Nifas Silk Lafto Woreda 05 Prosperity Party

Nifas Silk Lafto Woreda 05 Prosperity Party Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Nifas Silk Lafto Woreda 05 Prosperity Party, Political Party, WWW. FIRITCH. COM, Addis Ababa.

ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተን በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። ‎‎ውይይታችን...
12/09/2026

ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተን በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።

‎ውይይታችን በመከላከያ እና ደኅንነት፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኖሎጂ መስኮች ያለንን ትብብር ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጥንበት ነው። እንዲሁም የትምህርት ልምድ ልውውጦችን ማስፋት፣ በባህል እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረናል።

‎በተጨማሪም ለኮፕ 32 በምናደርገው ዝግጅት ያለንን አጋርነት ጨምሮ ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በልማት ግቦች ዙሪያ ትብብሮችን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ተወያይተናል። በወል ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረቱ የንግድ እና የኢኮኖሚ ልውውጦችን ይበልጥ ለማስፋፋትም በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል።

‎🇪🇹 🇷🇺

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት በሚል መሪ ቃል በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ አካል በመሆናችን ኩራት ይሰማናል።‎‎በብሪክስ አባል ...
12/09/2026

ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት በሚል መሪ ቃል በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ አካል በመሆናችን ኩራት ይሰማናል።

‎በብሪክስ አባል ሀገራት ዘንድ ሀብት፣ ቴክኖሎጂ እና ሰፊ ገበያ አለን፤ አሁን ያለው መልካም ዕድል እነዚህን አቅሞች በማስተሳሰር የላቀ እሴት መፍጠር እና ይህ እሴት ደግሞ ሀብቱ በሚገኝበት ቦታ መመረት እንዲችል ማድረግ ነው። ኢትዮጵያ በማዕድን ልማት፣ በታዳሽ ኃይል እና እያደገ በሚገኘው የኢንዱስትሪ መሠረቷ ላይ እነዚህን አጋርነቶች ለመገንባት ዝግጁ ናት።

‎በተጨማሪም በአሠራር ሥርዓቶቻችን ውስጥ ጽናትን መገንባት፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የአህጉራችንን ፍላጎት እንዲያገለግል ማድረግ፣ አስተማማኝ የዕዳ እፎይታ ሒደትን ማሳደግ እንዲሁም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ከኢኮኖሚ ሽግግር ጋር ማስተሳሰር ይኖርብናል።

‎የብሪክስ መድረክ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ጋር ተናኝተን መክረናል።‎‎በሕዳር 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ካደረጉት ታሪካዊ ጉብኝት የተገኘውን መልካም ዕድል ይበ...
12/09/2026

ከብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ጋር ተናኝተን መክረናል።

‎በሕዳር 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ካደረጉት ታሪካዊ ጉብኝት የተገኘውን መልካም ዕድል ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል።

‎ውይይታችን ኢንቨስትመንትን፣ ቱሪዝምን፣ የታዳሽ ኃይል አጋርነትን ማስፋፋት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ያለንን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። በተጨማሪም በማሌዢያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት፣ ምርታማነት እና የአምራች ዘርፍ ተሞክሮዎችን መውሰድ በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረናል።

‎ኢትዮጵያና ማሌዢያ ጠንካራ የኢኮኖሚ አጋርነት ለመመስረት የሚያስችል ከፍተኛ አቅም አላቸው፤ ይህም በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ፣ በክህሎት እና በዘላቂ ልማት ማዕቀፎች አዳዲስ ዕድሎችን የሚፈጥር ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


🇪🇹 🇲🇾

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኒው ዴልሂ ፣ህንድ ገብተዋል። ‎‎በጠ...
12/09/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኒው ዴልሂ ፣ህንድ ገብተዋል።

‎በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን፤ ከጉባኤው ጎን ለጎን ቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ትብብሮችን የሚያጠናክሩ የሁለትዮሽ ውይይቶች ይጠበቃሉ።



11/09/2026
እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ! አደረሰን!ሀሳብን ከተግባር አዋህደን፣ በተጨባጭ ስኬቶች የህዝባችንን ተስፋ አለምልመን 2018ን በውጤታማነት  አጠናቀን  ለላቀ ድል  መስረም 1/20...
11/09/2026

እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ! አደረሰን!

