23/04/2026
እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ ያለን!! የ2018 በጀት አመት የግማሽ ዓመት /የ6 ወር/ ስራዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ፋይናንስ ቢሮ ባደረገው ምዘና ከ11ዱ ክፍለ ከተሞች 1ኛ በመውጣታችን የተሰማንን ደስታ እየገለፅኩ።
ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ባለሙያዎች ፣ በክፍለ ከተማችን ለምትገኙ ትምህርት ቤቶች፣ ወረዳዎች፣ ጤና ጣቢያዎች ፣ የፑል አስተዳድርና ፋይናንስ ጽ/ቤቶች እና ለ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊና ባለሙያዎች ላደረጋችሁት ትጋት ላቅ ያለ ምስጋናዬን እያቀረብኩ ለሁሉም ባለሙያዎች እና ይሄንን ተግባር በቁርጠኝነት ላስፈፀማችሁ ኃላፊዎች ለበጀት አመቱ ማጠቃለያ ይሄንን አስመስጋኝ ስራ እንድታስቀጥሉ መልክቴን አስተላልፋለሁ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ እንየው ኃይሉ
ሚያዚያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም