10/03/2022
ብልጽግና ፓርቲ ነገ በሚጀምረው ጉባኤው የኢትዮጵያውያንን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ አስታወቀ
ብልጽግና ፓርቲ ነገ በሚጀምረው ጉባኤ የኢትዮጵያውያንን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ውሳኔዎች ይተላለፍበታል አለ።
ጉባኤውን አስመልክቶ የፓርቲው የህዝብና ዓለም አቀፍ ግኑኝነት ዘርፍ ሀላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ መግለጫ ሰጥተዋል።
ዶክተር ቢቂላ የብልጽግና አንደኛ ጉባኤ ባለፉት ሶስት አመታት ፓርቲው በሁሉም መስክ የተጎናጸፋቸውን ድሎች ይገመግማል ብለዋል።
የገጠሙትን ችግሮች እና ተግዳሮቶች በጥልቀት ገምግሞ ለማረም ታሪካዊ ውሳኔ ያሳልፋልም ብለዋል ።
ጉባኤው በጸጥታ ሁኔታ፣ በኢኮኖሚ እንዲሁም በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚመክርም ገልጸዋል ።
በዚህም ለዜጎች ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያመጡ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ነው ያሉት።
የብልጽግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ ነገ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ይጀምራል ።
በጉባኤው 1 ሺህ 600 የፓርቲው አባላት በድምፅ የሚሳተፉ ሲሆን፥ 400 ከተለያየ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ከውጭ ሀገራት የተጋበዙ እንግዶች ያለ ድምፅ ይሳተፋሉ።