አለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ሀይሎች ጓድ

አለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ሀይሎች ጓድ "..የኢትዮጵያ ጀግኖች ስማቸው ስነሳ
ከሩቅ ያስፈራሉ እንደ ዱር አንበሳ.." However, either we are ready to turn left or right, it is our turns.

ሰላም አስከባሪ ሀይሎች፦ ሰላም ፈላጊዎች እና ሰላም የሚገባቸው ዜጎች ፣ የሰላም ተጠያቂዎች እና ሀላፊዎች ፣ በብጥብጥ ሳይሆን በብቃት የምአምኑ ብቁ ተወዳዳሪዎች ናቸው።
ሰላማችንን እንጠብቃለን እንጂ ሰላምን ከሌሎች አንጠብቅም።
ሰላማችንን በሰለማዊ መንገድ እናደርግ ፣ እናስተዳድር ፣ እንምራ! Well Come to Global Peacekeeping Forces Alliance- "Africa" ;

Baga gara Jaallee Humnoota Kabachiisa Nagaa Idil Addunyaa - "Afrikaa" Naga'aan Dhuftan! ;

እንኳን ወደ አለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ሀይሎች ጓድ- "አፍርካ" በሰላም መጣችሁ! "ግዜያችሁም ዜጋችሁም ከምጎዳ ስትላፉ
ጎጆያችሁ እናታችሁ ይሻላል ስትኖሩም ስታርፉ
ደሰሰች ደከመች ብላችሁ ቀይ መስመሩን ሳታልፉ።"

Whether they have been abolishing or developing, our elders have done what has been seemed to be good to them. But, as we are 21st century generation, we have to eager to plan and do what could be able to match with our age. That is only peace making , peace managing, and peace leading. To do so we have so many youth force and resources. The only needed is facilitators and our elders permission to change and accept changes. As a result, Global Peacekeeping Forces Alliance plan to do what might not be done by our world military organizations leaded by united nation - NATO and the like if and only if we are true worldwide patriots that never escape and cheat people, our world rule and regulations as well as our world majority rule and minority right are the matter, and our world distraction and developments also concerns us. Let us make ,manage and lead our Peace PEACEFULLY!

የፅናት ቀን የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ለሀገር ሰላምና ልማት እያበረከቱ ያሉትን አስተዋጽኦ የሚያሳይ ነው።     ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጳጉሜ 02 ቀን 201...
07/09/2026

የፅናት ቀን የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ለሀገር ሰላምና ልማት እያበረከቱ ያሉትን አስተዋጽኦ የሚያሳይ ነው።
ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም

የፅናት ቀን የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ለሀገር ሰላም፣ ደህንነትና ልማት እያበረከቱ ያሉትን አስተዋጽኦ ለመላው ሕዝብ ለማስተዋወቅ የሚያስችል አጋጣሚ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታ ገለጹ።

ምክትል ኮሚሽነሩ የፅናት ቀንን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ዝግጅቱ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አስተዳደር፣ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አስተዳደር እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በጋራ የሚያዘጋጁት መሆኑን ጠቁመዋል።

ሀገራችን በጀመረችው የማንሰራራት ጉዞ የዕድገትና የልማት ግቦችን ለማሳካት ሰላምና ደህንነት መሠረታዊ ጉዳይ በመሆኑ፣ የፀጥታ ተቋማት የሚወጡት ሚና ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በጠንካራ ሕዝባዊ መሠረት ላይ ተገንብቶ ከዘመኑ ጋር የዘመነ አቅም በመገንባት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት፣ ብሄራዊ ጥቅምና አንድነት ለመጠበቅ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።

ሠራዊቱ የአየርና የየብስ ግዛትን በመጠበቅ፣ ሀገረ-መንግሥትንና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከሚያጋጥሙ ስጋቶች በመከላከል እንዲሁም በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች በመሳተፍ የሀገሪቱን ስም እያስጠበቀ መሆኑንም አክለዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በበኩሉ የሕግ የበላይነትንና ሰላምን በማስፈን፣ ዓለም አቀፍና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በመከላከል፣ ወሳኝ ተቋማትንና የቱሪዝም መዳረሻዎችን በመጠበቅ ለሀገራዊ ሰላምና ፀጥታ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ ጠቅሰዋል።

