29/05/2025
የአዲስ አበባ ሆቴሎች ዳግም የኮከብ ደረጃ ምዘና ውጤት ይፋ ኾነ
| በቱሪዝም ሚኒስቴር ሲካሄድ የነበረው የ2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሆቴሎች የዳግም የኮከብ ደረጃ ምዘና ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡
በምዘናው የ40 ሆቴሎች ውጤት ይፋ ያደረግ ሲሆን ከባለ 5 ኮከብ ደረጃ እስከ ባለ አንድ ኮከብ ደረጃ ያገኙ ሆቴሎች ደረጃው ተሰጥቷቸዋል፡፡
መግለጫውን የሰጡት የቱሪስት አገልግሎቶች ብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ታሪኩ ደምሴ በንግግራቸው የቱሪዝም ሚንስቴር የቱሪስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ደረጃ የመወሰን እና ተፈፃሚነታቸውን የመከታተል ስልጣን እንዳለው ጠቅሰው ምዘና ከተደረገላቸው ከ40 ሆቴሎች ውጤት ውስጥ 34 ሆቴሎች በዳግም ደረጃ ምዘና የተደረገላቸው ሲሆን 6 ሆቴሎች አዲስ የተመዘኑ ሆቴሎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
አክለውም በመዲናችን የነበሩ የባለ 5 ኮከብ ሆቴሎች በተጨማሪ 3 ሆቴሎች የባላ 5 ኮከብ ደረጃ አግኝተዋል ያሉ ሲሆን አዲስ ከተመዘኑ ሆቴሎች መካከል 2 ተጨማሪ ባለ 4 ኮከብ ሆቴሎች ተቀላቅለዋል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል በዳግም ደረጃ ምዘናው ከነበራቸው ከኮከብ ደረጃቸው የወረዱ ሆቴሎች ቢኖሩም የተወሰኑ ሆቴሎች ደግሞ ከነበራቸው ደረጃ ከፋ ያሉም ይገኙበታል ሲሉ አክለዋል፡፡
የምዘናው ላይ የሚንስቴር መ/ቤቱና ከክልሎች የተወጣጡ የባለሙያ ቡድኖችን በማደራጀት እንዲሁም በሁሉም ዘንድ ታአማኒነት እንዲኖረው በታዛቢነት 6 የሙያና የሆቴል ዘርፍ ማህበራት በሂደቱ እንዲሳተፉ ተደርጓል ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ባለ 5 ኮከብ ደረጃ ያገኙ ሆቴሎች
***
1. ሀያት ሬጄንሲ ሆቴል
2. ስካይ ላይት ሆቴል
3. ሸራተን አዲስ ሆቴል
4. ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል
5. ካፒታል ሆቴል
6. ራዲሰን ብሉ ሆቴል
7. ማሪዮት ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል
8. ጎልደን ቱሊፕ ሆቴል
9. ሂልተን አዲስ ሆቴል
10. ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል
11. ኔክሰስ ኢን ሆቴል