መሆኑን የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፕሮጀክት አስተባባሪ ኑርሰማ ረሽድ ገልፀዋል ።

ስልጠናው ከሙያ ብቃት ጎን ለጎን የሰዎች ግንኙነት እና የራስን ሕይወት የማቀናጀት አቅምን በማጎልበት ወጣቶችን ለሥራ ገበያ የተሻለ ዝግጅት ለማድረግ ዓላማ ያደረገ እንደሆነ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስልጠና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን ወ/ሮ ፋንታዬ ባብሎ ገልፀዋል ። አያይዘውም አስተሳሰብ ቀይረን እውቀት ለመጨመር ያለመ ስልጠና ስለሆነ ስልጠናው በተገቢው መልኩ እንዲካሔድ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል ።

Address

Akaki Kality Area
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አቃቂ ቃሊቲ የሚሰሩ እጆች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share