በዘመናዊው የፀጥታ ሥራ የመረጃ፣ የሳይበር ደህንነትና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሚና እየጨመረ መምጣቱን ያመለከቱት ምክትል ኮሚሽነሩ፣ የሀገሪቱን ወሳኝ ዲጂታል መሠረተ ልማቶች ከሳይበር ጥቃቶች መጠበቅና የዲጂታል ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የዘመኑ የፀጥታ ሥራ ዋና አካላት መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተለይም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስንና ሌሎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ከፀጥታ ሥራ ጋር በማስተሳሰር የሀገሪቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት፣ የፀጥታ ሥራን ለማዘመንና ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚደረገው ሥራ መጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የፅናት ቀን በዚህ መልኩ የፀጥታ ተቋማት የሚያከናውኗቸውን ሥራዎችና የሚያስመዘግቧቸውን ውጤቶች ለሕዝብ ለማስተዋወቅ፣ የተቋማትን ቅንጅት ለማጠናከርና ለሀገራዊ ሰላምና ልማት የሚያበረክቱትን ድርሻ ለማጉላት ጠቃሚ መድረክ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታ ገልጸዋል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ አበረ አየነው

ሳላም ለአለማችን ይሁን!
ሰላማችንን በሰለማዊ መንገድ እናደርግ ፣ እናስተዳድር ፣ እንምረ!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

https://dfmc.mod.gov.et/
https://www.facebook.com/EthioPolice.et
https://www.facebook.com/Ethiopeaces

ለኩሩ ህዝብ፤ ጀግና ሠራዊት  የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም  ህዝብ የሀገር መሠረት ነው፤ ሠራዊት ደግሞ የዚያን ሀገር ሰላም፣ ሉዓላዊነትና ደህንነት የሚጠብቅ ጋሻ ...
05/09/2026

ለኩሩ ህዝብ፤ ጀግና ሠራዊት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

ህዝብ የሀገር መሠረት ነው፤ ሠራዊት ደግሞ የዚያን ሀገር ሰላም፣ ሉዓላዊነትና ደህንነት የሚጠብቅ ጋሻ ነው። ሁለቱ በእምነትና በመተማመን ሲተሳሰሩ የሚፈጠረው ኃይል የሀገርን ጽናት ያጠናክራል። ህዝቡ የጦር ልጆቹን እንደ የራሱ አካል ሲቆጥር፣ ወታደሩም የሚጠብቀው የራሱን ቤትና ህዝብ መሆኑን ሲያምን ትስስሩ የበለጠ ይጠናከራል።

ጀግንነት የሚለካው በውጊያ ጊዜ ብቻ አይደለም። የተሰጠንን ቃል መጠበቅ፣ አደራን በታማኝነት መወጣት፣ ችግር ሲመጣ ኃላፊነትን ሳንሸሽ መቀበል የጀግንነት መገለጫዎች ናቸው። ወታደር የሚለየውም በዚህ አደራ ነው፤ ራሱን ከሀገር ጥቅም በታች አስቀምጦ ለሌሎች ሰላም የሚቆምበት መንፈስ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ በተለያዩ ዘመናት በፈተና ውስጥ ያሳለፈው ጉዞ የጽናትና የመስዋዕትነት ትምህርት ትቶ አልፏል። የሀገር ክብር ሲፈተን ህዝብና ወታደር በአንድ ልብ መቆም መቻላቸው በታሪክ የተመሰከረለት ነው። የዚህ ትስስር ዋጋ የሚታየው በአስቸጋሪ ወቅት ነው፤ ያኔ የተከማቸ እምነት ወደ ተግባራዊ ኃይል ይቀየራል።

የዘመናዊ ሠራዊት ብቃት በመሣሪያ ብዛት ብቻ አይወሰንም። የሙያ ብቃት፣ ዲሲፕሊን፣ ዕውቀት፣ ፈጣን ውሳኔና ተጠያቂነት የጦር ኃይልን የሚያጠናክሩ መሠረታዊ እሴቶች ናቸው። ከዚህ በላይ ግን የሠራዊት ጥንካሬ ከሚጠብቀው ህዝብ ጋር ባለው መተማመን ይጠናከራል።

