05/06/2026
የሶዶ ከተማ ፖሊስ መምርያ ከኢ/ር ወደ ዋ/ኢ/ር ማዕረግ ዕድገት ያገኙ ከፍተኛ መኮንኖችን አቀባበል አደረገ።
ሶዶ፣ ግንቦት 28/2018 ዓ.ም
ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምርያ ከኢ/ር ወደ ዋና ኢንስፔክተርነት ማዕረግ ሽግግር ላደረጉ መኮንኖች የ3ቱ ክ/ከተማ ፖሊስ አዛዦችና አመራሮች በተገኙበት ደማቅ አቀባበል አደረገ።
በመርሃ ግብር ላይ የተገኙት የከተማ ፖሊስ መምርያ አዛዥ
ኮ/ር ሀብታሙ አሰፋ እንደገለጹት ከኢ/ር ወደ ዋና ኢንስፔክተር ማዕረግ ዕድገት ላገኙ አባላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋል።
አዛዡ አያይዘውም የፖሊስ ተቋሙ ህዝብና መንግስት የተጣለበትን አደራ በመወጣት የከተማውን ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ደረጃ ማድረሱን ገልፀዋል።
ሰላም ለሁሉ መሠረት መሆኑን የጠቆሙት የፀጥታ መዋቅር የተደራጀና የተጠናከረ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
አመራሮች የሙያ ስነምግባራቸውን በመላበስ ሀገራዊ ኃላፊነት በተገቢው እንዲወጡም አመላክተዋል።
በአገልግሎታቸው የተሻሉና መስፈርቱን ያሟሉ 2 የፖሊስ አመራር ከኢ/ር ወደ
ዋ/ኢንስፔክተርነት ማደጋቸውን ገልጸዋል።
የሚጠብቁን ግዳጆችን በብቃት ለመወጣት የሙያ ስነምግባር በመላበስ በቁርጠኝነት መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በመጨረሻም የማዕረግ ዕድገት ያገኙ መኮንኖች፣ የተቋሙ አመራርና አባላት በጋራ የሻይ ቡና ፕሮግራም በማድረግ ተጠናቅቋል።
በጀግንነት መጠበቅ በሰባዓዊነት መጋልገል///