ሀሳብን ከተግባር አዋህደን፣ በተጨባጭ ስኬቶች የህዝባችንን ተስፋ አለምልመን 2018ን በውጤታማነት አጠናቀን ለላቀ ድል መስረም 1/2019ን አንድ ብለን ጀምረናል።

ለቃሉ የታመነው፣ በተግባር የተፈተነው ግዙፉ ፓርቲያችን፣ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለህዝባችን የገባውን ቃል አልቆ መፈፀም የሚጀምርበት ዓመት በመሆኑ፣ በአዲሱ ዓመት አንፀባራቂ ድል ለማስመዝገብ ቁርጠኛ አቋም ይዟል፡፡

በየዘርፉ የተጀማመሩ ትውልድ ተሻጋሪ ሰው ተኮር ተግባራትን አስፍቶ በማስቀጠል፣ የከተማችንን ተምሳሌታዊ ጉዞ ይበልጥ በማጠናከር፣ የተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ እና የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በአዲሱ ዓመት በአሳታፊነትና በአካታችነት መርህ ብርቱ ርብርብ ይደረጋል፡፡

አዲሱ ዓመት አርቆ በማለም፣ አስፍቶ በማቀድ፣ በዳበረ የስራ ባህል ቀን ከሌት በመታተር የብልፅግና ፓርቲን ፕሮግራሞች በተግባር በመተርጎም ለሀገራችን የማንሰራራት ምዕራፍ ትልቅ አቅም የሚፈጠርበት እንደሚሆን እምነታችን የፀና ነው፡፡

በድጋሜ እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ! አደረሰን እያልን፣ ለመላው የከተማችን ነዋሪዎች እንዲሁም የሀገራችን ዜጎች፣ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የስኬት፣ የእድገት የብልፅግና እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞታችንን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የህብረትና ቤተሰብ አባላት የ2019 በጀት ዓመት የፓርቲ ስራዎች ዕቅድ ውይይትና የግብ ስምምነት የፊርማ ስነስርዓ...
10/09/2026

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የህብረትና ቤተሰብ አባላት የ2019 በጀት ዓመት የፓርቲ ስራዎች ዕቅድ ውይይትና የግብ ስምምነት የፊርማ ስነስርዓት ተካሄደ ።

ከሁሉም ማህበራዊ መሰረት የተወጣጡ የህብረትና ቤተሰብ አመራሮችና አባላት የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን በጋራ ለመተግበርና የተቀመጡ ግቦችን በተጨባጭ ውጤት ለመደገፍ የዕቅድ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ የቀጣዩ ዓመት ዋና ዋና የሥራ አቅጣጫዎች፣ የሚጠበቁ ውጤቶች፣ የአፈጻጸም ሂደቶችና በጋራ ትብብር ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮች ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል። ዕቅዱ በተግባር እንዲወርድ የእያንዳንዱን አባል ድርሻና ኃላፊነት በግልጽ ለይቶ መሄድ ላይም ትኩረት ተሰጥቷል።

የዕቅድ ውይይቱ ከብልፅግና ስትራቴጂ መርሆች ጋር በማጣመር፣ ከሀሳብ ወደ ተግባር፣ ከተግባር ወደ ውጤት የሚወስድ የሥራ ባህልን ለማጠናከር ያለመ ነው። በተሳትፎ፣ በትብብር፣ በተጠያቂነትና በውጤታማነት መርሆች በመመራት የተሻለ አፈጻጸም ለማምጣት የጋራ ቁርጠኝነት ተረጋግጧል።

ብልፅግና የሚገነባው በጋራ ራዕይ፣ በተቀናጀ እቅድና በተግባራዊ ቁርጠኝነት ነው። ስለሆነም 2019 በጀት ዓመት የተቀመጡ ዕቅዶችን በትጋት በመፈጸም፣ የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብና የጋራ ብልፅግናን በማረጋገጥ የሚገለጽ የስኬት ዓመት ለማድረግ ዝግጅት ተደርጓል።

በውይይቱም ማጠቃለያ በፓርቲው የስራ ዘርፎች መካከል የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ግብ ስምምነት የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።

ዕቅዳችን በጋራ፣ አፈጻጸማችን በትብብር፣ ውጤታችን ለጋራ ብልፅግና!

