Lideta Sub City Housing Adminstration Office /የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Lideta Sub City Housing Adminstration Office /የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት

Lideta Sub City Housing Adminstration Office /የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት Admnstrating house in lideta sun city condominium and kebele house

ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ 106 የቀበሌ ቤቶችን ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው አቅመ ደካሞች፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአገር ባለውለታዎች ለሆኑ እና እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ የከተማችን ነዋ...
13/12/2025

ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ 106 የቀበሌ ቤቶችን ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው አቅመ ደካሞች፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአገር ባለውለታዎች ለሆኑ እና እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ የከተማችን ነዋሪዎችን ለይተን በእጣ አስተላልፈናል ።

ከህዝብ ጋር ባደረግነው ውይይት የተሰጡንን ጥቆማዎችን ጭምር ተጠቅመን ባደረግነው ማጣራት የለየናቸውን ነዋሪዎቻችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፣ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ የተዘነጉ፣ ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን አቅመ ደካማ ወገኖችን እንባ በማበስ እና ከነበሩበት አስከፊ ሕይወት በመታደግ ነገን በተስፋ እንዲያዩ የሚያስችል ስራ ተከናውኗል ።

በተለይም ከአራዳ ክፍለ ከተማ ከቁርጡሚ ወንዝ ዳርቻ ለተነሳችሁ፣ በሶስተኛ ወገን ክርክር ምክንያት ስትንገላቱ የቆያችሁ ዛሬ ችግሩን ፈተን የመኖሪ የቤት ስላገኛችሁ እጅግ ደስተኞች ነን፤ እንኳን ደስ አላችሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ክብርት ከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በስኬት እንድንተገብር ላገዘን ፈጣሪ ምስጋና ይሁን!ዛሬ በዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ በፍጥነትና በጥራት በ24 ህንፃዎች የተገነቡትን 1,287 ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች በ...
23/11/2025

ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በስኬት እንድንተገብር ላገዘን ፈጣሪ ምስጋና ይሁን!
ዛሬ በዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ በፍጥነትና በጥራት በ24 ህንፃዎች የተገነቡትን 1,287 ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች በይፋ መርቀናል።

የሁላችን መዲና የሆችው ከተማችንን የማርጀት እና የመቆሸሽ ታሪክ በየዕለቱ እየቀየርን፤ የማህበረሰባችንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችሉ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወን ነው።

በተለይም የሕዝባችንን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከ 380,000 (ሶስት መቶ ሰማንያ ሺህ) በላይ ቤቶችን በመገንባት ለተጠቃሚዎች አስተላልፈናል። ይህም ከለውጡ በፊት ባሉት 17 ዓመታት ከተገነቡት 179,000 (መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺህ) ቤቶች እጅጉን የላቀ ነው።

የመፍጠርና የመፍጠን መርህን በተጨባጭ ካረጋገጥንባቸው ፕሮጀክቶች ይህ ትልቅ ስኬት 24/7 የሥራ ባህልን በተግባር ላይ በማዋል የተገኘ ዉጤት መካከል አንዱ ነው።
የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በጀርመን አደባባይ፣ በአየር ጤና እና በግራር አካባቢ የሚገኙ ናቸው።

ዛሬ የመረቅናቸው ከ11 እስከ 18 ወለል ያላቸው 24 ሕንፃዎች የያዙት የመኖሪያ ቤቶችን ብቻ ሳይሆን ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ጭምር ነው።
ይህም የልጆች መጫወቻ ስፍራዎችን፣ የስፖርት ሜዳን፣ የመዝናኛ ስፍራዎችን ፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን እና ሌሎች የጋራ መገልገያዎችን አሟልተዋል ።

ይህ ፕሮጀክት ከግንባታ ባለፈ በርካታ የሥራ ዕድሎችን እና የእውቀት ሽግግርን ለወጣቶቻችን አስገኝቷል፤ የግንባታ አቅም ፈጥሯል፤ በተጨማሪም ጥራትንና ፍጥነትን በተመሳሳይ ጊዜ ማረጋገጥ እንደምንችል አሳይቷል። ቤቶቹን በተመጣጣኝ ዋጋ ለንግድ ባንክ ሰራተኞች ያስረከብን በመሆኑ በአንድ በኩል የቤት እጥረትን ለመፍታት አማራጭ እርምጃ ያስቀመጠ ሲሆን፣ በሌላ በኩል የቤት ልማት ፈንድን የፈጠረ ጭምር ነው።

ለዚህ ሥራ ስኬት የበኩላችሁን የተወጣችሁ አመራሮችን፣ ባለሙያዎችን እና ተቋማትን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

ማስታወቂያ ለተጠባባቂ ማህበር ቤት ተመዝጋቢዎች
17/11/2025

ማስታወቂያ ለተጠባባቂ ማህበር ቤት ተመዝጋቢዎች

10/11/2025

የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት
የተገልጋዩን እንግልት ለመቀነስ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