ይህ እምነት በቃል ብቻ የሚገነባ አይደለም። ወታደሩ በተሰማራበት ቦታ ሕግንና ሥርዓትን ሲያከብር፣ ህዝቡን በክብር ሲያገለግል፣ የሰው ልጅ ክብርን ሲጠብቅ እምነቱን በተግባር ያረጋግጣል። ህዝቡም ለሀገር ጉዳይ በኃላፊነት ሲሳተፍና ለሠራዊቱ የሚገባውን ድጋፍ ሲያደርግ ይህንኑ እምነት ይመልሳል።

ዛሬ የሚጠበቀው ከትውልድ የተላለፈውን አደራ በአዲስ ብቃት ማስቀጠል ነው። ሠራዊቱ በሙያዊ ዝግጁነትና በሥነ-ምግባር እየጠነከረ ሲሄድ፣ ህዝቡም ለሀገር ጉዳይ ያለውን ተሳትፎ ማጠናከር ይገባዋል። የጋራ ጥቅም ከግል ፍላጎት በላይ ሲቀመጥ የሀገር አቅም ይሰፋል።

ለኩሩ ህዝብ ጀግና ሠራዊት ያስፈልገዋል፤ ጀግና ሠራዊትም ከህዝቡ እምነት ይጠነክራል። ይህ የጋራ መተማመን ሲጸና የሀገር ጋሻ ይበረታል፤ የትውልድ ተስፋም ይለመልማል።

የዛሬ ትውልድ የተረከበውን ታሪክ በትጋት ማስቀጠል፣ የተሰጠውን አደራ በታማኝነት መወጣትና ለሚቀጥለው ትውልድ የተሻለች ሀገር ማስረከብ አለበት። ምክንያቱም የሀገር ጽናት የሚገነባው በአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን፣ በህዝብና በሠራዊት የጋራ አደራ ነው።

ለኩሩ ህዝብ፤ ጀግና ሠራዊት።ለጀግና ሠራዊት፤ የማይሰበር እምነት። ለጋራ አደራ፤ የጸናች ሀገር።

በፍፁም ከተማ

ሳላም ለአለማችን ይሁን!
ሰላማችንን በሰለማዊ መንገድ እናደርግ ፣ እናስተዳድር ፣ እንምረ!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

https://dfmc.mod.gov.et/
https://www.facebook.com/EthioPolice.et
https://www.facebook.com/Ethiopeaces

መከላከያ ሚኒስቴር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የመኖሪያ መንደር ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ አስቀመጠ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 10 ቀን 2018 ዓ.ም‎‎የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክ...
05/09/2026

መከላከያ ሚኒስቴር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የመኖሪያ መንደር ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ አስቀመጠ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 10 ቀን 2018 ዓ.ም

‎የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ተገኝተው ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር በጋራ በመሆን ሞዴል ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ግንባታ መሰረት ድንጋይ አስቀምጥዋል።

‎የዚህ ተግባር ዋና አላማ እንደ ሀገር የተቀመጠውን የክረምት የበጎ ፈቃደኝነት ተግባር እውን ለማድረግና የህዝቡን ኑሮ ቀላል ማድረግ ነው ያሉት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ መከላከያ ሚኒስቴር በአርዓያነት ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር በአጭር ጊዜ ገንብቶ ያስረክባል ብለዋል።

‎የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በህዝቦች መካከል አብሮ የዘለቀውን የመደጋገፍና የመተሳሰብ ባህል ተላብሶ አቅመ ደካሞችን በአስፈላጊ ወቅት በማገዝ ከህዝብ ጋር በጋራ የኖረ ሰራዊት ነው ያሉት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ይሄኛውም ተግባር እንደተቋም ሰላምን ከመጠበቅና የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ ባለፈ ሰራዊቱ የመልካም እሴት ባለቤትነቱን ያሳየበት መሆኑን ገልፀዋል።

