Yeka Subcity Construction Permit and Control office

Yeka Subcity Construction Permit and Control office በከተማችን በመካሔድ ያለው ግንባታ ሥራዓት ባለው እና ደረጃውን በጠበቀ መንገድ እዲመራ በማድረግ የሕዝብን ጤንነት እና ደህንነት እናረጋግጣለን��

ለሚ ኩራ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ከየካ ክ/ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ለመጡ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ልምድና ተሞክሮ በማካፈል በተለይ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከቅሬታ አፈታት፣ከ...
04/06/2026

ለሚ ኩራ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ከየካ ክ/ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ለመጡ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ልምድና ተሞክሮ በማካፈል በተለይ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከቅሬታ አፈታት፣ከተቋማት ጋር በቅንጅት ከመስራት ፣የከተማ ስታንዳርድ ከማስጠበቅ እና ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም በተለይም በግንባታ ክትትል ቡድን በአዲስ መልክ ቴክኖሎጂን በማልማት አገልግሎትን ከማዘመን አንፃር እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ተሞክሮ በማካፈል በቀጣይ ለተገልጋዩ የሚሰጡ አገልግሎቶች ፈጣን እና የህብረተሰቡን እርካታ ከፍ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ መስራት እንዲቻል አቻ ለአቻ የተሞክሮ ልምድ ልውውጥ ማድረግ ተችሏል።

ለሚ ኩራ ግንባታ ፈቃድና ቀጥጥር ጽ/ቤት
ግንቦት 27/2018ዓ.ም

02/06/2026
ግንቦት 4/ 2018 (ግፈቁባ)በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የአገልግሎት አሰጣጥና የሚሠራቸውን ተግባራት አስመልክቶ ለማስተዋወቅ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት...
12/05/2026

ግንቦት 4/ 2018 (ግፈቁባ)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የአገልግሎት አሰጣጥና የሚሠራቸውን ተግባራት አስመልክቶ ለማስተዋወቅ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመቀናጀት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በየ15 ቀኑ እየተዘጋጀ ከሚቀርቡት ጽሑፎች መካከል አንዱን ዛሬ ‹‹የፕላን ስምምነት ምን ማለት ነው?›› በሚል ርእስ የተዘጋጀውን ጽሑፍ እንድታነቡ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ1124 ተገልጋዮች የፕላን ስምምነት አገልግሎት መሰጠቱ ተገለፀ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን የየካ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፍቃድ...
06/05/2026

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ1124 ተገልጋዮች የፕላን ስምምነት አገልግሎት መሰጠቱ ተገለፀ

ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

የየካ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ፅህፈት ቤት ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፀው በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ዘመናዊ እና ቀልጣፋ አሰራርን በመከተል ለ1124 ተገልጋዮች የፕላን ስምምነት አገልግሎት መስጠቱን ገልጿል።

በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች እንግልትን የሚያስቀሩ ለማድረግ በርካታ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን የገለፀው ፅህፈት ቤቱ አሰራሮችን በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ባለጉዳዮች በቀላሉ የሚስተናገዱበት አሰራር መዘርጋቱ የተገለፀ ሲሆን ለ360 ተገልጋዮች አዲስ የግንባታ ፍቃድ፣ለ62 ተገልጋዮች የግንባታ ማሻሻያ ፍቃድ፣ለ788 ነዋሪዎች የእድሳት የግንባታ ፍቃድ፣ለ332 የግል ግንባታዎች ግንባታ የመጀመሪያ እርከን ማሳወቂያ ፈቃድ አገልግሎት መስጠቱን አክሏል።

በ718 አዲስ እና በ1362 ነባር የግል ግንባታዎች ላይ የክትትል እና ቁጥጥር ስራ ማካሄዱን የገለፀው ተቋሙ 85 ለተጀመሩ ግንባታዎች የማረዘሚያ ፈቃድ መስጠቱን እና በ3674 ህገ ወጥ የሆኑ የውጭ ማስታወቂያዎችን በመለየት የእርምት እርምጃ መውሰዱን አብራርቷል።

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!የትንሣኤ በዓል በክርስቲያኖች ዘንድ ልዩ ቦታ ያለው በዓል ነው። ሞት የተሻረበትና ሕይወት ዋስትና ያገኘበት ነው። ከሞት ባሻገ...
11/04/2026