የክፍለ ከተማው ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመቹ ጌታቸው እንደገለፁት ፅ/ቤቱ በየአመቱ የመንግስት ቤቶች ውል የማደስ ስራ ከዚህ በፊት በየወረዳው ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀው በ2018 በጀት ዓመት የወረዳ መዋቅር በመታጠፉ ምክንያት አገልግሎቱ በክፍለ ከተማው እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ገመቹ አክሎም ተገልጋዮች አገልግሎትን ፈልገው ሲመጡ ፦
👉ቴሌ ብር ተጠቃሚ መሆንና ክፍያን በዛ መፈፀም፣
👉 የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ኮፒ፣
👉የ2017 ዓ.ም ውል፣ ኪራይ የከፈሉበት ደረሰኝ፣
👉ተወካይ ከሆኑ ህጋዊ ውክልና ኮፒ፣
👉ወራሽ ከሆኑ የፍርድ ቤት የወራሽነት ማስረጃ ይዘው መምጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል ።

ጽ/ቤቱ የተገልጋዮች እንግልትና መመላለስ ለማስቀረት የሚያስችለውን ፕሮግራም ያወጣ ሲሆን በዚህ መሰረትም፦

ከ01/03/2018 ዓ.ም እስከ 07/03/2018 ዓ.ም የውል እድሳት ፕሮግራም
👉ሰኞ ወረዳ 5=43ቀበሌና 30ቀበሌ
👉ማክሰኞ ወረዳ 3=36ቀበሌና 37ቀበሌ
👉ዕሮብ ወረዳ 4=10ቀበሌ,ወረዳ6=12ቀበሌ,ወረዳ 8=15ቀበሌ
👉ሐሙስ, ወረዳ1=03ቀበሌ,ወረዳ 2=12ቀበሌ,ወረዳ 10=16ቀበሌ
👉አርብ,ወረዳ 9=51 እና 29 ቀበሌ
👉ቅዳሜ ወረዳ 7=34,ወረዳ 9=40ቀበሌ
👉እሁድ ወረዳ 5=41 ቀበሌ

መሆኑን ተገንዝበው ሁሉም ነዋሪዎች አገልግሎቱን በተቀመጠው መርሀ ግብር ብቻ መስተናገድ እንደሚችሉ እንገልፃለን ።

ማሳሰቢያ!
👇👇👇👇
ጽ/ቤቱ ቀጣይ ያሉትን ፕሮግራሞችን እያሳውቃለን ።

የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት የተገልጋዩን እንግልት ለመቀነስ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።የክፍለ ከተማው ቤቶች አስተዳደር  ፅ/ቤት  ሀላፊ አቶ ገመ...
28/10/2025

የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት
የተገልጋዩን እንግልት ለመቀነስ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

የክፍለ ከተማው ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመቹ ጌታቸው እንደገለፁት ፅ/ቤቱ በየአመቱ የመንግስት ቤቶች ውል የማደስ ስራ ከዚህ በፊት በየወረዳው ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀው በ2018 በጀት ዓመት የወረዳ መዋቅር በመታጠፉ ምክንያት አገልግሎቱ በክፍለ ከተማው እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ገመቹ አክሎም ተገልጋዮች አገልግሎትን ፈልገው ሲመጡ ፦
👉ቴሌ ብር ተጠቃሚ መሆንና ክፍያን በዛ መፈፀም፣
👉 የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ኮፒ፣
👉የ2017 ዓ.ም ውል፣ ኪራይ የከፈሉበት ደረሰኝ፣
👉ተወካይ ከሆኑ ህጋዊ ውክልና ኮፒ፣
👉ወራሽ ከሆኑ የፍርድ ቤት የወራሽነት ማስረጃ ይዘው መምጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል ።

ፅ/ቤቱ የተገልጋዮች እንግልትና መመላለስ ለማስቀረት የሚያስችለውን ፕሮግራም ያወጣ ሲሆን በዚህ መሰረትም፦

ከጥቅምት 17_23/2018 ዓ.ም

👉ሰኞ ወረዳ 5=30 ቀበሌ
👉ማክሰኞ ወረዳ 3= 26 ቀበሌ
👉ዕሮብ ወረዳ 4=10 ቀበሌ ,ወረዳ 6=12 ቀበሌ,ወረዳ 8=11&12 ቀበሌ
👉ሀሙስ ወረዳ 1=01ቀበሌ,ወረዳ 2=12 ቀበሌ,ወረዳ 10=17ቀበሌ
👉አርብ ወረዳ 9=50ቀበሌ, ወረዳ 7=32ቀበሌ
👉ቅዳሜ ወረዳ 5=43ቀበሌ,ወረዳ 3=36ቀበሌ
👉እሁድ(ጥዋት) ወረዳ 5=42ቀበሌ መሆኑን ተገንዝበው ሁሉም ነዋሪዎች አገልግሎቱን በተቀመጠው መርሀ ግብር ብቻ መስተናገድ እንደሚችሉ ገልፀዋል።

ማሳሰቢያ!
👇👇👇👇
ጽ/ቤቱ ቀጣይ ያሉትን ፕሮግራሞችን እያሳወቁ እንደምሄዱ ገልፀዋል።

እንኳን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ምርቃት አደረሳችሁ ÷ አደረሰን !!
09/09/2025

እንኳን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ምርቃት አደረሳችሁ ÷ አደረሰን !!

