31/03/2026
Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና
ከሙስና የጸዳ የግዥ ሥርዓት እንዴት መዘርጋት ይቻላል?
************
በግዥ ሂደት የሚፈጸም ሙስና የአገርን ሀብት ለጥቂት ግለሰቦች ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ በመሆኑ፣ ስርዓቱ ፍጹም ግልጽ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት መሆን አለበት። ውጤታማ የግዥ ስርዓት ሊኖሩት የሚገቡ ባህሪያት መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው።
✍️ በቴክኖሎጂ የታገዘ የግዥ ስርዓት (e-GP)፦ በተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ከሰውን ንክኪ መቀነስ ለሙስና ያለውን እድል በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል። የጨረታ ማስታወቂያዎች፣ ሰነድ ሽያጭና የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ስርዓቶችን በዲጂታል ሥርዓት እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል።
ከዚህ በተጨማሪም የእቃ አቅራቢዎች ያላቸውን ብቃትና ታሪክ በዲጂታል ሥርዓት እንዲመዘገብ በማድረግ፣ ብቃት የሌላቸው ወይም የጥቁር መዝገብ ላይ ያሉ ድርጅቶች እንዳይሳተፉ መቆጣጠርም ይገባል።
✍️ ግልጽነትና ፍትሃዊነት፦ ማንኛውም የግዥ ሂደት ለህዝብና ለተወዳዳሪዎች ክፍት መሆን ይኖርበታል። የጨረታ አሸናፊዎች የሚለዩበት መስፈርት ጨረታው ከመውጣቱ በፊት በግልጽ መቀመጥና ሂደቱም በተቀመጠው መስፈርት መከናዎን አለበት።
ከዚህ ባለፈም የጨረታው አሸናፊ ማን እንደሆነ፣ በስንት ዋጋ እንዳሸነፈና ሌሎች ያልተመረጡበት ምክንያት ለሁሉም ተጫራቾች ይፋ መደረግ ይኖርበታል።
✍️ጠንካራ የቁጥጥርና የኦዲት ስርዓት፦ ግዥው ከተፈጸመ በኋላም ሂደቱ ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። እንዲሁም እያንዳንዱ ከፍተኛ የግዥ ሂደት በገለልተኛ አካል ኦዲት መደረግ ይኖርበታል። በግዥው ሂደቱም ብልሹ አሰራር ተስተውሎበታል ብለው የሚገምቱ ተጫራቾች ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበትና ፈጣን ውሳኔ የሚያገኙበት ገለልተኛ አካል ሊኖር ይገባል።
✍️ የባለሙያዎች ሥነ-ምግባርና ብቃት፦ የግዥ ባለሙያዎች ለጥቅም የማይደለሉና በሙያው የሰለጠኑ መሆን አለባቸው። በግዥ ውሳኔ ሰጪነት ላይ ያሉ ባለሙያዎች ከሚጫረቱ ድርጅቶች ጋር ማንኛውም አይነት ዝምድና ወይም ጥቅም ካላቸው ከጨረታ ሂደቱ ራሳቸውን እንዲያገሉ የሚያስገድድ ህግ መኖሩን በመገንዘብ ራሳቸውን ማግለል ይኖርባቸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በግዥ ሂደት ላይ ስልጣኑን ያለአግባብ የተጠቀመ ማንኛውም አካል በህግ ተጠያቂ የሚሆንበት አሰራር በማጠናከር ተጠያቂ ማድረግ ያስፈልጋል።
በአጠቃላይ የግዥ ስርዓቱ ከሰዎች ዝምድና እና ከድብቅ ድርድር ይልቅ በውድድር፣ በብቃት እና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ በማድረግ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል ይገባል።
ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!
የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾
ሞባይል መተግበሪያ
ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis
or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231
ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/
ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