የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን AA Driver and Vehicle Authority

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን AA Driver and Vehicle Authority

የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን AA Driver and Vehicle Authority Head office Tel +25111667 2315/19/20

07/09/2026
07/09/2026
07/09/2026
07/09/2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጳጉሜን 2 - የማንሠራራት ቀን ያስተላለፉት መልዕክት ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ! ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ...
07/09/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጳጉሜን 2 - የማንሠራራት ቀን ያስተላለፉት መልዕክት

ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!

ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል። ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።

06/09/2026

የእመርታ ቀን!

በአዲስ አበባ ከተማ እመርታ ያስገኙ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች!

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ስኬቶች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር እንዲሁም የኢንቨስትመንት ዘርፉን በማነቃቃት ከፍተኛ ለውጥ ያመጡ ናቸው፡፡

ከተማዋን እንደ አዲስ ከፈጠሩ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች መሀከል የኮሪደር ልማት እንዱና ዋንኛው ነው፡፡ በዚህ ሰፊና ዘመን ተሻጋሪ ስራ ዘመናዊ የመንገድ ግንባታዎች በመግንባትና አስቸጋሪ እና በርካታ አመታት ያስቆጠሩ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት በመለወጥ እንዲሁም ያረጁና የጎሰቆሉ መኖሪያ መንደሮችን በአዲስ በመተካት ብሎም ለንግድ እንቅስቃሴ ምቹ የሆኑ ዘመናዊ ሱቆችንና ማዕከላትን በመገንባት ለነዋሪዎች ምቹ ከባቢን በመፍጠር የተሻለች ውብ ከተማ እንድትሆን ማድረግ ተችሏል፡፡

በከተማዋ የተገነቡ የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች እና የቱሪዝም መዳረሻዎችም ከተማዋን አረንጓዴ ገፅታን በማላበስ ለጤና ምቹ ከተማ እንድትሆን በማድረግ ለቱሪስት ምቹ እና ቀልብ ማረፊያ ከተማ እንድትሆን በማድረግ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኚዎችን ቁጥር በማሳደግ ለሀገር ኢኮኖሚው ከፍተኛ ሚና ማበርከት ችለዋል፡፡

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ እምርታን ካመጡ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች መሀከል የስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚህ እምርታ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በማስፋፋት ማዕከላቱን ለስራ አጥ ወጣቶች በማስተላለፍ አምራች እንዲሆኑ ማድረግ የተቸለ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የከተማዋን ኢኮኖሚ በማሳደግ የከተማ አስተዳደሩ የግል ኢንቨስትመንት በመሳብ ለበርካታ ባለሀብቶች ፍቃድ በመስጠት በግንባታ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ እንዲሁም በሪል-እስቴት ዘርፎች ሰፊ የሥራ እድሎች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታን ተፈጥሯል ፡፡

አዲስ አበባ ያከናወነችው ለትውልድ ተሸጋሪ ሌላኛው ስኬታማ ስራ የትምህርት፣ ጤና እና ማህበራዊ መሰረተ ልማት በማዘመን ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማትን በማስፋፋት ለትውልድ ተሻጋሪ አንዲሆን የተሰራው አመርቂ ስራ ማሳያ ነው፡፡

በአጠቃላይ አዲስ አበባ ከተማ በተመዘገበው የላቀ ስኬታማ ስራ ከተማዋ ለህፃናት እና ለወጣቶች ምቹ በማድረግ የስፖርት ሜዳና የመጫወቻ ስፍራዎች በመገንባት ለሁሉ የምትመች እና ሁሉን አካታች ከተማ በመሆን አመርቂ እመርታን ማስመዝገብ ችላለች፡፡

የእመርታ ቀን አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀ...
06/09/2026

የእመርታ ቀን

አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው! በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል።
በ«ሌማት ትሩፋት» የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን። ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር፤ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን።
እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ድሎች ኢትዮጵያ በሚያጋጥሟት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሸብረክ ሳትል በፅናት መጓዝ መቻሏን የሚያረጋግጡ ህያው ምስክሮች ናቸው፤ ይህ የእመርታ ጉዟችን ለመጪው ዓመት የሰነቀው ተስፋ እጅግ ግዙፍ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Address

Haile Gebresilassie Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን AA Driver and Vehicle Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን AA Driver and Vehicle Authority:

Shortcuts

Share