የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ -All Ethiopia Unity Party

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ -All Ethiopia Unity Party

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ -All Ethiopia Unity Party Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ -All Ethiopia Unity Party, Political Party, Addis Ababa.

 ፦*****************************************************የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ላለፉት 35 ዓመታት ሰላማዊ ትግሉን በፅናት ሲያስቀጥል ከ...
04/07/2026


*****************************************************

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ላለፉት 35 ዓመታት ሰላማዊ ትግሉን በፅናት ሲያስቀጥል ከሚታገልላቸው ፖሊሲዎች መካከል ፌደራሊዝም አወቃቀሩና የሥርዓተ መንግሥት አወቃቀሩ ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ።
ለምሳሌ፥ ኢትዮጵያ ሕዳር 1987 ዓ.ም የመንግስት ሰነድ ሆኖ የፀደቀው ባለ ሰማያዊ ቀለም ሕገ-መንግስት ተብዬው ገና ከፅንሰቱ 1968 ምናምን አካባቢ ከደደቢት የአንድ ድርጅት የመታገያ ፕሮግራም ሆኖ በህወሓት የተቀረፀ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ እንደነበርና በታሪክ አጋጣሚ ድንገት ሳያስቡት ኢትዮጵያን የምታክል ግዙፍ ሀገር እጃቸው ላይ በ1983 ዓ.ም ስትወድቅባቸው "ከመጣሽ ማርያም ታምጣሽ" ብለው ተቀበሏትና በዞባና በወረዳ የማስተዳደር እሳቤ ቀጥለው አገዛዛቸውን ሲያፀኑ እንደወግ የማስተዳደሪያ ሰነድ ያስፈልጋልና ያንኑ የጫካ ሰነዳቸውን የተወሰኑ የዓለምአቀፍ ድንጋጌዎችን ጨማመሩበትና የሀገር መምሪያ ሰነድ አድርገውት ሀገርን ያተራምሱበት ያዙ። ሰነዱም ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝም አድርገውት ላለፉት 40 የተጠጉ ዓመታትን እየተተራመስንበት እንገኛለን። መኢአድ ታዲያ ሀገር በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በብዙ ቋንቋና ባህል ስብጥሮሽ የበለፀጉ እና በቆዳ ስፋቱና በመልካ ምድራዊ አቀማመጥ የሰፉ ሀገራት ለአስተዳደር አመቺነቱ የፌዴራሊዝም አወቃቀር ተመራጭ ነው ብለን እናምናለን። ስለሆነም ላለፉት 35 ዓመታት የጂኦግራፊ (መልካ ምድራዊ አቀማመጥ) እና የባሕልና ኢኮኖሚ ትሥሥርን መሠረት ያደረገ የፌዴራሊዝም አወቃቀርን መሠረት አድርገን እየታገልን ብዙ ዋጋ ከፍለንበታል። በዚሁ መሠረትም የፓርቲያችን የአመራር መዋቅር እንኳን በ5ቱ የፌዴራሊዝም አወቃቀራችንን ለመምራት በሚያመቸን ሁኔታ፦
1. ሰሜን ኢትዮጵያ ቀጠና
2. ደቡብ ኢትዮጵያ ቀጠና
3. ምሥራቅ ኢትዮጵያ ቀጠና
4. ምዕራብ ኢትዮጵያ ቀጠና እና
5. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ቀጠና በሚል አወቃቀር እያንዳንዱ የቀጠና ኃላፊም በም/ፕሬዚደንት ማዕረግ የማዕከላዊ ሥራ አስፈፃሚ አባል በመሆን አሁን ያለው አወቃቀር እስኪቀየር ድረስ ያለፉት 9 መደበኛ ጉባዔያት ይሄንንኑ መዋቅር አስቀጥለው ነበር። "ነበር" የምልበት ምክንያት አሁን ያለው አመራር የተመረጠው በ10ኛው መደበኛ ጉባዔ የተመረጠ ሲሆን መዋቅሩም በምርጫ ቦርድ አስገዳጅ መመሪያ "የቀጠና መዋቅርን ተቀብዬ ለጉባዔው እውቅና ሰጥቼ ጉባዔውን አላፀድቅም" ስላለን የማዕከላዊ ኮሚቴ/ሥራ አስፈፃሚ/ መዋቅራችንንም ቁጥሩን ከ21 ወደ 13 እንድናወርደው ተገድደናል። ይሄ ሊሆን የቻለበት ብዬ በግሌ የምጠረጥረው እንዲሁ ከሰዎች ጋር ሳወራም ወደ እርገጠኛነት ያደረሰኝ ምርጫ ቦርድ አጀንዳችንን የማስነጠቅ ሴራ እንዳሴረብን እጠረጥራለሁ ጉባኤ ባደረግንበት አካባቢ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ አጀንዳ ፍለጋ በየመንግስት ተቋማቱ የሚያንጎዳጉድበት ወቅት ስለነበር በሰዓቱ ብልፅግና በመከላከያ ተቋም አማካኝነት የኛን የ5 ቀጠና አወቃቀር አጀንዳ አስይዟል የሚል ወሬ በከፍተኛ ደረጃ የሚናፈስወት ጊዜ ነበር። በዚህ ምክንያት የተቀማን ይመስለኛል።
ፕሮግራም ቀርፀን የምንታገልባቸው አጀንዳዎች መካከል፤
1. የፌዴራሊዝም አወቃቀር ጂዮግራፊካል/መልካምድራዊ/ አቀማመጥን መሠረት ያደረገና
2.መንግስታዊ አወቃቀራችን ደግሞ ፕሬዚዳንታዊ እንደሚሆን በ1995 ዓ.ም የታተመችው ባለ ብርቱካናማ ቀለም ሽፋን ያላት ቋሚ ፕሮግራማችን ላይ በግልፅ ተቀምጧል። ይህ ብቻ አይደለም ሌሎችም ብዙ ብልፅግና የሰረቃቸው አጀንዳዎችን አጭቃ ይዛለች ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።
ወደ ቀደመ ነገሬ ስመለስ ምንም እንኳን ፕሮግራማችን አሸናፊ መሆኑ ደስ ቢያሰኘኝም ሁሉም ነገር ያለ ጊዜው ፣ ያለቦታውና ያለባለቤቱ ሲሆን ትክክል አይመጣም። ፕሮግራሙን እንዴትና በማን ተግባራዊ ልናደርገው እየታሰበ እንደሆነ ታሳቢ መሆን ይገባዋል። ለምሳሌ ማን ነበር የሆነን ሰው "ክትፎ በፖፖ" በሚል አገላለፅ የገለፀው?(የግለሰቦቹን ስም መጥቀስ ስለሌለብኝ ነው) እንደ ግለሰቡ አገላለፅ ክትፎ ተወዳጅ ምግቡ ነው። ነገር ግን የቀረበለት አቀራረብ ክትፎነቱን አስቀይሮ ቆሻሻ አድርጎታል። እንደ ግለሰቡ አገላለፅ ክትፎ ክትፎ የሚሆነው በጣባ ሲቀርብ ነው። እናም ዛሬ ላይ የተያዘው አጀንዳ ወቅቱ እና አስፈፃሚ አካላቱና ተመካካሪዎቹስ እነማን ናቸው? እውነቱን እንነጋገር ከተባለስ እውን ይሄንን አጀንዳ ብልፅግና ከልብ በራሱ ተነሳሽነት ይሁነኝ ብሎ አቀረበው ወይ? ከሆነስ የዛሬ 7 ዓመት አካባቢ ወደስልጣን በመጣ ማግስት የጫጉላ ሽርሽር ላይ እያለ ገና ያኔ ስሙን ከኢህአዴግ ወደ ብልፅግና የቀየረበት የስም ማውጫ ዳቦ ሳይቆረስ ከብረውት የነበሩ ስለ ሕዝቤ ያገባኛል ሕዝቤ ጠይቆ ሳይመለስ የሚቀር ምንም አይነት ጥያቄ አይኖርም ብለው ለህዝባቸው ቃል ቢገቡ ከብልፅግናው ቁንጮ መሪ ለአንድ ክልል ተብሎ የሚነካካ ህገመንግስት የለም ብለው ጥያቄውን የቁጣ ምላሽ ለምን ሰጡት? ግዴለም ነገርዮውን ከጀርባ በኩል እንመርምረው? እኔ በግሌ ፓርቲዬም ነሚያምንበት አጀንዳዎቹ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ጠመም አድርገው ተረድተዋቸው አጣምመው በአጀንዳነው ቢያቀርቡትም አጀንዳችን አሸናፊ ሆኖ መምጣቱ ያን ሁሉ መሰዋዕትነት ለከፈልንለት ለሕዝብ ይጠቅማል ብለን ለማስፈፀም ስለሆነ አሸናፊነቱ ደስታን ይሰጠናል። ነገር ግን አጀንዳው አጀንዳችን ስለሆነ ብቻ ያለጊዜውና ያለቦታው እንዲሁም አስፈላጊነቱን በቅጡ ባልተረዱ አካላት ለመፍታት መውተርተር የመፍትሄ ውሉን አጥፍቶት እንዳያውሰበስበው ከፍተኛ ስጋት አለኝ (አለንም) ስንዴና አረምን መለየት ግዴታ እንደሆነ ቢታወቅም ስንዴና አረሙን የምንለየው ግን ስንዴውን ነቅለን አረሙን በመተው አይደለም ስንዴውን ተንከባክበን አረሙን በመንቀል እንጂ። እናም የተሰረቀ አጀንዳ ልክ እንደ አጀንዳ ፈጣሪው በትክክል ተረድቶት ሰራቂው ለሌላ ወገን በሚገባ ሊገልፀው ስለማይችል አጀንዳውን ለአጀንደ ፈጣሪው በአክብሮት መልሱለትና በተመቻቸ ጠረጴዛ ላይ ቀርቦ አግባብነት ባለው ተወያይና ውይይት ለውጤት እናብቃው እላለሁ።
በቀሪና ከፕሮግራማችን ላይ በተሰረቁ አጀንዳዎች እመለሳለሁ።
ቸር ይግጠመን!!