‎ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በከፋ ዞን ሁለት ወረዳዎች ላይ በተያዘው እቅድ መሰረት አስር ዘመናዊ መንደሮችንና ከዚያም በላይ በሚቀመጥ አቅጣጫ መሰረት ሰርቶ ለማስረከብ በየጊዜው ትኩረት ይሰጣል። በዚህም በመከታተልና ከግብ በማድረስ ሰራዊቱ በሀላፊነት የሚያጠናቅቀው መሆኑን ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ተናግረዋል።

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ በክረምት ወራት መንግስት ካስቀመጣቸው ግቦች ዜጋ ተኮር የበጎ ፍቃደኝነት ስራ በመሆኑ ድጋፍ የሚሹ አረጋዊያንን ማገዝ ፣ ወላጅ የሌላቸውን ህፃናት መንከባከብና መደገፍ በክልሉ በትኩረት እየተሰራበት ሲሆን የገጠር ሞደል መንደር የበርካቶችን ችግር የሚፈታ መፍትሔ ሆኗል ብለዋል።

‎መከላከያ ሚኒስቴር ያለበትን ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታ ተቋቁሞ ሰራዊቱ በሚከፍለው ወደር የለሽ ውለታና ተጋድሎ ሳይበቃ በዚህ በጎ ተግባር በመሳተፍ ያሳየው ቅንነትና አለኝታነት የህዝብ ልጅ መሆኑን ህዝቡ እንዲረዳ ያደረገ ደግነት መሆኑን ያነሱት ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ድጋፍ የሀገርንና የመንግስትን እሳቤ እውን ለማድረግ በመሆኑ የክልሉ መስተዳዲር ከጎኑ መሆኑን አረጋግጠዋል።

‎በእለቱ በመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር የተመራው ልዑክ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች አምስት ሽህ ደርዘን ደብተርና እስክብሪቶ ለከፋ ዞን ያበረከቱ ሲሆን አስር ሽህ ደርዘን ደብተርና እስክርቢቶ ለማስረከብ ቃል ገብተዋል። ቡድኑ በተጨማሪም ችግኝ የተከለ ሲሆን በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የመንግስት ተቋማትን ጎብኝቷል።

‎ዘጋቢ መሀመድ አህመድ
‎ፎቶግራፍ ሚኪያስ እስክንድር

ሳላም ለአለማችን ይሁን!
ሰላማችንን በሰለማዊ መንገድ እናደርግ ፣ እናስተዳድር ፣ እንምረ!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

https://dfmc.mod.gov.et/
https://www.facebook.com/EthioPolice.et
https://www.facebook.com/Ethiopeaces

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ያለው ከፍተኛ ሙያዊ ብቃት በአፍሪካ ካሉ የፀጥታ ኃይሎች መካከል ቀዳሚ ያደርገዋል - ቲቦር ናጅየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ምየመከላከያ ...
05/09/2026

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ያለው ከፍተኛ ሙያዊ ብቃት በአፍሪካ ካሉ የፀጥታ ኃይሎች መካከል ቀዳሚ ያደርገዋል - ቲቦር ናጅ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

የመከላከያ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ የተመራ ከፍተኛ ወታደራዊ ኃላፊዎችን ያካተተ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በቅርቡ በአሜሪካ ጉብኝት በማድረግ በፔንታጎን ከአቻዎቻቸው እና ሌሎች ከፍተኛ የአሜሪካ ጦር ሚኒስቴር አመራሮች ጋር የሁለትዮሽ የጋራ ምክክሮች አድርገዋል።

በዚህም በፔንታጎን የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ረዳት የመከላከያ ሚኒስትር ብራያን ጄ. ኤሊስ ጋር በጋራ በተመራ ምክክር የሁለቱን ሀገራት ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ትብብሮችን ወደ አዲስና የላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር ተግባብተዋል።

የቀድሞው የአሜሪካ አፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናጅ በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መካከል የተጀመረውን ወታደራዊ ትብብር ስትራቴጂካዊ ፋይዳ ያለው መሆኑን ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል።

ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር የሚደረግ ትብብር ከሁለቱ ወገኖች አልፎም ለቀጣናው ዘላቂ ሰላም የሚበጅ ውጤት እንደሚያስገኝ ተናግረዋል።