የአዲስ ዓመት ዋዜማ የድሮን ትርዒት
10/09/2026

የአዲስ ዓመት ዋዜማ የድሮን ትርዒት

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!ዘመን ከፈጣሪ ለሰው የተሰጠ የመሥሪያ መጽሐፍ ነው። ይህ የመሥሪያ መጽሐፍ ለእያንዳንዱ ሰው የተሰጡ የተወሰኑ ገጾች አሉት። የመጨረሻው ገጽ ተጠና...
10/09/2026

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!

ዘመን ከፈጣሪ ለሰው የተሰጠ የመሥሪያ መጽሐፍ ነው። ይህ የመሥሪያ መጽሐፍ ለእያንዳንዱ ሰው የተሰጡ የተወሰኑ ገጾች አሉት። የመጨረሻው ገጽ ተጠናቅቆ የማጠቃለያው ሽፋን እስኪከደን ድረስ የፈለግነውን የመጻፍ መብት በእጃችን ነው። አንዳንዶች ዓለምን የቀየሩ ሐሳቦችንና ሥራዎችን፤ ሌሎች ታሪክን የቀየሩ ዕሳቤዎችንና ቴክኖሎጂዎችን ጽፈውበታል። በተቃራኒው ዓለምን ያወደሙ፤ ሕዝብ የከፋፈሉና የጨረሱ፤ ተፈጥሮን ያዛቡ፤ ክፋትንና ጭካኔን ያስተማሩ ሐሳቦችንና ተግባራትን የጻፉበትም ጥቂት አይደሉም። ስንፍናንና ድንዛዜን፣ ዕንቅልፍንና ሐኬትን የጻፉም አሉ።

ኢትዮጵያውያን በዚህ የዘመን መጽሐፍ ውስጥ ምን እየጻፍን ነበር? አሁንስ ምን እየጻፍን ነው? ወደፊትስ ምን ለመጻፍ እናስባለን? ከኋላችን ያሰናበትነው አሮጌ ዓመት እና ከፊታችን የምንቀበለው አዲስ ዓመት እነዚህን ጥያቄዎች እንድንመልስ ያስገድዱናል። ዓለምን ያስደነቁ የንግድ፣ የግብርና፣ የሥነ ሕንጻ፣ የዘመን አቆጣጠር፣ የሥነ ከዋክብት፣ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር፣ ሥነ ሥዕልና ሥነ ዜማ፣ ሃይማኖትና ፍልስፍና - በዘመን መጽሐፋችን ውስጥ የጻፍንባቸው የዘመን ገጾች አሉን።
በተቃራኒው ረሃብና ቸነፈር፣ ጦርነትና እልቂት፣ መከፋፈልና መለያየት፣ ማነስና መድከም፣ የጻፍንባቸው የዘመን ገጾችም አሉን።

የትናንቱ ዘመን ጠባሳውንም ዐሻራውንም፣ ዕዳውን ምንዳውንም ሰጥቶን አልፏል። አሁን ወሳኙ ነገር በቀሩን ዘመናት ምን ቁም ነገር እንሰራለን? የሚለው ነው።

ኢትዮጵያውያን ዛሬ ለትውልድ የሚተርፍ አስደናቂ ታሪኮችን እየሰራን ነው። አረንጓዴ ኢኮኖሚን በአረንጓዴ ዐሻራ፤ ቱሪዝምን በገበታ ፕሮጀክቶች፤ የምግብ ሉዓላዊነትን በበጋ ስንዴና በሌማት ትሩፋት፤ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪን በኢትዮጵያ ታምርት እየገነባንና እያጸናን ነው። የኢነርጂ ዐቅማችንን በተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክትና ኑክሌር ቴክኖሎጂ ለማሳደግ፤ የአፈር ማዳበሪያ ግብአቶችን በሀገር ውስጥ ለመሸፈን፤ የአየር መንገድ አድማሳችንን በግዙፉ የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት ለማስፋት፣ ነገን አስበን ዛሬ እየተጋን ነው።

