17/10/2025
አደረጃጀቶቻን የተልዕኮ ስኬት ማረጋገጫ ዋልታ ናቸው!
በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም የክንፉ የዘርፍ አመራሮች ፣የህብረትና የቤተሰብ አመራሮች እንዲሁም እንዲሁም አባላት በተገኙበት ገመገመ።
ፓርቲያችን ብልፅግና መመሪያና አሰራርን የዘረጋቸው ተቋማት በማጠናከር፣ የተልዕኮ ስኬታማነት በማረጋገጥ ሁሉም የፓርቲ መዋቅር የለውጡና የተልዕኮ ባለቤት በማድረግ በጥራት ባጠረ ጊዜ ፍትሀዊነት በማረጋገጥ ያስቀመጣቸው ግቦች ያለመሸራረፍ በውጤት እየፈፀመ እንደሚገኝ በመረሀግብሩ ላይ ተገኝተው በመክፈቻ ንግግራቸው የገለፁት በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትልና ፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጆቴ ለዚህ ትልቁ ሚስጥር የተልዕኮውን ባለቤት መዋቅሩና ህብረተሰቡ በማሳተፍና ባለቤት አድርጎ መፈፀም በመቻሉ ነው ብሏል።
በመጀመሪያ ሩብ አመት እንደ ወጣት ክንፍ በርካታ መደበኛ የፓርቲ ተግባራቶች በተደራጀ መልኩ መፈፀሙን የገለፁት በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ወጣት ቤተሌሔም ትዳሩ በዝግጅት ምዕራፍ የነበሩ ጥንካሪዎችን በዝግጅት ምዕራፍ ወቅት አልቀን በመፈፀም ጠንካራ ተቋም የመፍጠር ስራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ አስገንዝቧል።
ተልዕኮ በስኬት ለመፈፀም ተግባርን በውጤት ለማሳካት ግብ ተኮር ስራ በመስራት ተጠናክሮ የቀጠለው የሀገራችን ማንሰራራት ጉዞ ባጠረ ጊዜ ከግብ ለመፈፀም የሚያስችል የሁሉአቀፍ ተነሳሽነትና ዝግጁነት ሊኖር እንደሚገባ በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ዳይሬክተር ወ/ሪት ነጃት ሙስጠፋ ገልጿል።
በመጨረሻም በተነሱት ሀሳም አስተያየቶችና ጥያቄዎች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር ተጠናቋል።