02/06/2026
ከባስኬቶ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የተላለፈ የምስጋና መልዕክት፣
ግንቦት 25/2018 ዓ.ም
ውድ የባስኬቶ ዞን ህዝቦች፣ የብልፅግና ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች፤
በ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሂደት ወቅት በከፍተኛ ንቃት፣ ኃላፍነት በተሞላ መንገድ ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁት አስተዋጾ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በህደቱ በንቃት በመሳተፍ እንዲሁም በድምጽ መስጫ ዕለት ከማለዳ እስከ ምሽት በትዕግስት በመጠበቅ ድምጻችሁን በመስጠት ኃላፊነታችሁን የተወጣችሁት ለሀገራችን የዴሞክራሲ ጉዞ ጉልህ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ላደረጋችሁት ሁሉ ከልብ እያመሰገንን
ፓርቲያችን ብልጽግና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህልና በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ፓርቲዎች ተፎካክረው ህዝብ በህጋዊ መንገድ በሚሰጣቸው ድምጽ ብቻ ስልጣን እንድያይዙ ማድረግ አንዱ የዴሞክራሲ ባህል መሆኑን የሚያምን በመሆኑ በምርጫው ከዝግጅት ጊዜ ጀምሮ በዞናችን በምርጫው ላይ ከተወዳደሩ ፓርቲዎች ጋር የጋራ ጉዳዮች ላይ አብሮ ስሰራ ቆይቷል።
በመሆኑም በዞናችን ምርጫው በሠላም እንድጠናቀቅ ላደረጋችሁት አስተዋጾ እያመሰገንን ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ መጠናቀቁ የህዝባችን የዴሞክራሲ ባህል እያደገ መምጣቱን፣ ለሰላም፣ ለልማት እና ለእድገት ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጫ ነው።
በመሆኑም ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠል መስራት እንዳለብን እየገለጽን እስከ አሁን የምርጫው ህደት ያለምን ኮሽታ በሠለማዊ መንገድ እንድጠናቀቅ ላደረጋችሁ የጸጥታ አካላትና መላው ህዝባችን ምስጋና እያቀርብን ቀጣይ በምርጫ ቦርድ በኩል የምገለጸውን ውጤት በመከታተል የኢትዮጵያን ማሸነፍ እናረጋግጣለን ።
የባስኬቶ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት
ግንቦት፣25/2018ዓ.ም
ላስካ