ከጨርቆስ ሰማይ ሥር

ከጨርቆስ ሰማይ ሥር Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ከጨርቆስ ሰማይ ሥር, kirkos, Addis Ababa.

"ትናንት የዛሬ መነሻ፣ ዛሬ ደግሞ የነገ መሰረት ነው። ዛሬ ላይ ሆነን ወደ ኋላ ስንመለከት፣ እነዚያን የማይደበዝዙ ትዝታዎች ስናወሳ፣ ለዛሬው ማንነታችን ጉልበት፣ ለነገው ጉዟችን ደግሞ ስንቅ ይሆናሉ ። የማይደበዝዘው ትዝታ በጨርቆስ ምድር ሰላም...ፍቅር... አንድነት

የድል ጉዞ እንደቀጠለ ነው !! ዛሬ በነበረው ተጠባቂ ጨዋታ ክለባችን ቅዱስ ቂርቆስ እግር ኳስ ክለብ አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት የኛ ፍቅር አንድነትን   2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በጨ...
03/06/2026

የድል ጉዞ እንደቀጠለ ነው !!
ዛሬ በነበረው ተጠባቂ ጨዋታ ክለባችን ቅዱስ ቂርቆስ እግር ኳስ ክለብ አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት የኛ ፍቅር አንድነትን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በጨዋታው ኮከብ ተጨዋች ብሩክ ሃይሌ (ኪለ) ተመርጧል ። ይህ ድል የሁላችንም ነው—የተጫዋቾቻችን ብርታት፣ የአሰልጣኞቻችን ጥረት እና የእናንተ የደጋፊዎቻችን ውጤት ነው !
ኩራት ለቂርቆስ!"

03/06/2026

😭

03/06/2026

የእግዚአብሔር ምሕረት ቸርነት በዘመናችን ሲገለጥ መራመድ መሄድ የማይችል ህጻን ልጅ በስውሯ ማርያም ምልጃ መቆም መራመድ ጀመረ።

02/06/2026

የቀድሞ ተጨዋች ሙሉጌታ ማሞ በውጪ ሃገር ማሕበሩ ከተመሠረተ ጀምሮ ሲያግዝ የነበረ ሲሆን ለእረፍት ኢትዮጵያ መጥቶአል በአካል በመገኘት ለቲሙ የምሳ ግብዣ አድርጎል ። የቂርቆስ ለገሃር የጤና ስፖርት ማሕበር በገንዘብ ስለደገፉ ከፕሬዝዳንቱ ደረጄ አንተነህ እጅ የምስክር ወረቀት እና የቲሙ መለያ ቲሸርት በስጦታ መልክ ተበርክቶለታል ።

29/05/2026

በከፍተኛ ዲቪዚዮን እየተወዳደረ የሚገኘው የቅዱስ ቂርቆስ እግር ኳስ ቡድን ከዕለት ወደ ዕለት ጥሩ መሻሻል እያሳየ በደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ይገኛል ። ለዚህም ዋና አሰልጣኝ ሳሚ ምስጋና ይገባዋል ።

29/05/2026

ብልሕ የሆኑ ቤተሰቦች ሴት ልጆቻቸውን ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ለፍልሰት አይገፋፋም:ማንኛውም ለስራ ስምሪት ወደ ዉጪ የሚደረግ ጉዞ ሕግና ስርዓቱ በተጠበቀ መልኩ መሆን አለበት።

28/05/2026

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ አሻራ ያሳረፉትን፣ ዋሊያዎቹን ከ31 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የመሩትን አንጋፋውን እና ተወዳጁን አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው በቅርቡ አግኝቻቸው ነበር።
ስለ "ከጨርቆስ ሰማይ ስር" ገጻችን ዓላማና ስራዎች ሳጫውታቸው በትልቅ አክብሮትና ደስታ ነው የተቀበሉኝ። የእሳቸው ታሪክና የሕይወት ተሞክሮ ለሁላችንም ትልቅ በመሆኑ፣ አንድ ቀን በገጻችን ላይ እንግዳ እንዲሆኑ ላቀረብኩላቸው ጥያቄ በሙሉ ፈቃደኝነት "እሺ" ብለውኛል።
አንድ ቀን ከኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው ጋር የሚኖረንን ልዩ ቆይታ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

26/05/2026

ስንቶቻችን እናውቃለን ብጽአት ስዩምና በዛወርቅ አሰፋ የተሳተፋበት የተሾመ ወልዴ ወይ ፍቅር የተሰኘው ሙዚቃ እጅግ ተወዳጅ ዘመን የማይረሳው ሙዚቃ ይኸን ጊዜ እንዴት ታስታውሱታላችሁ ?

26/05/2026
አይ ልጅነት! ሁላችንም ሰፈራችን ውስጥ አንድ 'ታዋቂ' ሱቅ ነበረችን። እኛ ልጆች ሆነን ከሱቅ ወጥቶ አይተነው ስለማናውቅ፣ መንገድ ላይ ካየነው ሌላ ሰው ነበር የሚመስለን። "እሱ እኮ የሱቁ ...
26/05/2026

አይ ልጅነት! ሁላችንም ሰፈራችን ውስጥ አንድ 'ታዋቂ' ሱቅ ነበረችን። እኛ ልጆች ሆነን ከሱቅ ወጥቶ አይተነው ስለማናውቅ፣ መንገድ ላይ ካየነው ሌላ ሰው ነበር የሚመስለን። "እሱ እኮ የሱቁ ሰውዬ ነው!" ብለን ስንደነቅ ትዝ ይላችኋል? 😂እናንተስ የልጅነት ጊዜያችሁ የማይረሱ ትዝታዎች ምንድን ናቸው? ከሰፈራችሁ ሱቅ ጋር የተያያዘ አስቂኝ ታሪክ አላችሁ? ኮመንት ላይ አካፍሉን!

Address

Kirkos
Addis Ababa

Telephone

+251976051514

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ከጨርቆስ ሰማይ ሥር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ከጨርቆስ ሰማይ ሥር:

Share