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

የትንሣኤ በዓል በክርስቲያኖች ዘንድ ልዩ ቦታ ያለው በዓል ነው። ሞት የተሻረበትና ሕይወት ዋስትና ያገኘበት ነው። ከሞት ባሻገር ሕይወት፣ ከመቃብር ባሻገር ትንሣኤ መኖሩ የታወጀበት ነው። ሞት መጨረሻ መቃብር መዳረሻ አለመሆናቸው የተረጋገጠበት ነው። በአዳም ምክንያት ወደ ምድር የወረደው ሰው፣ በክርስቶስ ምክንያት ወደላይ የወጣበት ነው።

የዘንድሮውን ትንሣኤ የምናከብረው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሚያልፍ ፈተና ውስጥ እንዳለች እያሰብን ነው። መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችን ፈታኝ መሆኑን እናውቃለን። ብርሃን እንዳናይ የሚጋርዱ፣ በጥልቁ ጨለማ ጠፍተን እንድንቀር አሥረው ለመያዝ የሚሞክሩ ወጥመዶች ብዙ ናቸው። ወደ ተስፋ ምድር እንዳንሻገር የሚጎትቱ ሰበቦች ሞልተዋል። ዳሩ ግን ከሕማማቱ ወዲያ ትንሣኤ፣ ከዕንቅፋቱ ባሻገር ስኬት እንደሚጠብቀን አምነን እንታገላለን።

በትንሣኤው ዋዜማ - ርግጠኞች፣ ተስፈኞች፣ ተስፋ ቆራጮች፣ ወሬኞች፣ ተስፋ አስቆራጮች፣ ተጠራጣሪዎች ነበሩ። ርግጠኞቹ የሕማማቱ ፈተና እንደሚያልፍ ርግጠኞች ነበሩ። የዕለተ ስቅለት መከራ፣ለዕለተ ትንሣኤ ዋዜማ ለመሆኑ ርግጠኞች ነበሩ። የድንጋዩ በር፣ የበሩ ማኅተም እና የመቃብሩ ጠባቂዎች ትንሣኤውን እንደማያስቀሩት ርግጠኞች ነበሩ። የሚናፈሰው ወሬ እና የሚሠራጨው አሉባልታ እድሜው አጭር መሆኑን ርግጠኞች ነበሩ። ርግጠኞችም ስለሆኑ መሥዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁዎች ነበሩ። እውነቱን ለመመስከር ቆራጦች ነበሩ። በመስቀሉ ሥር ለመገኘት ደፋሮች ነበሩ።

ተስፈኞቹ የርግጠኞቹን ያህል ሳያዩ የሚያምኑ አልነበሩም። ግን አንዳች መልካም ነገር ይጠብቁ ነበር። የተሰጠውን ትምህርት፣ የተደረገውን ተአምራት ሰምተዋል፤ አይተዋል፤ አንዳች ነገርም ጠብቀዋል። ነገር ግን ተገቢውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁዎች አልነበሩም። እውነትን ለመድፈር ቆራጦች አልነበሩም። ሐሰቱን ለመጋፈጥ ዐቅም አላገኙም። ቢያንስ ግን አንደበታቸውን ከክፉ ከልክለዋል።

ተጠራጣሪዎች አጥር ላይ የነበሩ ናቸው። በጥብርያዶስ ይበላሉ፣ በጎልጎታ ይክዳሉ። በሆሳዕና ይዘምራሉ፣ በሊቶስጥራ ይሸሻሉ፡፡ ተአምር ለማየት ይመጣሉ፣መከራ ለማየት ይሳቀቃሉ፡፡ ከደስታው አውጡልኝ፣ ከመከራው ጦመኛ ነኝ የሚሉ ናቸው።

ተስፋ ቆራጮች በሚያዩትና በሚሰሙት ቶሎ የሚወሰዱ ናቸው። በእውነትና በሐሰት፣ በፍርሃትና በጽናት መካከል ያለው ድንበር የጠፋባቸው ናቸው። ሕማማቱ ሲመጣ በቶሎ ወደ ትዝታ ገቡ። ሁሉንም ነገር የትናንት ታሪክ ብቻ አድርገው ወሰዱት። ሁሉንም ነገር “ልጡ የተራሰ፣ መቃብሩ የተማሰ” አድርገው ቆጠሩት። ከግራ ከቀኝ የሚሰሙት አሉባልታ፣ ከፊት ከኋላ የሚመጣው ጫጫታ፤ ከወዲህ ከወዲያ የሚማጣው እሳት፣ ከዚህም ከዚያም የሚያዩት መዓት አስፈራቸው። ነገን አስረሳቸው። በዚህ የተነሣ ተስፋ ቆርጠው ወደ ኋላ ተመለሱ።

