02/03/2026
ከዓድዋ የነፃነት ፋና ወደ ህዳሴው የብርሃን ሉዓላዊነት
ጀግኖች አባቶቻችን በዓድዋ አውድማ ለሀገራዊ ክብርና ለሉዓላዊነት ተዋድቀው ያቀበሉንን የነፃነት ፋና፣ የዛሬው ትውልድ በጉልበቱ፣ በእውቀቱና በሀብቱ ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ድል እየቀየረው ይገኛል።
ከጀግንነት ወደ ብልጽግና የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ቁሳዊ ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ የኢነርጂ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ትልቅ ፖለቲካዊና ታሪካዊ ድል ነው።
ዓድዋ የነፃነታችን መሰረት እንደሆነ ሁሉ፣ የህዳሴው ግድብ ደግሞ የድህነት ቀንበሩን የምንሰብርበት የብልጽግናችን ማማ ሆኗል።
"ህዳሴ ግድባችን በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን!" በሚለው መሪ ቃል ስር፣ ፕሮጀክቱ ያለ ውጭ እርዳታ በዜጎች ጥረትና ቁርጠኝነት የተገነባ መሆኑ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ትልቅ መልዕክት ያስተላለፈ የቀደመው ትውልድ በጦር ሜዳ የሀገርን ዳር ድንበር አስከብሮ እንዳስረከበን ሁሉ፣ የአሁኑ ትውልድም በልማት ግንባር ተሰልፎ የኢኮኖሚ ነፃነትን እያወጀ ይገኛል።
"ትላንት በዓድዋ አውድማ በደማችን ነፃነታችንን አስከበርን፤ ዛሬ ደግሞ በአባይ ወንዝ ላይ በእውቀታችንና በሀብታችን ብርሃንን ዘራን።"
ይህ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስኬት ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የኢነርጂ ማዕከል እንድትሆን ከማስቻሉም ባለፈ፣ ለቀጣዩ ትውልድ "የማይቻል ነገር የለም" የሚል የድል ስነ-ልቦናን አውርሷል። ከድል ወደ ልማት፣ ከጀግንነት ወደ ብልጽግና የሚደረገው ጉዞም በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ተመልክቷል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