Ethiopian Trading Businesses Corporation - ETBC

Ethiopian Trading Businesses Corporation - ETBC Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Trading Businesses Corporation - ETBC, Public & Government Service, Addis Ababa.

15/09/2026

የተሽከርካሪዎች የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

12/09/2026
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2019 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል::
10/09/2026

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2019 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል::

ኮርፖሬሽኑ በህክምና ላይ ለሚገኙ ህሙማን የበዓል ስጦታ አበረከተኮርፖሬሽኑ ከራስ ቲያትር እና ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በተለያዩ ሆስፒታሎች ማለትም በአበበች ጎበና፣ በራስ ደስታ...
09/09/2026

ኮርፖሬሽኑ በህክምና ላይ ለሚገኙ ህሙማን የበዓል ስጦታ አበረከተ

ኮርፖሬሽኑ ከራስ ቲያትር እና ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በተለያዩ ሆስፒታሎች ማለትም በአበበች ጎበና፣ በራስ ደስታ፣ ዘውዲቱ፣ ዳግማዊ ምኒሊክ እና ጋንዲ በመገኘት በህክምና ላይ ለሚገኙ150 ህሙማን የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን በማስመልከት የፍራፍሬ ምርቶችን ጳጉሜን 04/ 2018 ዓ.ም አበርክቷል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ሶስተኛውን ዘንቢል ሱፐር ማርኬት ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ከፈተየኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በዋና መ/ቤት ግቢ ውስጥ ጳጉሜን 04 ቀን 2018 ዓ.ም ዘንቢል ሱፐር ማርኬት ጠ...
09/09/2026

ኮርፖሬሽኑ ሶስተኛውን ዘንቢል ሱፐር ማርኬት ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ከፈተ

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በዋና መ/ቤት ግቢ ውስጥ ጳጉሜን 04 ቀን 2018 ዓ.ም ዘንቢል ሱፐር ማርኬት ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ በመክፈት ተደራሽነቱን በማስፋት ላይ ይገኛል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በኃይሉ ንጉሴ ኮርፖሬሽኑ ያሉትን ሱፐር ማርኬቶች ቁጥር በመጨመር ተደራሽነቱን እያስፋፋ መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ ቀደም በፒያሳና ሰሚት ሱፐር ማርኬቶች መከፈታቸውን አስታውሰዋል፡፡ በቀጣይም ሃይፐር ማርኬት ለመክፈት መታቀዱን በመጠቆም ህብረተሰቡ በአቅራቢያቸው የሚገኙ ሱፐርና ሚኒ ማርኬቶችን በመጠቀም ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በኮርፖሬሽኑ የኢንዱስትሪ ምርቶች ንግድ ዘርፍ ም/ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዮሚ አበጀ በበኩላቸው ዘርፉ በአለ በጅምላ በኩል በጅምላ የሚያቀርባቸው ምርቶች አሁን በተከፈቱት ሱፐርና ሚኒ ማርኬቶች ውስጥ በችርቻሮ እየቀረቡ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይም በተለያዩ ከተሞች ላይ የማስፋፋት ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል፡፡

ሱፐር ማርኬቱ የኢንዱስትሪ ውጤቶች የሆኑትን የምግብ ዘይት፣ የስንዴ ዱቄት፣ ፓስታ፣ ማካሮኒ፣ የንጽህና መጠበቂያዎች እና የመሳሰሉትን በዓይነት፣ በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ የያዘ ሲሆን ቦታው ለተገልጋዮች ምቹና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው፡፡

ይምጡ፣ ይጎብኙን፣ በምቾት ሸምተው ይመለሳሉ!

ኮርፖሬሽኑ አነስተኛ ገቢ ላላቸው  ሠራተኞች የአዲስ ዓመት ስጦታ አበረከተየኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አነስተኛ ገቢ ላላቸው በአዲስ አበባና በክልል ቅርንጫፍ ግብይት ማዕከላት ለሚገኙ...
08/09/2026

ኮርፖሬሽኑ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሠራተኞች የአዲስ ዓመት ስጦታ አበረከተ

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን አነስተኛ ገቢ ላላቸው በአዲስ አበባና በክልል ቅርንጫፍ ግብይት ማዕከላት ለሚገኙ የቢሮ ውበትና የጽህፈት ሥራ ረዳት ሠራተኞች መጪውን አዲስ ዓመት በማስመልከት የ5ኪሎ የስንዴ ዱቄት እና የ5 ሊትር የምግብ ዘይት እንዲሁም የገንዘብ ስጦታ አበርክቷል፡፡

በዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት የተዘጋጀውን ስጦታ የኮርፖሬሽኑ ሥራ አመራር አባላት ለሠራተኞች ያበረከቱ ሲሆን በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በኃይሉ ንጉሤ ባስተላለፉት መልዕክት ዝቅተኛ ገቢ እያገኙ ተቋማቸውን ለመቀየር እየተጉ የሚገኙ ሠራተኞች ተቋሙን ለማሳደግ ያላቸውን ጥረትና አስተዋጽዖ አድንቀው ኮርፖሬሽኑ ይህንኑ ቁርጠኝነታቸውን ከግምት በማስገባት በየበዓላቱ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞችም በተበረከተላቸው የአዲስ አመት ስጦታ መደሰታቸውን ከምስጋና ጋር ገልፀዋል::

የጨረታ ማስታወቂያ
08/09/2026

የጨረታ ማስታወቂያ

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 16:30
Tuesday 08:00 - 16:30
Wednesday 08:00 - 16:30
Thursday 08:00 - 16:30
Friday 08:00 - 16:30
Saturday 08:00 - 12:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Trading Businesses Corporation - ETBC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Trading Businesses Corporation - ETBC:

Shortcuts

Share