28/11/2025
"ጠንካራ አባል ለጠንካራ ፓርቲ"
የብልፅግና ቤተሰብ ውይይት አጠናክሮ ማስቀጠል የጠንካራ ፓርቲ ተቋም ውጤት ነው!!
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ የህዳር ወር የብልጽግና የቢሮ ምሁራን አባላት የቤተሰብ ውይይት ተካሄደ። በውይይቱም '' ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር! በብልሹ አሠራር ትግል ውስጥ የአባለት ሚና” እና 20ኛዉ የኢትዩጵያ ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን
'' በሚል ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን የቤተሰብ አባሉ ለፓርቲው አቅም የሚሆንበትን አግባብ እንደሚፈጥር አባላቱ ገልፀዋል ።
የብልፅግና ቤተሰብ ውይይቶች የአባላትን አቅም እና ጠንካራ ተቋም ለመገንባትም ትልቅ ድርሻ እንዳለው በውይይቱ ላይ በመግባባት ውይይቱ ተጠናቋል ።
ህዳር 19/2018 ዓ.ም