ወሬኞች ድሮም ወሬ ስቧቸው የመጡ ናቸው። ምን አለ ምን ተባለ ብለው የተሰባሰቡ ናቸው። የሰሙትንም ያልሰሙትንም፤ የሚያውቁትንም የማያውቁትንም፤ እውነቱንም ሐሰቱንም እያደባለቁ ኢየሩሳሌምን በወሬ ሞሏት። ቢያንስ ከትንሣኤው 15 ዓመት በኋላ ወንጌሉን የጻፈው ማቴዎስ፣ እስከዚያ ዘመን ድረስ ወሬው ብዙ ተቀባይ እንደነበረው ገልጧል።

ተስፋ አስቆራጮች ዓላማቸው ሰውን ሁሉ ከትንሣኤ መንገድ ማራቅ ነበር። እነርሱም አይሄዱ፣ ሰውም አያስኬዱ። ከመጀመሪያው አልተቀበሉትም፤ በኋላም አልፈለጉትም። ብዙ ሰዎች እንደተከተሉት ሲያውቁ ደግሞ ቅናት አቃጠላቸው፤ ክፋት አንገበገባቸው። ክርስቶስን ከሰሱ፤ ራሳቸው ምስክር ሆኑ፤ በመጨረሻም ራሳቸው ፈረዱ። መቃብሩን ዘጉ፤ ጠባቂ አስቀመጡ። በማኅተም አሸጉ። ነገር፣ ያለቀና የተቆረጠ መሰላቸው።

የትንሣኤ በዓል የእነዚህን ሁሉ እውነተኛ ማንነት የገለጠ ነው። ርግጠኞች የቆራጥነታቸው ውጤት በትንሣኤ አገኙ። ተስፈኞች እንዲህ ለሚያልፍ ጊዜ ባለመጽናታቸው አዘኑ። ተስፋ ቆራጮች አሻግሮ ማየት አቅቷቸው ከቦታቸው በመጥፋታቸው ተፀፀቱ። ወሬኞች በትንሣኤው እውነት የተነሣ ያ ሁሉ ወሬ እንደ ናቡከደነፆር ሐውልት ሲፈረካከስ አዩት። ተስፋ አስቆራጮች የገደሉት ክርስቶስ ሲነሣ፣ የዘጉት መቃብር ሲከፈት፣ ያተሙት ማኅተም ሲቀደድ፣ የመደቧቸው ጠባቂዎች ሲሸሹ በዓይናቸው በብረቱ አዩ። ትንሣኤው የሚነገር ሐቅ፣ የሚታይ እውነት ሆነ። ተጠራጣሪዎች ግን አሁንም አጥራቸው ላይ ሆነው ከግራም ከቀኝም ሳይሆኑ ቀሩ።

የኢትዮጵያችንም ነገር እንዲሁ ነው። በኢትዮጵያ ለውጥ ርግጠኞች የሆኑት ዋጋ ይከፍላሉ፤ ርግጠኝነትን ፈርተው ተስፈኞች የሆኑት ቢያንስ አንደበታቸውን ከክፉ ይጠብቃሉ፡፡ ተስፋ ቆራጮች ነገን ማየት ስለሚሳናቸው መንገዳቸውን ይቀይራሉ፡፡ ወሬኞች አውርቶ አዳሪዎች በመሆናቸው የወሬ እንጀራ ይጋግራሉ። ተስፋ አስቆራጮች “ወተቱን አጥቁረው፣ ማሩን አምርረው” የዋሖችን አታለሏቸው፡፡ ተጠራጣሪዎች አንዴ ትኩስ አንዴ ቀዝቃዛ ሲሆኑ፣ ለብ ብለው ቀሩ።

ኢትዮጵያችን ግን ትንሣኤዋን እያየች ነው። መግነዙን ፈትታዋለች፣ መቃብሩን ከፍታዋለች፤ ማኅተሙን ቀዳዋለች። ወሬኞች ከመቃብር ጠባቂዎች ጋር ተማክረው የሚያወሩትን ወሬ የምትሰማበት ጆሮ የላትም። ትንሣኤዋን አይለውጠውምና። እሷ ከዚህ በኋላ የምትጠብቀው ዕርገትን ነው። የምትጓዘው ኃይል እንደሚወርድላት አረጋግጣ ነው። ወደኋላ መመለስ የለም። ሕማማት አልፏል፤ዓርብም አልፏል፤ ቅዳሜም አልፏል። ትንሣኤ መጥቷል። በትንሣኤ ሌሊት የተኙ አልሰሙ ይሆናል። በተስፋ አስቆራጮች ተታለው የሄዱ ዜናው አልደረሳቸው ይሆናል። ትንሣኤ ግን እውን ሆኗል።