ቲቦር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ያለውን ከፍተኛ ሙያዊ ብቃት ያደነቁ ሲሆን ይህ ብቃቱ ደግሞ በአፍሪካ ካሉ የፀጥታ ኃይሎች መካከል ቀዳሚ እንደሚያደርገው አመልክተዋል።

የሰራዊቱን ጥንካሬም ከጥልቅ ስነ ምግባር እና ከዘመን ተሻጋሪ ወታደራዊ ታሪክ ጋር አያይዘው አንስተዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ያለው ሙያዊ ስነ ምግባር እና ታሪክ ሁልጊዜም በከፍተኛ የሙያ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ አድርጎታል ነው ያሉት።

ይህ ሰራዊት የአድዋን ታሪክ የሰሩ አርበኞችን ጀግንነት የወረሰ ነው ያሉት ናጅ፤ የኢትዮጵያውያን የውጊያ መንፈስ እና ለሀገር የመዋጋት ፍላጎት በደማቸው ውስጥ ያለ መሆኑን አመልክተዋል።

ይህ ተቋማዊ ብቃት አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ቀጣይነት ያለው ግንኙነትና አጋርነት ለመፍጠር ላለት ፍላጎት እጅግ የጎላ ፋይዳ እንዳለው አመልክተዋል።

አሜሪካ ጥቅሟን ለማስከበር ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ትብብር መፍጠሯ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ነው የተናገሩት።

የተረጋጋ እና የበለጸገ የአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካን ስትራቴጂካዊ ጥቅሞች እንደሚያስጠብቅም አፅንኦት ሰጥተዋል።

በአጠቃላይ ጥልቅ የሆነው የአሜሪካና ኢትዮጵያ ወታደራዊና ስትራቴጂካዊ ትብብር ሁሉንም ወገኖች አሸናፊ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።

ሳላም ለአለማችን ይሁን!
ሰላማችንን በሰለማዊ መንገድ እናደርግ ፣ እናስተዳድር ፣ እንምረ!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

https://dfmc.mod.gov.et/
https://www.facebook.com/EthioPolice.et
https://www.facebook.com/Ethiopeaces

በሁርሶ እጩ መኮንን ማሠልጠኛ ለአሰልጣኞችና ሰልጣኞች ሥልጠና ተሰጠ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ምበሁርሶ እጩ መኮንን ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ለሚገኙ አሰልጣኞች እና...
05/09/2026

በሁርሶ እጩ መኮንን ማሠልጠኛ ለአሰልጣኞችና ሰልጣኞች ሥልጠና ተሰጠ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

በሁርሶ እጩ መኮንን ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ለሚገኙ አሰልጣኞች እና ሰልጣኝ የእጩ መኮንኖች በሃገረ መንግስት ምስረታና በኢትዮጵያ ወታደራዊ ታሪክ ፤የዘመኑ የወታደራዊ ስነ ልቦና ጦርነት የሳይበር ደህንነት፤ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሠጥቷል።

የዘመኑ የስነ-ልቦና ጦርነት በሚል ርዕስ ትምህርት የሰጡት በመከላከያ የሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ የሰው ሃይል ምዘና መረጣ ኃላፊ ኮሎኔል ታምራት ዘርፉ የዘመኑ ጦርነት ከጦር ሜዳ ባለፈ በሰዎች አእምሮ እና ስነ-ልቦና ላይ እንዴት እንደሚካሄድ፣ እንዲሁም የመረጃ ፍሰትን በመጠቀም ተለዋዋጭ በሆኑ የውጊያ ውሎዎች ውስጥ ጠንካራ የስነ ልቦና ዝግጁነት ማዳበር የውጊያ ብቃትን፣ የውሳኔ ሰጪነት ችሎታንና የወታደራዊ አመራር ጥበብን ለማጎልበት ዋና መሰረት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የሃገረ መንግስት ምስረታና የኢትዮጵያ ወታደራዊ ታሪክ በሚል ርዕስ ትምህርት የሰጡት በመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ምክትል አዛዥ ለስርዓተ ትምህርት ዕድገት ጥናትና ምርምር ዲን ዶክተር ደምሌ ሞላው የሃገረ መንግስት ግንባታ ታሪካዊ ሂደትና የኢትዮጵያ ወታደራዊ ታሪክ አመሰራረትና የነፃነት የማስከበር ጉዞ የነፃነትና የጀግንነት ምሳሌ መሆኑን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር አያይዘው በጀግንነት እሴቶችና በሠራዊቱ ታሪካዊ ሚና ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የሰው ሰራሽ አስተውሎት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት የሰጡት በመከላከያ ሳይበር ማዕከል የሳይበር መከላከል መምሪያ ሃላፊ ኮሎኔል ንጋቱ በቀለ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳብና ወቅታዊ አስፈላጊነቱ ላይ በውጊያ ውሳኔ አሰጣጥ፣ በቅድመ መረጃ ስብሰባ፣ በመረጃ ትንተና ላይ የሚያመጣውን አብዮታዊ ለውጥ በተመለከተ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።

