Lideta woreda 5 communication office

Lideta woreda 5 communication office ይህ የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ኮሙዩኒኬሽን ፅ/ቤት ትክክለኛ

06/04/2026
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ሁሉን አቀፍ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ​መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም — በልደታ ወረዳ 05 "ትቦዎች የውሀ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ አይደሉም!!" በሚል ...
04/04/2026

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ሁሉን አቀፍ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ

​መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም — በልደታ ወረዳ 05

"ትቦዎች የውሀ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ አይደሉም!!" በሚል መሪ ቃል የጽዳት ዘመቻ ንቅናቄ ተካሄደ።
​በወረዳው የጽዳት እና ውበት ጽ/ቤት አስተባባሪነት የተከናወነው ይህ ንቅናቄ፣ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝን ሥርዓት በማስያዝ ሊከሰቱ የሚችሉ የጎርፍ አደጋዎችን ለመከላከል ያለመ ነው።

ቆሻሻን በአግባቡ በማስተዳደር አካባቢያችንን ከጎርፍ እንከላከል፤ ንጽህናችንን በመጠበቅም ጤናማና ውብ ከተማን እንፍጠር!

አረንጓዴ አሻራ፥ የዚህ ትውልድ ውጤት፤ የመጋቢት ስኬት! አረንጓዴ አሻራ በኢትዮጵያ፥ በ2011 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ ካስመዘገቡት አኩሪ፥ ...
01/04/2026

አረንጓዴ አሻራ፥ የዚህ ትውልድ ውጤት፤ የመጋቢት ስኬት!

አረንጓዴ አሻራ በኢትዮጵያ፥ በ2011 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ ካስመዘገቡት አኩሪ፥ በትውልድ ተዘካሪ ውጤት አንዱ ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የደን መጨፍጨፍ ለመከላከልና የአካባቢን የአየር ሁኔታ ለማሻሻል ብሎም የተራቆተውን መሬት አረንጓዴ በማልበስ የምግብ ሉኣላዊነትን ለመረጋገጥና በተለይም የአረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጾ እያበረከተ ይገኛል፡፡

ይህ ሀገራዊ ፕሮጀከት የመሬት መራቆትን በመቀነስ፣ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራዎችን በማጠናከር የምግብና የውሃ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ ኑሮን በማሻሻል እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅምን በማሳደግ የሀገሪቱን የወደፊት መልካም ዕጣ ፈንታ የሚያሳይ መሰረት እየጣለ ይገኛል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሀገር በቀል እሳቤ ከመሆን ባለፈ ባለቤቱና ተጠቃሚው ህዝቡና ህዝቡ ብቻ በመሆኑ፣ በዚህም በርካታ የስራ ዕድል መፍጠር የተቻለ ሲሆን በተለይ ወጣቶችና ሴቶች ችግኝ በማፍላትና በመንከባከብ በስፋት ተጠቃሚ እየሆኑ ነው፡፡ አረንጓዴ አሻራ የተሻሻለ የግብርና አሰራር በማስፈን፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ የውሃ ሀብትንና የብዝሃ ህይወት ጥበቃን በማረጋገጥ ዘላቂ ተጠቃሚነትን ያስገኝ ነው።

በአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች ተተክለዋል። በዚህ ሀገራዊ ፕሮጀክት በተለያዩ አካባቢዎች የችግኝ ማፍያ ቦታዎች ተቋቁመው በስፋት እየሰሩ ናቸው ፤ማህበረሰቡን በማሳተፍ የችግኝ ተከላና እንክብካቤ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ሲሆን በተለይም የአረንጓዴ አሻራ ፕሮጀክት በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት አገራትም ተስፋፍቶ መልካም ተሞክሮ በመሆን አርአያ መሆን ችሏል፡፡

አሁን ላይ ኢትዮጵያውያን በየአመቱ አሻራቸውን ለማሳረፍ በጉጉት የሚጠባበቁት የአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር ዘመቻ የአገሪቱን የአረንጓዴ እጽዋት ሽፋን ከማሳደግ በተጨማሪ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል በሰዎች አኗኗር ዘንድ ከፍተኛ ለውጥ እንዲኖር አድርገዋል፡፡

አረንጓዴ አሻራ፥ የዚህ ዘመን ትውልድ ውጤት ፤ የመጋቢት ስኬት!

አበባ የሆነችው አዲስ አበባ… የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በፈረንጆቹ 2025 መጋቢት ወር ከጆሃንስበርግ ከተማ ምክር ቤት ተወካዮች ጋር ውይይት ሲያካሂዱ ለንግግራቸው መነሻ ያደረ...
30/03/2026

አበባ የሆነችው አዲስ አበባ…
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በፈረንጆቹ 2025 መጋቢት ወር ከጆሃንስበርግ ከተማ ምክር ቤት ተወካዮች ጋር ውይይት ሲያካሂዱ ለንግግራቸው መነሻ ያደረጓት አዲስ አበባን ነበር።

ፕሬዚዳንቱ በአዲስ አበባ ከተማ የተመለከቱት የለውጥ ጉዞ እጅግ የሚደንቅ መሆኑን በመጥቀስ የከተማዋን ለውጥ በአድናቆት አንስተዋል።

በወቅቱ በመድረኩ ባደረጉት ንግግርም ‘በቅርቡ አዲስ አበባ ከተማን ጎብኝቼ ነበር፤ ከተማዋ እጅግ ምቹ፣ ውብ እና ጽዱ እንደሆነች አይቻለሁ። ኢንቨስትመንት እና ንግድን ተሟሙቆባታል ብለዋል።

“አዲስ አበባ የምታምር ከተማ ሆናለች። ዛሬ በአዲስ አበባ ስትንቀሳቀሱ የደመቁ ሰፊ እና ጽዱ ጎዳናዎች ታያላችሁ፤ የንግድ እንቅስቃሴውም እያደገ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ የፕሬዚዳንት ራማፎሳ የአድናቆት ምስክርነት ሌሎች አዲስ አበባን ባለፉት የለውጥ ዓመታት የጎበኟት ሁሉ የሚሰጡት ምስክርነት ሆኗል።

ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር በመዲናዋ የተወያዩት የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኤዚያኮንዋ የከተማዋን ውበትና ለውጥ አሞካሽተዋል።

አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በተጀመረው የመልሶ ማልማት ሥራ መደነቃቸውን በመግለጽ፤ በከተማዋ ልማት የነዋሪዎች ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ አካታች የልማት ስትራቴጂ ተተግብሯል ብለዋል።

የአዲስ አበባ የልማት ጉዞ በአፍሪካ ከተሞች እንደ ልምድ ሊስፋፋ እና አዲስ አበባም ሚናዋን ልትወጣ እንደሚገባም ተናግረዋል።

መዲናዋ ባስተናገደቻቸው ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ መድረክ ለመሳተፍ እንዲሁም ኢትዮጵያን ለመጎብኘት በአዲስ አበባ የተገኙ መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የድርጅት መሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ጎብኚዎች ሁሉ የከተማዋን ሁለንተናዊ ለውጥ ከማድነቅ ወደኋላ አላሉም።

የአንድነት ፓርክ፣ የወዳጅነት ፓርክ፣ የእንጦጦ ፓርክ፣ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ልማት፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የሳይንስ ሙዚዬም እና ሌሎች ሥራዎች የመዲናዋ የለውጥ ትሩፋት ናቸው።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lideta woreda 5 communication office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Lideta woreda 5 communication office:

Share