Arada Woreda five communication office

Arada Woreda five communication office ትክክለኛና ጥራት ያለው መረጃ ለህዝብ ተደራሽ ማድረግ

በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ሰራተኞች ነን ፤አመራሮችን እናውቃለን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እናሰራላችዋለን በማለት 6360259.09 (ስድስት ሚሊየን ሶስት መ...
23/02/2026

በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ሰራተኞች ነን ፤አመራሮችን እናውቃለን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እናሰራላችዋለን በማለት 6360259.09 (ስድስት ሚሊየን ሶስት መቶ ስልሳ ሺ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ ) ብር አታለው የተቀበሉ ግለሰቦች ተያዙ።

1. ቶማስ ማናዬ ተበጀ
2. ሳሙኤል ኪዳኔ ሃይሌ
3. ፅዮን አበራ ጣፋ
4. ዳዊት መንግሰቱ
5. ሚኪያስ አውላቸው
የተባሉት ግለሰቦች በ2017 ዓ.ም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳዳር ክልል ውስጥ የግል ተበዳይ አቶ መሬት ስፋ 3825 ካ.ሜ ላይ የከብት ማደለቢያ አገልግሎት ለማዋል የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በመሰራት በሂደት ላይ ያለ መሆኑን በማወቅ እኛ የመሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ አመራር ሹፌር እና ፀሃፊ ነን ፤ አብረናቸዉ ነው የምንሰራዉ ካርታ በአስቸኳይ እናስጨርስልካለን በማለት ከላይ የተገለፀውን የገንዘብ መጠን ከተቀበሉ በኋላ ከአከባቢው በመሰወራቸው በቀረበ ጥቆማ መሰረት በፖሊስ ክትትል ተይዘው በ12/06/2018 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

‎በገጠር ኮሪደር መርሃግብር የአርሶ እና አርብቶ አደሮችን ሕይወት የመቀየር ሥራ በመላው ሀገራችን በመስፋፋት ላይ ይገኛል። በምስራቅ ወለጋ ዞን ላይ እየተሠራ ያለው የመደ ጃለላ ቀበሌ የገጠር...
19/02/2026

‎በገጠር ኮሪደር መርሃግብር የአርሶ እና አርብቶ አደሮችን ሕይወት የመቀየር ሥራ በመላው ሀገራችን በመስፋፋት ላይ ይገኛል። በምስራቅ ወለጋ ዞን ላይ እየተሠራ ያለው የመደ ጃለላ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር ልማት ሥራ፤ ዘመናዊ የፀሐይ ኃይል መጠቀሚያ፣ የባዮጋዝ ሥርዓት፣ የእንስሳት በረቶች፣ መጸዳጃ ክፍሎች እና የምድረ ግቢ አረንጓዴ ስፍራዎች ሥራን ያካተተ፤ ለማኅበረሰቡ ዘላቂ እና የከበረ አኗኗርን የፈጠረ ሥራ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

19/02/2026
19/02/2026
"ቀልጣፋ አገልግሎት ለተከበረው ነዋሪችን!"  የካቲት 11/2018  ዓ.ም​አራዳ  ወረዳ 5 ኮሙኒኬሽን​ዛሬ በወረዳ 05 አስተዳደር "የአገልግሎት ቀን" አስመልክቶ የአመራርና የሰራተኛው ዋነኛ...
18/02/2026

"ቀልጣፋ አገልግሎት ለተከበረው ነዋሪችን!"

የካቲት 11/2018 ዓ.ም
​አራዳ ወረዳ 5 ኮሙኒኬሽን


ዛሬ በወረዳ 05 አስተዳደር "የአገልግሎት ቀን" አስመልክቶ የአመራርና የሰራተኛው ዋነኛ ትኩረት የነዋሪዎችን ጥያቄዎች በአንድ ማዕከል መመለስ ላይ ሆኖ ውሏል።

የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ያላቸዉን ጥያቄዎች በማቅረብ በአጭር ደቂቃዎች ውስጥ መስተናገድ ችለዋል ። የወረዳው አመራሮችና ሠራተኞች በየጽ/ቤቱ በመገኘት፣ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የፐብሊክ ሰርቪስ እና የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በቦታዉ በመገኘት አረጋግጠዋል። ነዋሪዎችም ስለ አገልግሎት አሰጣጡ ያላቸውን ማንኛዉም ቅሬታና አስተያየት የሚያቀርቡበት ሁኔታም ተፈጥሯል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arada Woreda five communication office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share