15/06/2026
የልደታ ጤና ጣቢያ ባካሄደው የመጀመሪያ ቀዶ ጥገና አገልግሎት አንዲት ወላድ እናትን በተሳካ ሁኔታ ማዋለድ እንደቻለ አስታወቀ።
ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰኔ 7/2018 ዓ.ም
በልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የልደታ ጤና ጣቢያ ዛሬ ባካሄደው የመጀመሪያ ቀዶ ጥገና አገልግሎት አንዲት ወላድ እናትን በሰላም ማዋለድ በመቻሉ ወላዷንም እንኳን በሰላም ተገላገልሽ፣ ባለሙያዎችም አገልግሎቱን እንኳን በስኬት ፈጸማችሁ በማለት ለወረዳው ማህበረሰብ የእንኳን ደስ አላችሁ ምኞቱን የክፍለ ከተማው አስተዳደር ገልጿል።
የክፍለ ከተማው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን በየነ ስለተጀመረው አገልግሎት እንደገለጹት የቀዶ ጥገና ባለሙያዎቹ ያላቸውን እውቀት ተጠቅመው ወላድ እናትን በብቃት ማዋለድ በመቻላቸው ሊመሰገኑ እንደሚገባ ገልጸዋል።
አክለውም እስከ አሁን ድረስ ጤና ጣቢያዎች በርካታ ወላዶች በሰላም ማዋለድ መቻላቸው እና አሁንም በልደታ ጤና ጣቢያ በአዲስ መልክ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩ የአገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በመጨረሻም ይህ የቀዶ ጥገና አገልግሎት መጀመሩ፣ ከዚህ በፊት አንዳንድ ወላድ እናቶች በሪፈር ምክንንያት ወደ ሆስፒታል ሄደው የሚገጥማቸው ድካምና እንግልት በማሰቀረት ወላድ እናቶችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል በመሆኑ ሁላችንም ደስ ብሎናል፤ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።