15/04/2022
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሚያዝያ 9 ቀን ጀምሮ አውደ ርዕይ እና ባዛር ያካሂዳል
***********************************************
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከሚያዝያ 9 ቀን እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ አውደ ርዕይ እና ባዛር እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡
በአውደ ርዕዩ 181 አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች 10 መካከለኛ ማኑፈከቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም 8 ተቋማት በድምሩ 199 ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡
በሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቡድን መሪ ወይዘሮ አቦዘነች ነጋሽ እንደገለፁት÷ 50 በመቶ ኢንተርፕራይዞቹ የሴቶች ሲሆኑ አምስት ኢንተርፕራይዞች ደግሞ የአካል ጉዳተኞች ናቸው፡፡
አውደ ርዕዩ እና ባዛሩ 22 ሺህ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሯ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዋናነትም የገበያ ትስስርን ለማጠናከር እና ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በምርትና በጥራት መሻሻሎችን ማሳየታቸውን ለማረጋገጥ ታስቦ መዘጋጀቱ ተመላክቷል፡፡
አውደ ርዕዩ ጀሞ ቁጥር 1 አደባባይ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
በፈትያ አብደላ
ምንጭ ፋና ድረ ገጽ