የሕዳሴ ግድብን ፍጻሜ፤ የመስኖ ግድቦችን ፍሬ፤ የሩዝ ምርትን ከፍታ፤ የፍራፍሬ ምርትን ተአምር፤ የወጪ ንግድን ጭማሬ፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያችንን ውጤት፤ በአፍሪካ የፈጠርነውን የኢነርጂ ትሥሥር፤ ዲጂታል 2030ን ስኬት፤ የኮሪደር ልማታችን የኢትዮጵያን ሀብትና ውበት መግለጥ፤ የዘመን መጽሐፋችን እየመዘገበ ነው። የወንዝ ዳርቻ ልማታችን አፈራችንንም፣ ከተማችንንም፣ ጤናችንንም፣ ውኃችንንም እየጠበቀ መሆኑን፤ መድኃኒት የማምረት ደረጃና ዐቅማችም እያደገ መሄዱን፤ የማዕድን ፍለጋችን፣ ምርታችንና ሽያጫችን የዘመናት ስብራትን እየጠገነ መምጣቱን፤ የባሕር በር አጀንዳችን ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ማግኘቱን፤ የኢትዮጵያ የተጽዕኖ አድማስ መስፋቱን - የዚህ ዘመን የመጽሐፉ ገጾች እያሠፈሩ ናቸው።

እነሆ የዘመን መጽሐፋችንን የ2019 አዲስ ምእራፍ የምንጀምረው ሀገራዊ ምክራችንን በስኬት አጠናቅቀን ነው። ይሄንን ምክክር ለዘመናት ኢትዮጵያውያን ይጠይቁት ነበር። ችግራችንን በጦርነት ከመፍታት ይልቅ ለምን አንመካከርም ይሉ ነበር። በየብሔረሰቡ ያለውን የመነጋገርና የመመካከር ባህል ለምን ወደ ፖለቲካው አናመጣውም ይሉ ነበር። የዘመን መጽሐፍ ገጾችን ስናነባቸው ይሄን ጥያቄ ያቀረቡ ወገኖች ብዙ ዋጋ መክፈላቸውን ያስነብቡናል። እኛ ግን ሐሳቡን አመንንበት፤ አምነንም ተቀበልነው፤ ተቀብለንም ተገበርነው። ማመናችንና መተግበራችን ትክክል እንደሆነ የሚያሳዩ ውጤቶችንም ምክክሩ አስገኘልን።

የመጀመሪያው ውጤት “የጠላት ሟርት መክሸፉ” ነው። ኢትዮጵያውያን ሊመካከሩ አይችሉም፤ ቢመካከሩን ወደ ተቀራቢ ሐሳብ አይደርሱም የሚለውን ሟርት አክሽፈነዋል። ለመመካከር እንደምናቅድ፤ አቅደን እንደምንጀምር፤ ጀምረን እንደምንጨርስ በሀገራዊ ምክክር አስመስክረናል። ብዝሃ ሐሳቦቻችን በሀገር ጉዳይ የጋራ አቋም ከመያዝ እንደማያግዱን በተግባር አይተናል።

ሁለተኛው “ባህሉ” ነው። ከፀሐይ በታች ባሉ ጉዳዮች የመወያየት፣ የመነጋገርና የመግባባት ፖቲካዊ ባህልን ማዳበራችን ታላቅ ስኬት ነው። ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የልሂቃን ጉባኤ አድርጋ ይሆናል። ለሕዝቡ “እኛ እናውቅልሃለን” የሚሉ ልሂቃን፥ የሀገርን ችግሮች በመፍታት ስም የሥልጣን ክፍፍል የሚያደርጉባቸው ጉባኤዎች ተካሂደዋል። የዘመናት ጥያቄዎቻችን ግን መፍትሄ አላገኙም። ከልሂቃን ድርድር ይልቅ ሕዝባችን ራሱ መክሮ ራሱ መፍትሔ የሚያመለክትበት ሀገራዊ ምክክር ማድረግ ያስፈለገን በዚህ ምክንያት ነው። በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ በደማቅ ብዕር የሚጻፍ ታላቅ ጉባኤም ተናወነ።