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት እውነተኛ የፖለቲካ ድርድር እንዲካሔድ ጠየቀለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአራት የፖለቲካ ፓርቲዎች የተመሰረተው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ሀገርን አፅንቶ ለማስቀጠል እ...
28/06/2026

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት እውነተኛ የፖለቲካ ድርድር እንዲካሔድ ጠየቀ

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአራት የፖለቲካ ፓርቲዎች የተመሰረተው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ሀገርን አፅንቶ ለማስቀጠል እውነተኛ የፖለቲካ ድርድር እንዲካሄድ ጠይቋል።

የፓርቲዎቹ ስብስብ መንግሥት ወደ እውነተኛ ድርድር እስከሚመጣ ድረስ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።

በሀገር ብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ የማይደራደር አቋም እንዳለውም ይፋ አድርጓል።

የትብብሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌትነት ወርቁ ከአሐዱ መድረክ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ መንግሥት ምርጫ አሸንፌያለሁ በሚል ባለፉት ዓመታት ይከተለው በነበረው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ሀገርን አደጋ ላይ ይጥላል ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል።

ትብብሩ ምርጫው ይደገም የሚል አቋም እንደሌለውም ኃላፊው አብራርተዋል።

"ለተፈጠሩ ችግሮች እልባት ለመስጠት የድርድር ሂደቱን መጀመር ለነገ የማይባል ተግባር ነው" ያሉት አቶ ጌትነት የዲሞክራሲ ሥርዓት ባልዳበረባት ኢትዮጵያ የተፈጠሩ ችግሮች በአንድ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ይፈታሉ የሚል እምነት እንደሌላቸው ጠቁመዋል።

ትብብሩ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምላሽ እስከሚያገኙ ድረስ ከሥርዓቱ ጋር የሚያደርገውን ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቋሙን በድጋሚ አስታውቋል።

#አሐዱ

4አመት የፈጀው የኦህዴድ ብልፅግና 8ቱ አጀንዳ እና አዲስ ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት ዝርጋታ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""...
26/06/2026

4አመት የፈጀው የኦህዴድ ብልፅግና 8ቱ አጀንዳ እና አዲስ ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት ዝርጋታ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚባለው የውሸት ተቋም ላለፉት አራት ዓመታት በአገር አቀፍ ደረጃ አጀንዳዎችን ሲያሰባስብ መቆየቱና በቅርቡ ይፋ አደረግኳቸው ባላቸው ነጥቦች ላይ በብዙኃኑ ዘንድ ከፍተኛ ትችትና ጥያቄ እየቀሰቀሱ ይገኛሉ።

በተለይም በአገሪቱ ውስጥ ''ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት'' ለመዘርጋት የታለመ ይመስላል የተባለው አካሄድ እና ለዓመታት የተለፋበት አጀንዳ በጥቂት መስመሮች ሊጠቃለል የሚችል መሆኑ የምክክሩን አስፈላጊነትና ተዓማኒነት ያጋለጠ ሆኗል ።

❇️ በ4 መንገድ ከፍለን ማየት እንችላለን.......

