Kolfe keranio Sub City Woreda 05 Prosperity Party Youth Wing

Kolfe keranio Sub City Woreda 05 Prosperity Party Youth Wing Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kolfe keranio Sub City Woreda 05 Prosperity Party Youth Wing, Political organisation, ኮልፌ ቀራንዮ ክፈለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር, Addis Ababa.

‹በሚተካው ደም የማይተካው ክቡር የሆነውን የሰው ህይወት እናድን› በሚል መሪ ሃሳብ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር  ወጣቶች  ክንፍ ከ ...
16/07/2026

‹በሚተካው ደም የማይተካው ክቡር የሆነውን የሰው ህይወት እናድን› በሚል መሪ ሃሳብ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ወጣቶች ክንፍ ከ ወረዳው ህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎፍቃድ ጽ/ቤትጋር በጋራ በመሆን የደም ልገሳ መርሀ ግብር አካሂዷል ።

የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ላይ ቋሚ ደም ለጋሾች፣ የወረዳው አስተባባሪ ኮሚቴ እና አመራሮች ፣ የወጣት ክንፍ አባላት እንዲሁም የወረዳው ነዋሪ የተሳተፉበት እንደሆነ እና ዋና ዓላማውም አሁን ላይ በተለያየ አደጋዎችና በህመም እንዲሁም በወሊድ ምክንያት የሚከሰት ደም መፍሰስ የእናቶች ሞት ለማስቀረት የደም ልገሳው መርሃ ግብሩ መዘጋጀቱ ተገልጿል ።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የወረዳው የወጣቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት ቃልኪዳን ዱፌራ
እንደተናገሩት ራሳቸውን ግባር ቀደም በማድረግ በፈቃደኝነት የተሞላ ደም መለገሳቸውን ጠቁመው ደም መለገስ የእናቶችን እና በተለያዩ አደጋ ተጋላጭ የሚሆኑ ዜጎችን መታደግ እና ህይወትን ማትረፍ መቻል በመሆኑ እጅግ ደስተኛ ሆነን ልንፈፅመው የሚገባ በጎ ተግባር ነው ብለዋል።

አክለውም ወጣት ቃልኪዳን ዱፌራ የደም ልገሳ ፕሮግራሙ ተሳታፊ ለሆኑ እና የስጦታዎች ሁሉ ውድ የሆነውን ደም የሠጡ ባለ ቅን ልቦችን በወረዳው ብልፅግና ፓርቲወጣቶች ክንፍ ስም ምስጋና ይድረሳችሁ ብለው በፈፀማችሁት ተግባር ሀገርና ህዝብ ያመሰግኗችኋልና ልትኮሩ ይገባችኋል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ወጣቶች በተመቻቸላቸው የስራ እድል በችግኝ ማፍላት ሥራ ውጤታማ መሆናቸውን ገለጹ፨  በኮልፌ ቀራንዩ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፖርቲ ወጣት ክንፍ አባላት በወረዳ 05 ቅጥር ግቢ ውስጥ የተደራጁ ...
05/07/2026

ወጣቶች በተመቻቸላቸው የስራ እድል በችግኝ ማፍላት ሥራ ውጤታማ መሆናቸውን ገለጹ፨

በኮልፌ ቀራንዩ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፖርቲ ወጣት ክንፍ አባላት በወረዳ 05 ቅጥር ግቢ ውስጥ የተደራጁ አባላት የችግኝ ማፍላት ሥራን በስፋት በመያዝ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

ወጣቶቹ በተለይ የደንና ችግኞችን በማፍላት በአካባቢው ያለውን የችግኝ ፍላጎት በማሟላት ላይ ይገኛሉ።

በወረዳው የተደራጁት እነዚህ ወጣቶች፣ ዘመናዊ የችግኝ ማፍያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ጥራታቸውን የጠበቁ ችግኞችን እያመረቱ መሆኑን ይናገራሉ። አሁን ላይም በተለያዩ የንግድ ተቋማትና በግለሰብ ገበያተኞች ዘንድ ተፈላጊነታቸው እየጨመረ መምጣቱን ለማወቅ ተችሏል።

ወጣቶቹ እንደሚሉት፣ በጋራ በመደራጀት የሚሠሩት ይህ የችግኝ ምርት ሥራ ለአካባቢ ጥበቃና ለደን ልማት ያለው ሚና የላቀ ነው። የተደራጁት ወጣቶች ለወደፊትም የችግኝ ማፍያ ጣቢያቸውን በማስፋትና የፍራፍሬ ዝርያዎችን በማበልጸግ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እየሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።

አያይዘውም የንብ እርባታው በክፍለ ከተማው ካሉ አረንጓዴ ልማቶችና የከተማ ግብርና ስራዎች ጋር ተቀናጅቶ በመከናወኑ፣ ለአካባቢው ስነ-ምህዳር መሻሻል የጎላ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

"ከድህነት ማዶ አሻግሮ ወደ ብልጽግና ጎዳና የሚያስገባን ትክክለኛ መንገድ፣ መለያየት ሳይሆን መተባበር ነው፤ መበታተን ሳይሆን መሰባሰብ" ነው"የመደመርመንገድ ገጽ 188
14/06/2026

"ከድህነት ማዶ አሻግሮ ወደ ብልጽግና ጎዳና የሚያስገባን ትክክለኛ መንገድ፣ መለያየት ሳይሆን መተባበር ነው፤ መበታተን ሳይሆን መሰባሰብ" ነው"

የመደመርመንገድ ገጽ 188

23/05/2026
23/05/2026
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፈን የክላስተር 4የህብረት አመራሮች የ2ተኛ መንፈቅ አመት የበጋ ተማሪዎች የማጠናከርያ ትምህርት አስጀመሩመርሃ ግብሩ የተገ...
19/02/2026

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፈን የክላስተር 4የህብረት አመራሮች የ2ተኛ መንፈቅ አመት የበጋ ተማሪዎች የማጠናከርያ ትምህርት አስጀመሩ

መርሃ ግብሩ የተገኙት የወጣት ክንፉ ሰብሳቢ ወጣት ቃልኪዳን ዱፌራ እንዳሉት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤት እንዲሻሻሉ እና በቀጣይ የትምህርት ደረጃ ዝግጁ እንዲሆኑ በማሰብ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። በፕሮግራሙ ውስጥ ዋና ዋና የትምህርት ክፍሎች በአስተማሪዎች እና በህብረት አመራሮች ድጋፍ እየተሰጡ መሆኑ ተጠቁሟል።

Address

ኮልፌ ቀራንዮ ክፈለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር
Addis Ababa

Telephone

+251962242818

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kolfe keranio Sub City Woreda 05 Prosperity Party Youth Wing posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share