በተካሄደው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሕዝባችንን ዋና ባለቤትና ዋና ተዋናይ በማድረግ ተጠናቅቋል። ሁሉንም አካባቢዎች፤ ሁሉንም ብሔረሰቦች፤ ሁሉንም እምነቶች፤ አብዛኞቹን የፖለቲካ አመለካከቶች፤ ሀገር ቤቱንና ዳያስፖራውን፤ ገበሬውን፣ አርብቶ አደሩንና ወዛደሩን፤ የሥራ ኃላፊዎችንና መደበኛ ዜጎችን፤ የተማሩትንና ያልተማሩትን፤ ወንዶችንና ሴቶችን፤ በዚህ መጠን በአንድ ጉባኤ በአንድ ቦታ ማገናኘት አዲስ ታሪካችን ነው። በዘመን መጽሐፍም በወርቅ ቀለም ተጽፏል።

ሦስተኛው “ውጤቱ” ነው። በአጀንዳዎች ላይ ተግባብተናል። እነዚህ ስምምነት የተደረሰባቸው ጉዳዮች አንድ በአንድ ወደ ተግባር የሚወሰዱ ናቸው። ባህል የሚሆኑ አሉ። ሥርዓት የሚሆኑ አሉ። አሠራር ተደርገው የሚዘረጉ አሉ። ዕሳቤ ሆነው የምንመራባቸው አሉ። ዐዋጅ ሆነው የሚወጡ አሉ። የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ሐሳቦች የሚሆኑ አሉ። የመዋቅር ማሻሻያ የሚሆኑ አሉ። የነገዎችን ትእምርቶች፣ ሐውልቶች፣ ስያሜዎችና ሀገራዊ ብራንዶች የሚወስኑ አሉ። የትናንት ጉዟችንን የሚያርሙ፣ የሚያስታርቁና በተሻለ መግባባት የሚተረጉሙ አሉ።

መንግሥት ሁሉንም ሐሳቦች በተገቢው መንገድ ይጠቀምባቸዋል። የኢትዮጵያን የነገ ጉዞ በሚያቃና መልኩ ግብአት ሆነው ያገለግላሉ። በየጊዜው የሚጠቀሱ፣ የሚወሱና የሚነሡ ዕሳቤዎች ይሆናሉ። የኢትዮጵያ የዘመን መጽሐፍ ከሀገራዊ ምክክሩ በፊትና በኋላ የተለየ ነገር እንደሚጽፍ አምናለሁ። የመግባባት፣ የመስማማትና የመሰናኘት ጉዟችን እየሠመረ መሄዱን ይመዘግባል። የተግባባንባቸው ሐሳቦች መሬት ወርደው፣ ሥር ይዘው፣ ፍሬ ማፍራታቸውን ይተርካል።

ሀገራዊ ምክክራችን ገደ መልካም መሆኑን በምክክሩ ብቻ ሳይሆን በውጤቱም እያሳየ ነው። በአዲስ ዓመት ዋዜማ በመቶ የሚቆጠሩ ታራሚዎችን መንግሥት በምሕረት እንዲፈቱ አድርጓል። ይሄንን ያደረገበት ዓላማ ሁለት ነው። የመጀመሪያው የሀገራዊ ምክክሩን ውጤት በፍቅር፣ በይቅርታና በሰላም ለመጀመር ነው። ወደ ሀገራዊ ምክክር የመጡ ልዩ ልዩ ወገኖች በአንድም በሌላም ስሕተት የታሠሩ ወገኖች በይቅርታ እና በህግ አግባብ እንዲፈቱ ጠይቀው ነበር። መንግሥት ይሄንን ተቀብሎ በሂደቱ የተስማሙትን ፈትቷል። የምክክሩም ዓላማ ኢትዮጵያውያን በጉዳዮች ላይ እንዲነጋገሩ የተግባቡባቸው የመፍትሔ ሐሳቦች እንዲያቀርቡ ነው። መንግሥትም ለምክክሩ ሐሳቦች ትግበራ ያለውን ቁርጠኝነት በዚህ የይቅርታ ሂደት ማሳየት ጀምሯል።

