11/04/2026
*ሞት ክርስቶስን ከሦስት ቀናት በላይ ይይዘው ዘንድ አልቻለምና ጌታችን ከሞት መንጋጋ ወጣ*
ለመላው የቦሌ ክ/ከተማ ክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲሁም ወጣቶች
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ
ውድ የክ/ከተማችን ወጣቶች በጌታችን ስቅለት እና ትንሳኤ የቤተ መቅደስ መጋረጃ መቀደድ በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል የነበረው የጥል ግድግዳ እንደፈረሰ ሁሉ
እኛም በዓሉን ስናከብር ከዘር ከጎጥ ከትንንሽ ሃሳቦች በመራቅ ትልቋን ሃገራችንን ኢትዮጵያን በመያዝ እንዲሁም አፍሪካዊ እሳቤን በማቀንቀን በእውነተኛ እህት እና ወንድማማችነት ስሜት እንድናከብር
በቃሉ የቤትህ ቅናት በላኝ ተብሎ እንደተፃፈ እንዲሁ ክርስቶስ ተሰቅሎ ሲመለከት ቤተ መቅደሱ በተራው ስለ ክርስቶስ እንደቀና እሱም ሰላምን እንደሰጠን እኛም ለኢትዮጵያ እድገት ብልፅግና ሰላም እና አብሮነት በመቅናት የበኩላችንን እንድንወጣ
እንዲሁም ክርስቶስ ነፍሳትን ከሲኦል እና ከእስራት ነፃ እንዳወጣ ወደ ሲኦል ወርዶ ድንቅ ስራን እንደሰራ እኛም ወጣቶች በተሰማራንበት የስራ መስክ ባለን ሞያ ሁሉ ተግተን ከልባችን በመስራት ራሳችንን ህዝባችንን እና ሀገራችንን በኢኮኖሚ ካለንበት ደረጃ ከፍ ማድረግ ይገባናል።
እኛ ወጣቶች በስቅለቱ በክፉዎች ምክር ያልሄደ ተብሎ ስሙ እንደተጠራው ራሱን ሰውሮ እና ደብቆ እንደ ቆየው በጎው እና ፃድቁ ሰው ዮሴፍ ራሳችንን ልናደርግ ይገባል እሱ የአይሁድ ሸንጎ አባል እና አማካሪ ቢሆንም ክርስቶስን ለመስቀል በተማከሩበት በክፉዎች ምክር ያልሄደ በክርስቶስ ላይ በሚሳለቁት በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ ምስጉን ሰው ነበር ራሱን ሰውሮ የቆየው ይህ ሰው ደቀ መዝሙርነቱን ይፋ ያደረገበት ዕለት ግን እጅግ ከባድ ቀን ነበር ክርስቶስ በግፍ ተገርፎ በግፍ በተሰቀለበት ዕለት እኔ የእርሱ ደቀመዝሙር ነኝ ብሎ ያለፍርሃት ራሱን ገለጠ
ይህን ለማድረግ ከጌታ ጋር ለኖሩት ደቀመዝሙራት ግን አልተቻለም ነበር በዚህ ምሳሌነት እኛ ወጣቶችም ሀገራችንን ኢትዮጵያ ሊያፈርሱ ከሚሹ ሌብነት ዘረኝነት ብልሹ አሰራሮች ከፅንፈኛ አስተሳሰቦች እንዲሁም አመለካከቶች በመራቅ እና በመከላከል በክፉዎች ምክር ባለመሳተፍ ሀገር የመገንባት ሂደቱን ልናፋጥን ይገባል
በመጨረሻም አንድ ልብ ሆነው የነበሩትን ሞት እና ሰይጣንን የከፋፈላቸው ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ባለ ብዙ ቀለም ኢትዮጵያ ሀገራችን የምታከብረው የትንሳኤ በዓል በጋራ በመተጋገዝ እንድናከብር ጥሪዬን አስተላልፋለው በድጋሜ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰን አደረሳቹ
ሔለን ለገሰ የቦሌ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣት ክንፍ ኃላፊ