1.የጊዜ እና የሀብት ብክነት፡ አራት ዓመት ለምን?
አንድን አገር ከፖለቲካዊና ማኅበራዊ ቀውስ ለመታደግ የሚቋቋም የምክክር ኮሚሽን ዋናው መሣሪያው ጊዜ ነው። ሆኖም ኮሚሽኑ አጀንዳ ለማሰባሰብ ብቻ አራት ዓመታትን መፍጀቱ የሂደቱን ስንፍና እና ውጤታማ አለመሆን በግልጽ ያሳያል።

፩. የሕዝብ ተስፋ መሟጠጥ፦ አገሪቱ በከፍተኛ የጸጥታ፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ባለችበት ወቅት መፍትሔ ያመጣል የተባለ ተቋም ለአራት ዓመታት ማውጠንጠኑ በሕዝቡ ዘንድ የነበረውን ተስፋ ወደ መቆረጥና ግዴለሽነት ቀይሮታል።

፪. የሀብት መባከን፦ በከፍተኛ የውጭና የአገር ውስጥ በጀት የሚንቀሳቀስ ተቋም ይህንን ሁሉ ጊዜ ወስዶ ያመጣው ውጤት ዜሮ መሆኑ የሕዝብና የአገር ሀብት ያላግባብ መባከኑን ያሳያል።

፫. ዋናው ስህተት፦ አራት ዓመት የፈጀው ሂደት ያመጣው አጀንዳ ማንኛውም የአገሪቱን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተል ምሁር ወይም ተራ ዜጋ በ4 ቀናት ውስጥ (እንኳን 4 ቀን 4 ሰዓት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ) በ8 መስመር ሊያጠቃልለው የሚችለው የታወቀና የተለመደ የአገሪቱ ችግር መሆኑ ነው።

2. ''የፕሬዝዳንታዊ መሪ'' ፍላጎት እና የታዘዘ አጀንዳ ጥርጣሬ:- በምክክር ሂደቱ ውስጥ ጎልቶ እየታየ ያለውና ትልቁን ትችት ያስከተለው ጉዳይ፣ ኢትዮጵያ ወደ "ፕሬዝዳንታዊ የሥርዓተ መንግሥት አወቃቀር" እንድትሻገር መንገድ የሚጠርግ አጀንዳ ይዞ መቅረቡ ነው። ይህ አካሄድ ኮሚሽኑን ካቋቋመው ገዥ አካል ፍላጎት ጋር የተቆራኘ እንደሆነ በግልፅ ያሳያል ።

፩. የሕዝብ ፍላጎት ወይስ የፖለቲካ ፍላጎት? ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት የዜጎች ቀዳሚ ጥያቄ የዕለት ተዕለት ሰላም፣ የሕግ የበላይነት፣ የኢኮኖሚ መረጋጋት እና የሰብዓዊ መብቶች መከበር እንጂ የሥርዓተ መንግሥት ለውጥ (ከፓርላማዊ ወደ ፕሬዝዳንታዊ) አይደለም።

፪. የአምባገነንነት ሥጋት፦ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ጠንካራ ተቋማት በሌሉበት መዋቅር ውስጥ "ሥልጣንን በአንድ ፕሬዝዳንት እጅ ላይ ማከማቸት" አገሪቱን ወደ ፍጹም አምባገነንነት ሊመራት እንደሚችል ታሪክና የጎረቤት አገራት ተሞክሮ ያሳያል። "ኮሚሽኑ ይህንን የመሰለ ስስ አጀንዳ ይዞ መምጣቱ ገለልተኝነቱን ሙሉ በሙሉ ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል።

3. የይዘት ጥልቀት ማጣት፡ 8 መስመር የማይሞላ አጀንዳ ኮሚሽኑ ''አገር አቀፍ አጀንዳ'' ብሎ ያቀረባቸው ነጥቦች ለአራት ዓመታት የተደረገ ጥናትና የምክክር ውጤት ለመሆናቸው ምንም ዓይነት ማረጋገጫ የማይሰጡ ጥልቀት የሌላቸውና ላይ ላዩን የተቀነጨቡ ናቸው።

✍️የሚጠበቅ የነበረው ውጤት:-
▪️የችግሮቹን ስር የሰደደ ምክንያት (Root Causes) የያዘ ዝርዝር ሰነድ
▪️ሁሉንም ወገኖች ያካተተና ስምምነት የተደረሰበት ፍኖተ ካርታ
▪️ለአገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ተጨባጭ መፍትሔ አመልካች ነጥቦች

✍️ በተግባር የቀረበው ውጤት:-
▪️የፖለቲካ ኃይሎችና ታጣቂዎች ባልተሳተፉበት የተሰበሰበ አጀንዳ
▪️በጥቂት መስመሮች የተጠቃለሉ አጠቃላይ መፈክሮች
▪️ነባር ውዝግቦችን መልሶ የሚያባብስ አወዛጋቢ ሀሳብ

