ጉለሌ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት በአዲስ ምዕራፍ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • ጉለሌ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት በአዲስ ምዕራፍ

ጉለሌ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት በአዲስ ምዕራፍ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ጉለሌ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት በአዲስ ምዕራፍ, Government Organization, Addis Ababa.

 #ጉለሌ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ 2019 ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያደጉ ሀገራቸውን በአለም መድረክ ለማየት ጫፍ የደረሱ ኩራቶቻችን ናችሁ
01/06/2026

#ጉለሌ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ 2019 ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያደጉ ሀገራቸውን በአለም መድረክ ለማየት ጫፍ የደረሱ
ኩራቶቻችን ናችሁ

27/05/2026

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሰን፣ አደረሳችሁ!

ስለዒድ አል-አድሐ “ዐረፋ” በዓል ስናስብ ሦስት ነገሮች ቀድመው ይታወሱናል። መስዕዋትነት፣ መታዘዝ እና መተጋገዝ። አባት ልጁን ለመስዕዋት ያቀረበበት፤ ልጅ የአባቱን ትዕዛዝ የፈጸመበት፤ ሙስሊሞች የመተጋገዝን እሴት ለዓለም የገለጡበት በዓል ስለሆነ “ዐረፋ” በሕዝበ-ሙስሊሙ ዘንድ ትልቅ ትርጉም አለው።

እስማኤል ለነብዩ ኢብራሂም የመጀመሪያ እና ተወዳጅ ልጃቸው ነው። አላህ (ሱ.ወ.) ይሄን ተወዳጅና የመጀመሪያ ልጅ እንዲሠዉለት ሲጠይቃቸው ታዘዙ እንጂ ወደኋላ አላሉም። ለመታዘዝ የሞከሩት ነገሩ ቀላል ሆኖ አይደለም። ልጅን ያህል ነገር መስዕዋት ማድረግ ምኑ ይቀላል? የአባትነት ስሜት ይተናነቃል። የሰይጣን ሹክሹክታ ይፈታተናል። የቤተዘመድን ወቀሳ እና የጎረቤትን አስተያየት መቋቋምም ይከብዳል። ነብዩ ኢብራሒም፥ በዚህ ሁሉ አጣብቂኝ ውስጥ አንድ ሐቅ ተገልጦላቸዋል። ከራስ ስሜት፣ ከሰው ሐሜት እና ከወዳጅ ፍላጎት የሚልቅ ታላቅ ዓላማ እንዳለ አምነዋል። ስለዚህም በፈተና ውስጥ ጸንተው ቆሙ፤ ቆራጥነታቸውም በተግባር ታየ።

ሀገር የምትገነባው ከራስ ጥቅም በላይ በሚያስቡ እና ከግላዊ ፍላጎታቸው በላይ ለመፈጸም በቆረጡ ዜጎች ነው። የሚወዱትን ነገር እንኳን ሳይቀር ለመሠዋት ዝግጁ የሆኑ ዜጎች ሲበዙላት ሀገር ትበረታለች። እስማኤላቸውን ለመስጠት የማያመነቱ ዜጎች የሞሉባት ሀገር ጽኑ ናት።

የለመድናቸው፣ የምንወዳቸው፣ የራሳችን ገንዘብ ያደረግናቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጥ ዓላማ ግን አለ፤ እሱም “ሀገርነት እና ሉአላዊነት” ይሰኛል። ሀገርነት የሚገነባው ከመውሰድ ይልቅ በመስጠት ነው። ሉአላዊነት የሚጸናው በፈተና ሳይወድቁ በመቆም፤ በወጀብ ሳይናወጡ መጓዝ በመቻል ነው።

