19/08/2024
በስራ ላይ ያለውን የከተማውን ሲስተም በአዲስ ለመተካት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ስራ ውይይት ተደረገ
: ነሃሴ 12/2016ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት እየሰጠችበት ያለውን የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ሲስተም የሚተካ አዲስ የCRVS, e-ID and Mobile ID የተባለ ሲስተም አልምቶ ወደ ስራ ለማስገባት የጋራ ውይይት መድረክ መደረጉ ተገልጸ።
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በቶፓን ግራቪቲ ኢትዬጵያ አማካኝነት አልምቶ ለመተግበር ስራ የተጀመረውን አዲስ ሲስተም በተመለከተ
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ ፣ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፕ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መለከት ሳህሉ ፣ የቶፓን ግራቪቲ ኢትዮጵያ ኩባንያ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ቃልኪዳን አረጋ እንዲሁም ሌሎች ሃላፊዎችን እና ከፍተኛ ሙያተኞች ተሳትፈውበታል።
ይህ አዲስ ፕሮጀክት ነባሩን ሲስተም በመተካት የተቋሙን አገልግሎት ወደ ኦንላይን የሚያሻግር፣ በከተማዋ ጤና ተቋማት ላይ ስርዓት በመዘርጋት ልደት እና ሞትን በየዕለቱ በመመዝገብ የሲቪል ምዝገባ ሽፋን እና መረጃን የተሟላ ማድረግ የሚያስችል፣ ስማርት ኤሌክትሮኒክ መታወቂያን እንዲሁም ሞባይልን እንደ መታወቂያ መጠቀምያ መተግበርያን ያካተተ ሲሆን አዲስ አበባን ወደ ስማርት ሲቲነት ለመቀየር ከፍተኛ ሚና ያለው ከመሆኑም ባሻገር ተቋም እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ የሚያዘምን እንደሆነ ተነግሯል።
ቶፓን ግራቪቲ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ መንግስት የሼር ባለቤትነት በሃገር ውስጥ የተቋቋመ የልማት ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ሲስተም የማልማት እና ተያያዥ የፖስፖርት እና ልዩ ልዩ መታወቂያ ፕሮጀክት ስራዎችን ተረክቦ እየሰራ ያለ ኩባንያ ነው። ኩባንያው በኢትዮጵያ ፓስፖርት እና መሰል የምስጢራዊ ህትመቶችን መስራት የሚችል ፋብሪካ በሃገር ውስጥ ተከላ መጀመሩ ይታወሳል።
ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን
ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et
ዩትዩብ (youtube)፡ https://www.youtube.com/
ፌስቡክ (facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686
ቴሌግራም (telegram): https://t.me/addisvaitalpress
ፖስታ ሳ.ቁ (Box No)፡ 20320
C R R S A is a government organization established by law to deliver Civil Registration & Residency services in Addis Ababa. The agency is responsible for registration of vital events & issuance of residency identification within the domain of the city.