⚠️ ይህ የይዘት ጉድለት የሚያሳየው ኮሚሽኑ ወይ የሕዝቡን እውነተኛ ብሶትና ፍላጎት ለማዳመጥ ፈቃደኛ አለመሆኑን ወይም ደግሞ አስቀድሞ የተዘጋጀለትን አጀንዳ ለማጽደቅ ሕዝባዊ መድረኮችን እንደ ሽፋን መጠቀም መምረጡን ነው።

4. መሠረታዊ ስህተቶችና ማጠቃለያ:-
በአጠቃላይ ይህ ''የምክክር ኮሚሽን አጀንዳ አሰባሰብ'' ሂደት የሚከተሉትን ትላልቅ ስህተቶች ፈጽሟል፦

፩. አካታችነት ማጣት፦ ዋና ዋና የፖለቲካ ተዋናዮች "የታጠቁ ኃይሎችና የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች በሌሉበትና በስደት ወይም በእስር ላይ ባሉበት" ሁኔታ የተሰበሰበ አጀንዳ አገራዊ መግባባት ሊፈጥር አይችልም።

፪. ቅደም-ተከተል አለማወቅ (Misplaced Priorities)፦ አገር በጦርነትና በደኅንነት እጦት እየታመሰች ባለችበት ወቅት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ የሰላም ጥሪዎችን ትቶ ስለ መዋቅራዊ ለውጥና ስለ "ፕሬዝዳንታዊ መሪ" ማውራት ፈረስን ከሠረገላ ፊት እንደማስቀደም ይቆጠራል።

፫. የእውነተኛ ውይይት መድረክ አለመሆን፦ ሂደቱ ከታችኛው ማኅበረሰብ ፍላጎት የተነሳ ሳይሆን ከላይ ወደ ታች (Top-down) የተጫነና አስቀድሞ የተሰመረለትን መስመር ተከትሎ የሄደ በመሆኑ ስሙ ''ብሔራዊ ምክክር'' ይባላል እንጂ በተግባር ግን ''የአንድ ወገን አጀንዳ ማሳጠሪያ'' ሆኖ አልፏል።

ስለሆነም አራት ዓመት ፈጅቶ የመጣው ይህ ባለ 8 መስመር አጀንዳ፣ የኢትዮጵያን ዘላቂ ችግሮች ከመፍታት ይልቅ አዳዲስ የፖለቲካ ውዝግቦችንና ጥርጣሬዎችን የሚወልድ የታለመለት የሕዝብ ትስስርና እርቅ ላይ የራሱን አሉታዊ ጥላ ያረፈበት ውድቅ ሊደረግ የሚገባው ሰነድ ነው ማለት ይቻላል።

እርሰዎስ ይህን የምክክር ኮሚሽኑን አጀንዳ እንደት አዩት ? ሀሳብዎን ቢያካፍሉን ።

ሐሙስ ሰኔ 18 ጠዋት 3:00-5:00 የትብብሩ አመራሮች በአሐዱ ሬዲዮ፣ አሐዱ መድረክ ቀርበው ማብራሪያ ይሰጣሉ። ይከታተሉ፣ ይሳተፉትብብር ለኢትዮጵያ አንድት- Coalition for Eth. ...
24/06/2026

ሐሙስ ሰኔ 18 ጠዋት 3:00-5:00 የትብብሩ አመራሮች በአሐዱ ሬዲዮ፣ አሐዱ መድረክ ቀርበው ማብራሪያ ይሰጣሉ። ይከታተሉ፣ ይሳተፉ
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድት- Coalition for Eth. Unity

22/06/2026

የሕዝብ ድምፅ ማንኛውም የፖለቲካ ኃይል ወይም ባለሥልጣን እንደፈለገ የሚያድለው ሀብት ሳይሆን የዜጎች ነፃ ፈቃድ መግለጫ ነው ። ስለዚህ የሕዝብን ድምፅ በፖለቲካ ስምምነት ወይም በሌላ መንገድ ለተላላኪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማደል ከእውነታም ሆነ ከዲሞክራሲ መርሆች ጋር የማይጣጣም ነው። የምርጫ ውጤት ሊመሠረት የሚገባው በሕዝብ እውነተኛ ውሳኔ ላይ እንጂ በጓዳ ፖለቲካዊ ድርድር ወይም በበጎ ፈቃድ በሚሰጥ ድልድል ላይ የተመሠረተ አይደለም ።

21/06/2026

የአንባ ገነን መንግስታት ትልቁ መሳሪያቸው ሕዝብ ላይ ፍርሀትን ማንገስ ነው ።
ፈርተህም ሞት ፣ ስደት ፣ እርሃብ እና መፈናቀል ስለማይቀርልህ ተደራጅና ለነጻነትህ ታገል
!!

የትብብር ጥሪ ለመላው ኢትዬጵያውያን ወዳጆቻችንና ደጋፊዎቻችን በሙሉ----------የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) በገዥዎች ለሚንገላቱ እና ግፍ ለሚፈፀምባቸው መላው ኢትዮጵያ...
20/06/2026

የትብብር ጥሪ
ለመላው ኢትዬጵያውያን ወዳጆቻችንና ደጋፊዎቻችን በሙሉ
----------
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) በገዥዎች ለሚንገላቱ እና ግፍ ለሚፈፀምባቸው መላው ኢትዮጵያውያን ፍትህ እንዲያገኙ ያለ አድሎ ሲሰራ ቆይቷል ። ይህንን ተግባርም አጠናክሮ ለመቀጠል ማህበራዊ ሚዲያ ወሳኝ በመሆኑ ከዚህ በፊት ከ20 k በላይ ተከታይ የነበረው የድርጅቱ የፌስቡክ ገፅ በገዥዎች የሚዲያ ሚሊሻ ርብርብ እንድዘጋ በመደረጉ ምክንያት ይሔንን አነስተኛ ተከታይ ያለው የፓርቲውን ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ተከታዩን ለማሳደግ ፎሎውና ላይክ በማድረግ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ እንድትወዳጁን በአክብሮት እየጠየቅን ለወዳጆችዎም በማጋራት የበኩልዎትን ድርሻ እንዲያበረክቱ አንጠይቅዎታለን ።
https://www.facebook.com/share/18zpXPVs9r/

Political Party

ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ)አዲስ አበባጉዳዩ:- ኮሚሽኑ በአርሲ፣ አሰኮ ፍጅትን በተመለከተ ያወጣውን ሪፖርት በተመለከተ::የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ከነችግሩም ...
19/06/2026

ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ)
አዲስ አበባ

ጉዳዩ:- ኮሚሽኑ በአርሲ፣ አሰኮ ፍጅትን በተመለከተ ያወጣውን ሪፖርት በተመለከተ::

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ከነችግሩም ቢኾን ባለፉት ዓመታት በሀገር ውስጥ የሚፈጸሙ ግፎችን ከቦታው በመረጃና ማስረጃ እያስደገፈ መፍትሔ የሚለውንም እየጠቆመ ያቀርብ እንደነበረ ይታወሳል። ኾኖም ከቅርብ ጊዜያት ወዲኽ ይኽ ትጋትና እውነትን የማፈላለግ ሂደት እየተቀየረ የመጣና ምን አልባትም ሪፖርት ከወጣ እንዲያውም ከሚታወቅበት ወጣ ያለ የማድበስበስ ተግባር እየተስተዋለ ይመስለናል።

ለማሳያ ከሰሞኑ በአርሲ ዞን፣ አሰኮ ወረዳ ሃይማኖትንና ማንነትን ማዕከል ያደረገ የተቀናጀ ፍጅትና ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ቃጠሎን በተመለከተ ኮሚሽኑ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት የሟቾችን ቊጥር 3(ሦስት) ያደረገ ሲኾን፣ ጥቃቱም ሃይማኖትን ማዕከል ያላደረገና የፈጸመውም "ኦነግ ሸኔ" እንደኾነ በእርግተኝነት ደምድሟል። ትብብራችን ባለው መረጃ የሟቾች ቊጥር ከተጠቀሰው በአሥር እጥፍ እንደኾነ፣ ፍጅቱም በአጋጣሚ የተፈጠረ ሳይኾን ሃይማኖትን ማዕከል ያደረገ መኾኑን ከታማኝ ምንጮች አረጋግጧል። ለፍጅቱ የአካባቢው መንግሥት መዋቅር እጁ አለበት የሚለው የሰለባዎች ተደጋጋሚ ቅሬታና በአጠቃላይ በአርሲ የሚደርስ የተቀናጀ ዘር ፍጅት የብዙ አካላት እጅ የሚሳተፍበት መኾኑ እየታወቀ ኮሚሽኑ በፍጥነት ድምዳሜ ላይ መድረስ ፖለቲካዊ ዓላማና ማድበስበስ የተፈለገ አስመስሎታል። ከኮሚሽኑ የሚወጡ ሪፖርቶችንም ሕዝብ እንዳያምናቸው አድርጓል ብለን እናምናለን::