የሳይበር ደህንነት ትምህርት የሰጡት ሻለቃ ይርጋለም ሀይሉ፣ በቴክኖሎጂ በረቀቀው የኢንፎርሜሽን ዘመን የሳይበር ምህዳር አምስተኛው የጦርነት ሜዳ በመሆኑ፤ የወታደራዊ መረጃ መረቦችን መከላከልና ሊሰነዘሩ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን ቀድሞ ማክሸፍ የሃገርን ደህንነት ለማረጋገጥ የማያወላውል ቅድመ ሁኔታ የሚተነትን መኮንን መገንባት አሰፋላጊ እንደሆነ አሥረድተዋል።

ዘጋቢ ውብሊቀር ደሳለው
ፎቶግራፍ ታማራት ጌቱ

ሳላም ለአለማችን ይሁን!
ሰላማችንን በሰለማዊ መንገድ እናደርግ ፣ እናስተዳድር ፣ እንምረ!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

https://dfmc.mod.gov.et/
https://www.facebook.com/EthioPolice.et
https://www.facebook.com/Ethiopeaces

ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ መከላከያ እንደ ተቋም ተሸላሚ ሆኗል፡፡የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ምየመከላከያ ስነ-ምግባር መከታተያ መምሪያ ከፌደራል ስ...
04/09/2026

ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ መከላከያ እንደ ተቋም ተሸላሚ ሆኗል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

የመከላከያ ስነ-ምግባር መከታተያ መምሪያ ከፌደራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከነሃሴ 27 እስከ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለሶስት ቀናት ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ እቅድ እና ሪፖርት ዝግጅት ክትትል ዳይሬክተር ኮሎኔል ፈይሳ ታደሰ መከላከያ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ላሳየው ትጋት እና ቁርጠኝነት በሀገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጅ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል በአንድ ወቅት ብቻ ተሰርቶ የሚጠናቀቅ የአጭር ጊዜ ተግባር ባለመሆኑ በየጊዜው በአባላቱ ዘንድ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ በቅንጅት እና በመዋቅር ተደራጅቶ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ ስልጠናው የሀብት ብክነትን ለመቀነስ እና አበላቱን በስነ-ምግባር ለመገንባት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

የመከላከያ ስነ-ምግባር መከታተያ መምሪያ ሃላፊ ተወካይ ሌተናል ኮሎኔል ሲሳይ ተስፋሁን በበኩላቸው ተቋማችን መከላከያ ከተሰጠው የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ እና ሀገርን የመጠበቅ ሃለፊነት አንፃር ስነ-ምግባር፣ የዓላማ ፅናት እና ዲሲፕሊን የማይታጠፉ መሰረቶቻችን ናቸው ብለዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የፌዴራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከፍተኛ የስልጠና ባለሙያዎች አቶ የኋላሸት ደሳለኝ እና ወይዘሮ ሜሮን ዳምጤ ስልጠናው በሰልጣኞች ላይ ተጨባጭ የእውቀት፣ የክህሎት እና የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

መከላከያ ህዝብን እና ሀገርን በነፍሱ የሚያገልግል ሰራዊትን የሚመራ ተቋም በመሆኑ ጠላትን በጥይት ፊት-ለፊት ከመፋለም ባልተናነሳ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መጋፈጥ እንዲችል ስልጠናው የጎላ ሚና አለው ብለዋል፡፡

ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
ፎቶግራፍ እፀገነት ዴቢሳ

ሳላም ለአለማችን ይሁን!
ሰላማችንን በሰለማዊ መንገድ እናደርግ ፣ እናስተዳድር ፣ እንምረ!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

https://dfmc.mod.gov.et/
https://www.facebook.com/EthioPolice.et
https://www.facebook.com/Ethiopeaces

የኮማንዶ ክፍለ ጦር በማንኛውም ጊዜ የሚሰጠውን ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን አሥታወቀ፡፡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የኮማንዶ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ሰለሞን ...
02/09/2026

የኮማንዶ ክፍለ ጦር በማንኛውም ጊዜ የሚሰጠውን ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን አሥታወቀ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም

የኮማንዶ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ሰለሞን ፀጋዬ ክፍለ ጦሩ በቅርቡ የጥፋት ኃይሎችን በመመንጠር ያስመዘገበው ታላቅ ድል፣ የሀገርን ሰላምና ሉዓላዊነት ለማስከበር ያለውን ፅናት ያሳየበት መሆኑን ገልፀው ይህ ውጤቱ ወታደራዊ ግዳጅን በስኬት መወጣት ብቻ ሳይሆን፣ የአባላቱን የላቀ የውጊያ ጥበብ በሚገባ ያሳዬ ነው ብለዋል።

ክፍለ ጦሩ እጅግ አስቸጋሪ በሆኑ መልክዓ ምድር ውስጥ የጠላትን የጥፋት መረብ በመስበር እና በመበጣጠስ ረገድ የነበረው ሚና የተጣለበትን ሀገራዊ ግዳጅ የመፈፀም አቅሙን ያረጋገጠበት ነው ያሉት አዛዡ ይህ በውጤት የታጀበ ስምሪት፣ የክፍለጦሩ ሠራዊት በአካልና በታክቲክ የደረሰበትን ከፍተኛ የብቃት ደረጃ ያሳየ እንደሆነ ገልፀዋል።

ኮሎኔል ሰለሞን ፀጋዬ የክፍለጦሩ ሠራዊት ወትሮ ዝግጁነት ባረጋገጠበት ወቅት የክፍለ ጦሩ አስደማሚ ድልና ለአፍታም ቢሆን የማይላላው ወታደራዊ ዝግጁነት አስተማማኝ የሀገር ደህንነት ዋስትና መሆኑን በድጋሚ ያረጋገጠበት ደማቅ ገፅታ እንደሆነ አብራርተዋል፡ዘገባዉ የክፍለ ጦር የሠራዊት ስነ ልቦና ግንባታ ነው

ሳላም ለአለማችን ይሁን!
ሰላማችንን በሰለማዊ መንገድ እናደርግ ፣ እናስተዳድር ፣ እንምረ!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

https://dfmc.mod.gov.et/
https://www.facebook.com/EthioPolice.et
https://www.facebook.com/Ethiopeaces

የሎጀስቲክ ዝግጁነት የውጊያ ቁልፍ አቅም መሆኑ ተገለፀየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የሰሜን ምሰራቅ ዕዝ ሎጀስቲክ ክፍል በግዳጅ ቀጣና በመዘዋወር የኮሩን ሎጀስቲካዊ...
01/09/2026

የሎጀስቲክ ዝግጁነት የውጊያ ቁልፍ አቅም መሆኑ ተገለፀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም

የሰሜን ምሰራቅ ዕዝ ሎጀስቲክ ክፍል በግዳጅ ቀጣና በመዘዋወር የኮሩን ሎጀስቲካዊ ዝግጁነት እና የውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ብቃት አረጋግጧል።

ቡድኑ በዕዙ ስር ከሚገኝ የአንድ ኮር ክፍለጦሮች የግዳጅ ቀጣና በመገኘት ከሠራዊቱ የነብስ-ወከፍ የውጊያ ቁሳቁሶች ጀምሮ በውጊያ ውስጥ ወሳኝ የሆኑ ሎጀስቲካዊ አቅርቦት እና የውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ዝግጁነቶችን በፍተሻ አረጋግጧል።

