Finote Tibeb ፍኖተ ጥበብ

Finote Tibeb ፍኖተ ጥበብ ሚሊዮን በለጠ አሰፋ

02/06/2026

https://vt.tiktok.com/ZSxTsujAY/..
ይግባኝ ! ፪
ይግባኝ ለሥላሴ ፥ ለአጋእዝተ ዓለም ፤
ሰማየ ሰማያት ፥ ላለው በአርያም ፤
ምንም ሳላንዛዛ ፥ መግቢያና ሐተታ ፤
በአጭሩ አቀርባለሁ፥ ጥያቄ አቤቱታ ።
የምንሰማውና የምናየው ሁሉም ፤
ከአእምሮ በላይ ነው ፥
. . . ሕማም ማስከተሉም፤
በዚህ በእኛ ዘመን እየሆነ ያለው ፤
የአጼዎቹ ጊዜ አይወዳደረው ፤
ወያኔና ደርግም አይስተካከለው ፤
ከግራኝ በባሰ ፣ ከጣሊያን በከፋ ፣
ከዮዲት ጉዲትም ፥ከድርቡሽ በሰፋ ፤
ስንቱ ተቃጠለ ፥ ስንት ሰው ነደደ ፤
እልፍ ሰው ተገድሎ ፥ ቀሪው ተሰደደ ፤
የምድራዊው ችሎት፥ ፍርድ ተንጋደደ፤
አቤት የምንለው ፥ ስለሌለ ሰሚ ፤
ደረሰብን በደል ፥ ዘግናኝ አስቀያሚ ፤
መዶሻ ሚዛኑ ፥ የሹሙ መፈንጫ ፤
ሕጉ የላላ ነው ፥ ወንጀለኛ መቅጫ ።
የንብረቱ መውደም ፣ የቤቱም ፈረሳ ፤
የልባችን ቁስል ፥ መቼም ሳይረሳ ፤
ሀገር ሳትጠበን ፥ ሁሉም ተርፎ ሞልቶ ፤
ሀብትና ንብረቱ ፣ ጥሪቱ ፥
. . . ተነጥቆ ወይም ተቀምቶ ፤
የቀረ ሰው የለም ፥ ተገፍቶ ተገፍቶ ፤
እንጨቆረር ይሁን? ወይም ገጠር ገብቶ ።
ጌታ ሆይ! ፈጣሪ ፥ ልዑል እግዚአብሔር ፤
እንባችንን አብስ ፥ ሳይውል ወይ ሳያድር ።
ግልባጭ ለገልባጭ ፤ / ካለ
ይግባኝ ! ለአምላክ ፤
ብቻ በፈጠነ መፍትሔውን ላክ ::
መጨረሻ ላይም ፥ አለኝ መፈክር ፤
ቁመቱ ያጠረ ፥ ቅጥነቱ እንደ ክር ፤
የሀገር አፍራሹን ፥ አናቱን አፍርሳት !
አቃጥሎ ፈጀን ፥ የአመድ ልጅ እሳት ፤
አስከፍቶት ይሆን? ይግባኙ ለአራጄ ፤
ተናግሬስ ይሆን? በጣሙን ነድጄ!
ከሆነም አልፈራም ፥ ይኼውና እጄ ።

ሚሊዮን በለጠ አሰፋ፤ 18/9/2018
https://vt.tiktok.com/ZSxTxBsaF/

Ingection exchange rate
31/05/2026

Ingection exchange rate

07/05/2026

ይግባኝ! ለፈጣሪ፥ በላይ በሰማይ፤
ጊዜ ሳላጠፋ በጣም ባስቸኳይ ፤
አዝኖብን ለራቀን ለኃያሉ ጌታ ፤
መንበረ መንግሥቱ ፥ ከዙፋኑ ቦታ።
የፍታብሔሩ ፣ የሕግ ቍጥሩ ፥
. . . አያሻኝም ይቅሩ ፤
እንደሚከተለው ፥ ጉዳዬን ባጭሩ፦
በዚህ ብኩን ጊዜ በዚህ ከንቱ ዓለም፤
የሚነጥቀን እንጂ የሚሠጠን የለም።
ቀማኛዉም በዛ ፥ በሰበብ ባስባቡ ፤
ውሃና ኮረንቲ ፥ ይፋጃል ንባቡ ።
ቴሌም ብሶበታል ጭካኔውም በዛ ፤
ሙጭልፍ ያደርጋታል ካርድ ስንገዛ።
አድፍጦ ጠብቆ ፥ እንደ ሴቷ ነብር ፤
ደም መጣጭም አለ መዋጮና ግብር።
ነዳጅ ስለጠፋ ፥ ሰልፉም ስለ በዛ ፤
የታክሲ ወጪአችን እጅግ በጣም በዛ።
የቻርጅ መኪና፣ ሦስት እግር ኵርኵር ፤
ፋንዲያ የሚጥል ፥ ፈረስ ጋሪ ሳይቀር ፤
እያቆራረጡ ሲወርዱ ሲወጡ ከዚህና ከዛ፤
ሲያልቡን ይውላሉ ፥ በዋዛ ፈዛዛ ።
ግልባጭ ... ለገልባጭ /ካለ
ይግባኝ ለእግዚአብሔር ፤
ብቻ በፈጠነ መፍትሔ ወርውር ።

ሚሊዮን በለጠ አሰፋ ሚያዚያ 27 - 2018

28/04/2026

Address

Addis Ababa

Telephone

0911723075

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Finote Tibeb ፍኖተ ጥበብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Finote Tibeb ፍኖተ ጥበብ:

Share

Category