Tiratu Beyene Biltu ጥራቱ በየነ ቢልቱ

Tiratu Beyene Biltu ጥራቱ በየነ ቢልቱ Mayor of Hawassa City
(1)

እኔም የመራጭነት ካርድ በወሰድኩበት ምርጫ ጣቢያ ተገኝቼ ድምፄን በመስጠት መርጫለሁ!
01/06/2026

እኔም የመራጭነት ካርድ በወሰድኩበት ምርጫ ጣቢያ ተገኝቼ ድምፄን በመስጠት መርጫለሁ!

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሌሊት በነቂስ በመውጣት ድምፃቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ::ምርጫው በከተማችን ሀዋሳ በተረጋጋ እና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል:: ህ...
01/06/2026

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሌሊት በነቂስ በመውጣት ድምፃቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ::

ምርጫው በከተማችን ሀዋሳ በተረጋጋ እና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል:: ህዝባችንም ዲሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ ይበጀኛል ያገለግለኛል የሚሉኦለውን ለመምረጥ ድምፁን እየሰጠ ይገኛል::

በከተማችን የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ 6 ፕሮጀክቶችን አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል!ዛሬ ለአገልግሎ የበቁ ፕሮጀክቶችን የክልላችን ፕረዝዳንት ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ ተገኝተው ያስመ...
27/05/2026

በከተማችን የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ 6 ፕሮጀክቶችን አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል!

ዛሬ ለአገልግሎ የበቁ ፕሮጀክቶችን የክልላችን ፕረዝዳንት ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ ተገኝተው ያስመረቅን ሲሆን በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የኢፌዲሪ ፕላንና ልማት ሚኒስትር ሚንስትር ክቡርት ዶ/ር ፍፁም አስፋና የክልልና የከተማ ከፍተኛ ሀላፊዎች ተገኝተዋል::

ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በገባነው ቃል መሰረት ዛሬ ለምረቃ የበቁት G+3ትምህርት ቤት፣ G+3 በታቦር ገቢዎች ህንፃ፣ G+3 የሚሊኒየም የጤና ማስፋፊያ ህንፃ፤ G+1 የፍርድ ቤት፤ G+2 የሀዋሳ ከተማ የአንድ ማዕከል አገልግሎት( መሶብ) እና G+8 የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ይገኙበታል ።

እነዚህ ፕሮጀክቶች ከተማች ውስጥ አዳዲስ የተጀመሩ ወይም ከዚህ በፊት ተጀምረዉ የዘገዩ ፕሮጀክቶችን በአዲስ የፕሮጀክት ክትትል እሳቤ እና በ24/7 የስራ ባህል በመስራት በፍጥነትና በጥራት የተጠናቀቁ ናቸው::

ፕሮጀክቶቹ ከጅምር እስከ መጠናቀቅ ሀሳብ በማመንጨት; ግንባታ በማስጀመርና በመከታተልና ለፍፃሚ እንዲበቃ ለመራችሁ፣ ላአስተባበሩ፣ ለገነቡ፣ ለአማከሩና ለደገፉ አካላት ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ::

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል-ዓድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ ልባዊ ምኞቴን በማቅረብ በዓሉ የሰላም የደስታና የፍቅር ...
27/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል-ዓድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ ልባዊ ምኞቴን በማቅረብ በዓሉ የሰላም የደስታና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ዒድ ሙባረክ!

"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል በሀዋሳ የብልፅግና ፓርቲን የሚደግፍ ደማቅ ህዝባዊ ሰልፍ በዋና ዋና ጎዳናዎችና በሀዋሳ ስቴዲየም  ላይ እየተካሄደ ይገኛል!በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ብልፅ...
26/05/2026

"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል በሀዋሳ የብልፅግና ፓርቲን የሚደግፍ ደማቅ ህዝባዊ ሰልፍ በዋና ዋና ጎዳናዎችና በሀዋሳ ስቴዲየም ላይ እየተካሄደ ይገኛል!

በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ብልፅግና ፓርቲያችን ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም መስኮች ያስመዘገባቸውን ድሎች ለማስቀጠል እና ተጨማሪ ድሎችን ለማስመዝገብ የስንዴ ነዶ ምልክቱ በማድረግ በምርጫው ይወዳደራል!

መላው ህዝባችንና የብልፅግና ፓርቲ ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶ በመምረጥ ኢትዮጵያን የብልፅግና ተምሳሌት ሀገር ለማድረግ ከያዝነው ራዕይ ጎን እንድትቆሙ ጥሪዬን አቀርባለሁ::

የዛሬው የቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ ደማቅ ሆኖ እንዲካሄድ ያደረጋችሁ የከተማችን ነዋሪዎች; የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎችን እጅግ አድርገን እያመሰገንኩ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ይበልጥ አጠናክረን እንደምንቀጥል ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ!

ብልፅግናን ይምረጡ!

13/05/2026
አዲሱ የሀዋሳ የኮሪደር ልማት - ከሳውዝ ስታር- መናኽሪያ- ሼል ፣  - ከሳውዝ ስታር - እርሻ ጣቢያ፣  - ከሱሙዳ -ሎጊታን እና - ከጥቁር ውሃ - ሳውዝስፕሪንግ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ...
11/05/2026

አዲሱ የሀዋሳ የኮሪደር ልማት
- ከሳውዝ ስታር- መናኽሪያ- ሼል ፣
- ከሳውዝ ስታር - እርሻ ጣቢያ፣
- ከሱሙዳ -ሎጊታን እና
- ከጥቁር ውሃ - ሳውዝስፕሪንግ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ስራው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው!

ሀዋሳ-የፍቅር ከተማ!

30/04/2026
በኮሪደር ልማት አምረው የተሰሩት የከተማችን ሀዋሳ ጎዳናዎች ታላላቅ ስፓርታዊ ውድድሮች እና ኩነቶችን ለማስተናገድ ተመራጭ ሆነዋል:: ዛሬ ማለዳ "ለሀዋሳ ከፍታ እንሩጥ" በሚል ከኮሚርሻል ኖሚ...
26/04/2026

በኮሪደር ልማት አምረው የተሰሩት የከተማችን ሀዋሳ ጎዳናዎች ታላላቅ ስፓርታዊ ውድድሮች እና ኩነቶችን ለማስተናገድ ተመራጭ ሆነዋል::

ዛሬ ማለዳ "ለሀዋሳ ከፍታ እንሩጥ" በሚል ከኮሚርሻል ኖሚስ ጋር በጋራ በተዘጋጀው የሩጫ ውድድር ላይ በርካታ የከተማችን ነዋሪዎች የተሳተፉበት ደማቅ ውድድር አካሄደናል::

ከተማችን ሀዋሳ በየሳምንቱ አዳዲስ ኩነቶችን ማስተናገዷን ቀጥላለች!

26/04/2026

"ሀዋሳ የመዝናኛና የደስታ፣ የፍቅርና የውበት፣ የዓሳና የቡርሳሜ ከተማ ብቻ ሳትሆን ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ብርሃን የሚያመነጭ በአፍሪካ ትልቁ የሶላር ሴል የሚመረትባት ከተማ ሆናለች!"

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tiratu Beyene Biltu ጥራቱ በየነ ቢልቱ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share