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ሎጀስቲክ ኃላፊ ኮሎኔል ነጋሽ እሬ የኮሩ የሠራዊት ክፍሎች በማንኛውም ሁኔታ የሚገጥማቸውን ጠላት ተዋግተው ማሽነፍ የሚያስችል አስተማማኝ የሎጀስቲካዊ አቅርቦት እና የውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሙሉ ዝግጁነት እንዳላቸው በፍተሻ መረጋገጡን ገልፀዋል።

የታጠቀውን የውጊያ ማቴሪያል በአግባቡ በመያዝ የተሰጠውን ህዝባዊ አደራ በታላቅ ኃላፊነት መፈፀም የሚችል ጠንካራ ሠራዊት መገንባቱን የጠቀሱት ኃላፊው የውጊያ ቁልፍ አቅም የሆነው ሎጀስቲካዊ ዝግጁነት መረጋገጡ ለግዳጅ ስኬት ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል ።

ሠራዊታችን በቡድንም ይሁን በነፍስ ወከፍ ደረጃ የሚታጠቃቸው በርካታ ውድ እና ዘመናዊ ትጥቆች ያሉት መሆኑን አውስተው እነዚህን ትጥቆች በእንክብካቤ በመያዝ ዘውትር የውጊያ ዝግጁነታችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል ሲሉ አሳስበዋል።

የኮሩ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ኮሎኔል ፈንታሁን አሊ በበኩላቸው ኮሩ አሁን ያለበትን ወታደራዊ ፣ ስነ- ልቦናዊ እና ሎጀስቲካዊ ዝግጁነት ደረጃ አጠናክሮ በመቀጠል በማንኛውም ግዳጅ ድል አስመዝጋቢ ለመሆን ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል።

ዘጋቢ ሱራፌል መልሰው
ፎቶግራፍ ትዕግስት እናውጋው

ሳላም ለአለማችን ይሁን!
ሰላማችንን በሰለማዊ መንገድ እናደርግ ፣ እናስተዳድር ፣ እንምረ!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

https://dfmc.mod.gov.et/
https://www.facebook.com/EthioPolice.et
https://www.facebook.com/Ethiopeaces

የኮማንዶ ክፍለ ጦር ማንኛውንም ግዳጅ በአጭር ጊዜ በብቃት መፈፀም የሚያስችል አቅም ገንብቷል።የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ነሃሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ምየኮማንዶ ክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ሳዲቅ ...
01/09/2026

የኮማንዶ ክፍለ ጦር ማንኛውንም ግዳጅ በአጭር ጊዜ በብቃት መፈፀም የሚያስችል አቅም ገንብቷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ነሃሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም

የኮማንዶ ክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ሳዲቅ አህመድ ክፍለጦሩ ማንኛውንም ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል። ክፍለጦሩ የሀገርን እና የህዝብን ሠላም ለማደፍረስ ጥረት በሚያደርጉ የሠላም ፀር በሆኑ ቡድኖች ላይ አሥፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ሁሌም ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

በደማችን የምንፅፈው ደማቅ ታሪክ ለቀጣዩ ትውልድ ብሩህ ተስፋ ነው ያሉት ኮሎኔል ሳዲቅ አህመድ ክፍለ ጦሩ የፅንፈኛችን ሴራ እያከሸፈ ይህን ተላላኪ ቡድን በገባበት ገብቶ እየሽመደመደው ሥለመሆኑም አንስተዋል።

የኮማንዶ ክፍለጦር ሠራዊት አሁንም ተስፋ ቆርጦ በየሸጡ እየተሹሎከሎከ ህዝብን የሚዘርፈውን ፅንፈኛ እየተከታተለ መመንጠሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ዘጋቢ አበበ ካሳሁን
ፎቶ ግራፍ አስና አብደላ

ሳላም ለአለማችን ይሁን!
ሰላማችንን በሰለማዊ መንገድ እናደርግ ፣ እናስተዳድር ፣ እንምረ!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

https://dfmc.mod.gov.et/
https://www.facebook.com/EthioPolice.et
https://www.facebook.com/Ethiopeaces

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ሀይሎች ጓድ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share