ስለኾነም ኮሚሽኑ ይኽን ሰተሳሳተ ሪፖርት ማውጣት የፈለገበትን መግፍኤና እንደገና በማጣራት የስህተቱን ማስተካከያ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደረግ፣ እንዲኹም የመንግሥት መዋቅሩን ድርሻ በመጥቀስ ተጠያቂነት እንዲኖር ብሎም ሕዝቡ ተፈጥራዊ መብቱን ተጠቅሞ ራሱን እንዲከላከል የሚያደርግ መፍትሔ እንዲጠቁም ጭምር በአክብሮት እንጠይቃለን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

አቶ አብረሃም ጌጡ
የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፕሬዝዳንት
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
***
ገጾቻችንን ይወዳጁ
https://www.facebook.com/share/1JwwMKYDV1/

የብፌ ፖለቲከኛና የሳይበሩ ሸኔ ትንኮሳ የዝኾን ጆሮ ላይ ያረፈ ዝንብ ናቸው! ከሰሞኑ የትብብሩ አመራር በመምሰል የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ ነኝ በሚል በተግባርም በአስተዋጽዖም የማናውቀው ግለሰብ እ...
05/06/2026

የብፌ ፖለቲከኛና የሳይበሩ ሸኔ ትንኮሳ የዝኾን ጆሮ ላይ ያረፈ ዝንብ ናቸው!

ከሰሞኑ የትብብሩ አመራር በመምሰል የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ ነኝ በሚል በተግባርም በአስተዋጽዖም የማናውቀው ግለሰብ እንዲኽና እንዲያ አለ የሚል ውርውር ሲል ታዝበናል። ታዲያ ሳይበር ሸኔውም የዕለት የስድብና የንክሻ ምሱን ያገኘ መስሎት ክራቫት ያሰሩ የብፌ ጌቶችን እንደዋና ማጣቀሻ ሲያዘዋውራቸው ታዝበናል።

ትብብራችን ዐለት ላይ የቆመ ሕንፃ እንጂ ለእነ ሆድ አምላኩ ጊዜም ኾነ ቦታ ሊኖረው አይችልም። በዚኹ አጋጣሚ ብኩርናችኹን ለጥቂት ፍርፋሪ አበል ለውጣችኹ በስሙ ነግዳችሁ ያስፈሰሳችሁት ደም ወደሰማይ እንደሚጮኽ ከሆቴል ዙረቱና ከማወራረጃ ፍለጋ መለስ ስትሉ እንድታስታውሱት ይኹን።

የምን ሥጋ አልጋ ሲሉት መሬት እንዲሉ የጨመደዱትን የልብሳችንን ጫፍ አስለቅቀን አመዱ ላይ ብቻዎን እንዲንከባለሉ ሙሉ ፈቃዳችንን የሰጠን መኾኑን በደስታ እንገልጻለን፤ ለሕዝቡ ክብር ስንል የተውነውንም ይፋ እናደርጋለን። ቦርዱም ተቀላቢን ለመቀነስ እጁ ላይ ያለ በሆደ ሰፊነት የያዘውን የክስ ደብዳቤ እንዲመለከት እኛም እንገፋለን።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ በትብብሩ ስም የትብብሩ አቋም ያልኾነ እንዲያውም እየተከታተለ በተፃራሪው የቆመ በአቅሙ እንደዶሮዋ ጭሬ ላፍሰው መግለጫ ሲሰጥ ሰማንምተናል። በዚ አባሎቻቾን፣ ደጋፊዎቻችን፣ ለእውነት የቆሙ የሚዲያ አካላትና ሕዝቡ ግራ ተጋብቷል። ስለኾነም ትብብሩ ማኅተም ያልተደገፈ፣ በይፋዊ ገጾቻችን ላይ የማይገኝና ትብብሩ በይፋ ያልወከላቸው አካላት የሚሰጡት የጽሑፍም ኾነ የደጅ ጥናት ዓይነት የሚዲያ ልምምጦች የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት አቋም እንዳልኾኑና ወደፊትም እንደማይኾኑ በአክብሮት እንገልፃለን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት - ለኢትዮጵያ
ግንቦት ፳፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ገጾቻችንን ይወዳጁ
https://www.facebook.com/share/1JwwMKYDV1/

የጨረባው  ምርጫ  ዴሞክራሲን  አያዋልድ፣  መፍትሔ  አይፈይድ!   (በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰጠ መግለጫ) ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ከ...
03/06/2026

የጨረባው ምርጫ ዴሞክራሲን አያዋልድ፣ መፍትሔ አይፈይድ!
(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰጠ መግለጫ)

