SNNPRS Bureau of Livestocks and Fishery Resources

SNNPRS Bureau of Livestocks and Fishery Resources Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from SNNPRS Bureau of Livestocks and Fishery Resources, Hawassa.

20/08/2022
26/03/2022
18/02/2022
22/01/2022
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በም/ር/መ/ማዕረግ የግብርና ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር የስራ ርክክብ አከናወኑ፡፡ጥቅምት 01/2014 ዓ.ምበም/ር/መ/ማዕረግ ...
11/10/2021

የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በም/ር/መ/ማዕረግ የግብርና ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር የስራ ርክክብ አከናወኑ፡፡

ጥቅምት 01/2014 ዓ.ም
በም/ር/መ/ማዕረግ የግብርና ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮና የተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የቀድሞው የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ሴክተር ማናጅመንት አባላትና የሴክተሩ ሰራተኞች በተገኙበት የስራ ርክክብ አከናውነዋል፡፡ በስራ ርክክብ ስነ-ስርዓት ወቅትም በምክትል ር/መስተዳድር ማዕረግ የቀድሞው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱና የቀድሞው እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘይኔ ቢልካ ለአዲሱ ኃላፊ የስራ ርክክብ በማከናወን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የተከበሩ አቶ አንተነህ ፍቃዱ አሁን ላይ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል በመንግስት የሚሾሙ ሓላፊዎች እንዲህ በግልጽ የስልጣን ርክክብ ማድረግን ልምድ አድርገው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
የቀድሞው የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ቢሮ አዲስ በወጣው የክልሉ አስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር መመሪያ መሰረት በግብርና መዋቅር እንዲካተት በመወሰኑ ምክንያት የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ቢሮን በዋና ኃላፊነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ዘይኔ ቢልካም የስልጣን ርክክብ አከናውነዋል፡፡ አቶ ዘይኔ በመልክታቸው የተጀመሩ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ አዲሱ አመራርና የዘርፉ ሰራተኞች ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ለተመዘገቡ አመርቂ ውጤቶች ላበረከቱት አስተዋጽዖ የሴክተሩን አመራሮችና ባለሙያዎች ሊመሰገኑ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በም/ር/መ/ማዕረግ የግብርና ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር በመልዕክታቸው የቢሮ ኃላፊዎች የህዝብ አገልጋይ እንደሆኑና አርሶና አርብቶ አደሩ እንዲሁም ሀገራችን ከግብርናው ዘርፍ የምትጠብቀውን ውጤት ለማሳካት ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የዚህ አይነቱ የስልጣን ርክክብ ያልተለመደ በመሆኑ በቀጣይነት ልጠናከር እንደሚገባም አስታውቀዋል፡፡ ይህ የስልጣን ርክክብ የሰንደቅ-ዓላማ ቀን በሚከበርበት ዕለት በመከናወኑ ታሪካዊ ከመሆኑም በላይ የሴክተሩ አመራሮችና ሰራተኞች ለስኬታማ ስራ በጋራ ቃል የምንገባበት ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይ የሴክተሩ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የክልሉን የግብርና ዘርፍ ለማጠናከርና ውጤታማ ለማድረግ የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

08/10/2021
02/10/2021
በጋሞ ዞን በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በዜይሴ ወዜቃ ቀበሌ በዓሣ እርባታ የተሰማሩ ባለሀብቶች ውጤታማ መሆናቸው ተገለጸ፡፡-------//-------በጋሞ ዞን በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በዜይዜ ወ...
29/09/2021

በጋሞ ዞን በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በዜይሴ ወዜቃ ቀበሌ በዓሣ እርባታ የተሰማሩ ባለሀብቶች ውጤታማ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
-------//-------
በጋሞ ዞን በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በዜይዜ ወዜቃ ቀበሌ በዓሣ እርባታ ዘርፍ የጆንሰንና ኢሌኒ የዓሣ እርባታ ዘርፍ የእንቨስትመንት ፍቃድ በመውሰድ በ2010 ዓ.ም በዓመቱ አጋማሽ መሬቱን የተረከበ ሲሆን የተረከበውን መሬት በቀጥታ በተሰማራበት እና ፍቃድ በወሰደበት ዘርፍ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ያሳየ ባለሀብት ነው፡፡ በመሆኑም ለሌሎች ባለሀብቶች በዓሣ እርባታ ዘርፍ ለመሰማራት ፍቃድ በማውጣት መሬት ቢወስዱም ግን ፍቃድ ባወጡበት የሥራ ዘርፍ አለመሰማራት ችግሮች ምክንያቱ ባይታወቅም በሰፊው ይስተዋላል፡፡ በአጠቃላይ በየትኛውም ዓይነት የእንስሳት እርባታ ዘርፍ የሚሰማራ ባለሀብት ውጤታማ መሆን እንደሚችል የጆንሰንና ኢሌኒ የዓሣ እርባታ ዘርፍ አንዱ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡
ምንጭ፡- የጋሞ ዞን እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት መምሪያ

Address

Hawassa
0000

Telephone

251462125491

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SNNPRS Bureau of Livestocks and Fishery Resources posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to SNNPRS Bureau of Livestocks and Fishery Resources:

Share