31/03/2025
አባትና ልጅ ተያይዘው ሽርሽር ሲሄዱ ከአማኑኤል ሆስፒታል አጠገብ ይደርሳሉ...አባት ለልጁ ይህ የእብዶች ሆስፒታል ነው ብሎ ያሳየዋል...
ልጅም አባቱን...ማነው የሚጠብቃቸው? ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ አባትም በር ላይ የቆሙትን ሁለት ኮስማና ዘበኞች ያሳየውና እነሱ ናቸው ይለዋል...
ልጁም ይገረምና... ይህ ሁሉ እብድ ተባብሮ ቢመጣባቸው ምን ያደርጋሉ? ብሎ እንደገና ይጠይቀዋል፡፡
አባትም የኮረኮሩትን ያህል ይስቅና... እብዶች ምን ጊዜም ቢሆን ሊተባበሩ አይችሉም! ብሎ መለሰለት፡፡
ከአንጋፋው ደራሲና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማ "ደራሲው" በተሰኘው መፅሐፉ ውስጥ ከገፅ 125-126
"እብዶች ምን ጊዜም ቢሆን ሊተባበሩ አይችሉም!" የምትለዋን አረፍተ ነገር ሳነባት አስገረመችኝ! አስደነገጠችኝም!
ዛሬ ላይ አንድነትን የማይሹ እና መተባበርን የማይፈልጉ አካላቶች ሀገራችን ውስጥ በሁሉም ብሄርና ሀይማኖት ውስጥ አሉ፡፡
እነዚህ አካላቶች እብዶች ይሆኑ እንዴ?! ...እብዶች በመሆናቸው ይሁን መተባበርንና አንድነትን የማይፈልጉት?
እነዚህን እብዶች እንደ በግ እየተነዳ የሚከተላቸው የሀገሬ መንጋ ህዝብስ እንደነሱ አብዶ ይሆን?
እኔንጃ!
Mp Ethiopia 👌 በትክክል ተግልጾል😊