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ከቅድመ ኹኔታዎች አለመሟላትና ከነጉድለቱ፣ መሠረታዊ የኾኑ የሀገር ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት በንግግር፣ በድርድርና በጥልቅ ውይይት መኾን አለበት በሚል ሩቅና አዋጭ እሳቤ፣ የውስብስብ ችግሮች መፍቻ የሀሳብ የበላይነት መኾኑን አስልተን፣ በዚኽ ከደረጃ በታች በኾነ ምርጫ ቀርቶ በእውነተኛ ምርጫም ቢኾን የገዘፈውና የተወሳሰበው ሥርዓት ወለድና መጠነ ሰፊ ችግር ማስወገጃ መንገድ ንግግርና ድርድር ነው በሚል እና ከውጭ ኾኖ ተባለ ከማለት በተጨባጭ ነውሩን ለማጋለጥ እጅግ በተቀዛቀዘ ስሜት በተወሰኑ አስቻይነት አላቸው ባልንባቸው አካባቢዎች ተወስነን ወደምርጫው ገብተናል። በሂደቱ ላይ እንደአቅም የአገዛዙን የነውር ገመና በማጋለጥና መሰል የፖለቲካ የበላይነትን የተጎናጸፍንበት ነው።

ውጤቱ እና በኹሉም አካባቢዎች የተፈጸሙ ችግሮች ገና ተጠቃለው ያልመጡ ቢኾንም በሂደቱ ከቅድመ ምርጫ፣ የምርጫ ዕለትና የምርጫ ማግስት ኾነን ስናየው ከነግዙፍ እንከኑ፣ ከአሳሳቹ 97% የአስቻይነት ሪፖርትና ትንተና፣ ከኢሕአዴጋዊ የጥርነፋ ውርስ ባህርይ/co-opted/ እና 99.9% የጥቅለላ አባዜና ጉምዥታ ያልተላቀቀ፣ በዓይነቱም ኾነ በድርጊቱ በታሪክ ከሚታወቁት የጨረባ ምርጫዎች ያልተለየ መኾኑ ገሃድ የወጣ ነው። በቅርብ ታሪካችን እንዳየነው ይኽ ልማድ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ፣ እጅግ የተወሳሰበውንም የሀገራችንን ችግር ከድጡ ወደ ማጡ ከመውሰድ የዘለለ ዴሞክራሲን አያዋልድም፣ መፍትሔም አይፈይድም! ውጤቱም ምንም ቢኾን የትኛውም ዕጩ በትብብሩ ስም ምክርቤት እንዳይገባና ቢገባም ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ነው። በዚኹ አጋጣሚ ከነበዛ እንከኑም ቢኾን በጠባቧ ቀዳዳ የቦርዱ ኃላፊዎችንና ውስን ድርጅቶች ላደረጉትና እያደረጉ ላለው ጥረት እውቅና አለን።

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት አገዛዙ ለዘመኑ በማይመጥንና ከባህርይ አባቱ በወረሰው የጨረባ ምርጫ ራሱን ለንግሥና ከማጨት ወጥቶ የስልጣን ምንጭና ባለቤት ሕዝብ ብቻ መኾኑን ተረድቶ የሕዝብን ድምጽ እስከሚያከብር ትግሉን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲኾን በቅርቡ ሕዝብን ያሳተፈ ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ የተሟላ መግለጫ የሚሰጥ ይኾናል።

ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ፣ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ እንዲኹም ዓለምአቀፉ ሚዲያ ከሰሞኑ ላደረገው የላቀ አስተዋጽዖ እውቅና እየሰጠን አኹንም እንደጀመረው የኢትዮጵያን ጉዳይ በቅርበት እንዲከታተል፣ ግፎችን እንዲያጋልጥ፣ አገዛዙ ሸብረክ ብሎ ከፖለቲካ ኃይሎች ጋር እስከሚደራደር ምንም ዓይነት እውቅና የመስጠት የሚመስል መልዕክት ከማስተላለፍ እንዲቆጠብ እንጠይቃለን።

ያ ባይኾን በኢትዮጵያውያን ቁስል ላይ እንጨት እንደመስደድ፣ ለንጹሓን እልቂት ቦምብ እንደማቀበል፣ የግፉ አጋፋሪ እና ከኢትዮጵያውያን ጥቅም በተቃራኒ የቆሙ እንደኾነ አድርገን እንቆጥረዋለን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት -ለኢትዮጵያ
ግንቦት ፳፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Address

Addis Ababa
17013

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ -All Ethiopia Unity Party posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share