በዚህ የይቅርታ ሂደት የተፈቱ ወገኖች በሀገራዊ ምክክር ምክረ ሐሳቦች ላይ አዎንታዊ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ ይታመናል። ካለፈው መንገድ በመማር የወደፊቱን መንገድ የሰላምና የዴሞክራሲ መንገድ ያደርጉታል ተብሎ ተስፋ ተደርጓል። ማኅበረሰቡም እነዚህ ወገኖች በሀገር ሰላምና ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ማገዝና መምከር አለበት።

መነጋገር፣ መከራከርና መፎካከር ሲቻል ግጭትና ጦርነት አዋጪ አይደለም። የብዕርና የሐሳብ ጊዜ እንጂ የጠመንጃ እና የጉልበት ጊዜ አልፏል። የኢትዮጵያ የዘመን መጽሐፍ ካሁን በኋላ የጠመንጃና የጉልበት ታሪክን አይመዘግብም። በታሪካችን ውስጥ በቂ ግጭቶችና ጦርነቶች መኖራቸውን የዘመን መጽሐፋችን አሳይቶናል። ቀጣዩ ምእራፍ አዳዲስ መንዶችን እንጂ አሮጌ አካሄዶችን አይመዘግብም።

ቀጣዩ ዓመት የጉባ ብሥራቶችን የበለጠ ተግባራዊ የምናደርግበት ዘመን ይሆናል። የፖለቲካ ምኅዳሩ ሰፍቶ የተለያዩ ዕሳቤዎችንና አካሄዶችን በብሔራዊ ጥቅም አስተሣሥረን የምንጓዝበት ዓመት ይሆናል። ሁለንተናዊ ሉዓላዊነታችን ይበልጥ የሚከበርበት፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ይበልጥ የሚጸናበት፣ በሁሉም ዘርፎች የጀመርነው ምርታማነት በዓይነትና በጥራት የሚጨምርበት፣ ሀገራችንም የቀጣናውና የአፍሪካ መሪነቷን ሥር መሠረት የምታስይዝበት፤ የኢትዮጵያ ብልጽግና ትውልድ ተሻጋሪ እንዲሆን ተደርጎ የሚገነባበት ዓመት ይሆናል።

ይህ እንዲሳካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ፣ የልሂቃን ሚና፣ የሃይማኖት አባቶች ጸሎት፣ የጸጥታ ተቋማት ጥንካሬና ቁርጠኝነት፣ የአምራች ኢንዱስትሪው ትጋትና ብርታት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ ቅልጥፍናና ለሕዝብ አሳቢነት፣ የገበሬውና የአርሶ አደሩ አይበገሬነት፣ የወጣቶችና ሴቶች ያላሰለሰ ጥረት፣ የሚዲያዎች ሐቀኝነት፣ የዲጂታል ዘርፉ ዘመናዊነት፣ የሲቪል ሰረቫንቱ ንጽሕናና አገልግሎት፣ እጅግ ወሳኞች ናቸው።

አዲሱ ዓመት በኢትዮጵያ የዘመን መጽሐፍ ላይ አዲስ ታሪክ፣ አዲስ ሐሳብና አዲስ ሥልጣኔ የምንጽፍበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ይህ እንደሚሆንም አምናለሁ። ፈጣሪም እንደሚረዳን እተማመናለሁ።

መልካም አዲስ ዓመት።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጳጉሜን 5፣ 2018 ዓ.ም

10/09/2026

Address

WWW. FIRITCH. COM
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nifas Silk Lafto Woreda 05 Prosperity Party posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share