ከቻላችሁ አጥር ላይ ያላችሁ ውረዱ። ተስፈኞች ርግጠኞች ሁኑ። ተጠራጣሪዎች እመኑ። ወሬኞች ከአፍ ወደ መዳፍ ተለወጡ። ምክንያቱም - ኢትዮጵያ ወደ ትንሣኤ ተቃርባለች።

የኢትዮጵያ ትንሣኤ ከሚበሰርባቸው ምዕራፎች አንዱ ግንቦት ላይ የሚካሄደው ምርጫ ነው። ትንሣኤን ያለ ሕማማት እንደማናስበው ሁሉ ዴሞክራሲንም ከውጣ ውረድ ነጥሎ ማየት አይቻልም። በዓለም ላይ በደልዳላ መንገድ ተጉዞ ዴሞክራሲን የገነባ ሀገር የለም። ዴሞክራሲና ብልጽግና ያለ ጽናት አይሳኩም። ከእኛ በፊት ዐመጻውን በትዕግሥት የመከቱ ተሻግረዋል፤ ሑካታውን በጽናት ያለፉ አሳክተዋል። ብንመኝም ፈተናውን አናስቀርም፤ መጽናት ግን እንችላለን። ከድህነት መውጫው ብርታታችን፣ ወደ ዴሞክራሲ መድረሻችው ትዕግሥታችን እንደሆነ አምነን ለኢትዮጵያ ትንሣኤ በሙሉ ልባችን እንትጋ!!

በድጋሚ መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንልን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሚያዝያ 03 ቀን 2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የበላይ አመራሮች በየካ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ያለውን የአግልግሎት አሰጣጥ አስመልክቶ ክትትልና ድጋፍ...
22/03/2026

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የበላይ አመራሮች በየካ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ያለውን የአግልግሎት አሰጣጥ አስመልክቶ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ግብረ መልስ ሰጡ፡፡
መጋቢት 12/2018 ዓ.ም (ግፈቁባ)

የከተማው ምክር ቤት እና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሰጡትን ግብረ መልሶች ተመርኩዞ እንዲሁም ባለሥልጣን መ/ቤቱ ራሱ በምስለ ተገልጋይ ያገኛቸውን ግኝቶች መነሻ በማድረግ የበላይ አመራሮች በየካ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ያለውን የአግልግሎት አሰጣጥ አስመልክቶ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ግብረ መልስ ሰጥተዋል፡፡
የየካ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤቱ በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት 9 ወራት ታቅደው የተከናወኑ የተግባራት አፈጻጸም በሠነድና በመስክ ጉብኝት በማረጋገጥ ለበላይ አመራሩ አሳይቷል፡፡ በዋናነት ከተሰጡት ግብረ-መልሶች መካከል ከኅብረተሰቡ የሚቀርቡ አስተያየቶችንና ቅሬታዎችን ከወዲሁ እያዩ ቶሎ ብሎ መፍታት እንደሚገባ፣ ሕገ-ወጥ ግንባታና ማስታወቂያዎች ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መሥራት እንደሚያስፈልግ፣መረጃዎችን በአግባቡ በመያዝና ባለሙያዎችም በትክክል መረጃዎችን መሠረት አድርገው እየሠሩበት ያለውን ሁኔታ አጠናክረው እንዲቀጥሉበት የሚሉት ይገኙበታል፡፡
በአጠቃላይ በጥሩ ጎን የታዩትን ይበልጥ አጠናክሮ በማስቀጠል በድክመት የታዩ ጉዳዮችን ደግሞ በፍጥነት አስተካክሎ ማስቀጠል እንደሚገባ የበላይ አመራሩ መመርያና አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡

22/03/2026

አገልግሎት አሰጣጥ በተገልጋዩ ዕይታ...

12/03/2026

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎቹን የአገልግሎት ጥያቄዎች በውጤታማነት ለመመለስና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተገልጋዮች ገለፁ።

https://www.facebook.com/share/v/1K9WbnZaMK/

Address

Yeka Subcity
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeka Subcity Construction Permit and Control office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share