የእውነት ኢትዮጵያ ሲያልፍላት ማየት የምንሻ ከሆነ ምኞታችን በተግባር ይገለጥ። የሀገር ኩስመና ካሳሰበን ለግዝፈቷ እንድከም። ያጎበጣትን የድህነት ቋጥኝ ለመሸከም ትከሻችንን እናመቻች። ጎተራዋ እንዲሞላ እጃችን አፈር ይንካ። የጠየመ ገጽዋ እንዲፈካ በሥራ ሌት-ተቀን እንሰለፍ። የተቀማ ክብሯ እስኪመለስ ድርሻችንን እንወጣ። ሀገር መውደዳችን ከልብ ከሆነ መስዕዋት ለመሆን አናመንታ።

የዐረፋ በዓል የመታዘዝና የመስዕዋት ብቻ ሳይሆን የመደጋገፍና የመተጋገዝ በዓል ጭምር ነው። በዐረፋ ከሚከናወነው እርድ አንድ ሦስተኛው ለምስኪኖች እንዲሰጥ የእስልምና አስተምህሮ ያዛል። በዐረፋ ሕዝበ-ሙስሊሙ ደስታና ሐዘኑን እየተጋራ በዓሉን ያከብራል። የዐረፋ እለት አንድም ሰው ተከፍቶ አያሳልፍም፤ በዐረፋ ሰሞን ማንም ሰው ተርቦና ተጠምቶ አያድርም። በዓሉ ትርጉም የሚሰጠው ሕዝበ-ሙስሊሙ ያለውን ተካፍሎ ሲያከብረው ነው። ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታን የሚሻገሩበት መፍትሄው መተሳሰብና መተጋገዝ እንደሆነ ከዐረፋ እንማራለን። ሀገርም ከፈተናዎችዋ በላይ እንድትሆን እኒህ እሴቶች ወሳኝ ናቸው።

ዐረፋ ማኅበረሰባዊ በዓል የሚባለው ለዚህ ነው። ሰዎች በግላቸው የሚያከብሩት አይደለም። ቤተሰቡ፣ ጎረቤቱ፣ ሠፈሩ፣ ከተማው የሚያከብረው በዓል ነው። ያላቸውና የሌላቸው፤ የሚችሉና የማይችሉ፤ ታላላቆችና ታናናሾች፤ ባለ ሥልጣናትና ተራ ዜጎች፣ በአንድነት የሚያከብሩት በዓል ነው። ሰው የሚኖረው በቤቱ ውስጥ አይደለም። በማኅበረሰቡ ውስጥ ነው።

ማኅበረሰባዊ ትሥሥርና ትብብር ለዜጎች እና ለሀገር ደኅንነት ወሳኝ ናቸው። ማኅበረሰባዊ ትሥሥር ስለሌሎች እንድናስብ፣ ስለሌሎች እንድንሠራ እና ስለ ሌሎች ዋጋ እንድንከፍል ያደርገናል። ራሳችንን በሌሎች ጫማ ላይ አቁመን እንድናይ ያስችለናል። የሁላችንም ሰላም፣ የሁላችንም ደኅንነት እና የሁላችንም ጥቅም ካልተከበረ በቀር የግላችንን ብቻ ልናስከብር እንደማንችል ያስገነዝበናል። ስለዚህም ማኅበራዊ ግዴታን እንደ ዜግነት ግዴታ ወስደን እንድንሠራ ያደርገናል።

ምርጫ ማኅበራዊና ዜግነታዊ ግዴታዎችን ከምንወጣባቸው የዴሞክራሲ መገንቢያ መሳሪያዎች መካከል ዋነኛው ነው። ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ዴሞክራሲ አይሳካም። ያለ ምርጫም የሕዝብ ተሳትፎ ምሉዕ አይሆንም። የዴሞክራሲያችን መሰረት ጥንካሬው የሚለካው በተሳትፎአችን መጠን ነው።

የዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ሀገረ-መንግሥታዊ ሥርዓታችን የሚጠነክርበት መሰረት ነው። የዴሞክራሲ ልምምዳችን አንድ ደረጃ ከፍ የሚልበት፤ የቀጣይ ዓመታት የሀገራችንን እጣ-ፈንታ የምንበይንበት፤ ከምንም በላይ ብዝሃ-ድምጽ የሚሰማበት የሕግ መወሰኛ ምክርቤት የምንመሰርትበት ወሳኝ አጋጣሚ ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር ዜግነታዊ ግዴታችንን ለመወጣት ብቻ ሳይሆን በካርዳችን ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለማረጋገጥ እየተዘጋጀን እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ።

በድጋሚ መልካም የዐረፋ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ!
ዒድ ሙባረክ!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ግንቦት 18፣ 2018 ዓ.ም

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች  የእግር ኳስ ውድድር በክ/ከተማው  ሻምፒዮናነት ተጠናቀቀ።ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ፅ/ቤት   በክ/ከተማና በ10ሩም ወረዳዎች ያሉ የ...
27/05/2026

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች የእግር ኳስ ውድድር በክ/ከተማው ሻምፒዮናነት ተጠናቀቀ።

ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ፅ/ቤት

በክ/ከተማና በ10ሩም ወረዳዎች ያሉ የተቋም ሰራተኞች መካከል ለሶስት ሳምንታት በ 3 ምድብ ተክፍሎ በ 11 ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የቆየው የእግር ኳስ ውድድር በ 03 ሜዳ በተካሄዱ የደረጃና የፍፃሜ ውድድሮች የተጠናቀቀ ሲሆን ጉ/ክ/ከተማ ከወረዳ 9 አስተዳደር ባደረጉት የዋንጫ ጨዋታ ጉለሌ ክ/ከተማ 4 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል።
በውድድሩ ወረዳ 10 አስተዳደር 3ኛ፣ ወረዳ 9 ሁለተኛ እና ክፍለ ከተማው 1ኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

 #ሲሪያ ተሾመ የክለባችን ኮከብ ለብሄራዊ ቡድን ማሸነፊያ ጎሎች ሁለት አሲስት ጀግናችን በርቺ
25/05/2026

#ሲሪያ ተሾመ የክለባችን ኮከብ ለብሄራዊ ቡድን ማሸነፊያ ጎሎች ሁለት አሲስት ጀግናችን በርቺ

456 likes, 10 comments. “ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪 Football Federation”

25/05/2026
🇪🇹 የጨዋታ ቀን ! ⚽️በ2026 ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ዛሬ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ቡሩንዲን ከቀኑ 9:00 ላይ ትገጥማለች። ...
24/05/2026

🇪🇹 የጨዋታ ቀን ! ⚽️

በ2026 ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ዛሬ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ቡሩንዲን ከቀኑ 9:00 ላይ ትገጥማለች።

ድል ለኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

 #2ኛው ተወዳጁ የባቤ ካፕ  በደጃች ውቤ ጤና ስፖርት አሸናፊነት ተጠናቀቀፎቶ VIP.COM02
18/05/2026

#2ኛው ተወዳጁ የባቤ ካፕ በደጃች ውቤ ጤና ስፖርት አሸናፊነት ተጠናቀቀ
ፎቶ VIP.COM02

የ2018 የአዲስ አበባ ሊግ 22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር 21ኛ ሳምንት የደረጃ ሰንጠረዥ🏟አበበ ቢቂላ ስታዲየምTelegram T.me/Dagu_SportTelegram T.me/DaguLive
14/05/2026

የ2018 የአዲስ አበባ ሊግ

22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር
21ኛ ሳምንት የደረጃ ሰንጠረዥ

🏟አበበ ቢቂላ ስታዲየም

Telegram T.me/Dagu_Sport
Telegram T.me/DaguLive

 #ጉለሌ 3 ተጫዋች ለኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን መልካም ዕድል ሀገራችን መልካም ዕድል ልጆቻችን
12/05/2026

#ጉለሌ 3 ተጫዋች ለኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን
መልካም ዕድል ሀገራችን መልካም ዕድል ልጆቻችን

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911775075

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጉለሌ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት በአዲስ ምዕራፍ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share