 !!
08/09/2025

!!

🎆🎆🎇 እንኳን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ዋዜማ አደረሳችሁ ÷ አደረሰን !!🎇🎆🎆🤲በሕብረት ቸርሰንዋል ዳግማዊ አድዋ...
08/09/2025

🎆🎆🎇 እንኳን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ዋዜማ አደረሳችሁ ÷ አደረሰን !!🎇🎆🎆

🤲በሕብረት ቸርሰንዋል ዳግማዊ አድዋ...

ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተውጣጣ የምዘና ቡድን የልደታ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤትን የ2017 በጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት መሰረት ያደረገ ምዘና በዛሬው...
24/07/2025

ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተውጣጣ የምዘና ቡድን የልደታ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤትን የ2017 በጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት መሰረት ያደረገ ምዘና በዛሬው ዕለት በ17/11/2017 ዓ.ም አካሄደ።
የልደታ ክፍለ ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራት ለመመዘን ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተውጣጡ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች በምዝናው ተሳተፉ ሲሆን በክፍለ ከተማው የሚገኙ የጽ/ቤት ኃላፊው ፤ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
በምዘናው የጽ/ቤቱ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም በሰነድ እና በአካል ምልከታ በዝርዝር በማየት የምዘና ቡድኑ የማጠቃለያ አስተያየት ስጥቷል፡፡
ጽ/ቤቱ በአከራይ ተከራይ ምዝገባ ፤ በኮሪደር ልማት ተነሺዎች መረጃ አያያዝ እና ከክፍለ ከተማው መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር ያከናወኛቸው አበይት ተግባራትን በስሩ ባሉ 10ሩም ወረዳ ጽ/ቤቶች ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ እና ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት እንዲሁም አገልግሎት እስጣጡን ለማዘመን በቆራትነት እረፍት የለሽ ስራ በመስራት ውጤት ማስመዝገቡን የገለፁት አቶ ደምስ በየነ የልደታ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ናቸው፡፡
በቀጣይም በጥንካሬ የተያዙትን ስራዎች በማስቀጠል እና ጥቂት የተንጠባጠቡ ስራዎችን በቅንነት ወስዶ በማስተካክል ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ የጽ/ቤት ኃላፊው አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ለምዘና የመጡትም ቡድኖች ደጋፊና መልካም በቀጣይ በትብብር ለመስራት እና የቋሙን ስም ለመገንባት በጋራ በመስራት ተሸለ ቦታ ለማድረስ በመግባባት ምዘናው ተጠናቋል፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች :- https://t.me/LidetaHousingAdminstrationOffice

 #ማስታወቂያየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ስፍራዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ የተደረጉ ፕላዛዎችና ፓርኪንጎች ውስጥ የሚገኙ ንግድ ሱቆችን እና መጋዘኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለማ...
19/05/2025

#ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ስፍራዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ የተደረጉ ፕላዛዎችና ፓርኪንጎች ውስጥ የሚገኙ ንግድ ሱቆችን እና መጋዘኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት የወጣ ማስታወቂያ ፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ !!

19/05/2025

#ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ስፍራዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ የተደረጉ ፕላዛዎችና ፓርኪንጎች ውስጥ የሚገኙ ንግድ ሱቆችን እና መጋዘኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት የወጣ ማስታወቂያ ፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ !!

የልደታ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት የወረቀት አገልግሎት ለማስቀት የሚያስችልና አገልግሎትን በኦን ላይን የሚሰጥበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጓል።በፕሮግራሙ ማስጀመሪያ የአዲስ አ...
10/03/2025

የልደታ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት የወረቀት አገልግሎት ለማስቀት የሚያስችልና አገልግሎትን በኦን ላይን የሚሰጥበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጓል።

በፕሮግራሙ ማስጀመሪያ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ቢሮ ሀላፊና ምክትል ሀላፊዎች የክፍለ ከተማ አስተባባሪዎች የወረዳ አመራሮች በተገኙበት አስጀምረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ቅድስት እንደተናገሩት ውስን የሆነ የመንግስትና የህዝብ ሀብት ወደ አንድ ቋት በማስገባት ለማስተዳደርና ፍትሀዊ በሆነ አግባብ ማከፋፈል እንዲቻል ይህ ቴክኖሎጂ ይጠቅማል በማለት በጽ/ቤቱ የሚነሱ ቅሬታዎችንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚቀርፍ ይሆናል ብለዋል

አዲስ አበባ ስማርት እየሆነች እንድትመጣ እየተሰራ ያለበት አግባብ በፍጥነት እያደገ መምጣቱን ሀላፊዋ ገልፀው የቤቶች አገልግሎትም በቴክኖሎጂ በመታገዝ የወረቀት ንክኪን በማስቀረት ኦን ላይን አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የተሰራው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል ይገባል።

ፕሮግራሙን አስጀምረን ወደ አገልግሎት ስንገባ የሲስተም መቆራረጥ እንዳይኖር ማገዝ ያስፈልጋል በማለት ለፕሮግራሙ መሳካት ድጋፍ ላደረጋችሁ አመራሮች ባለሙያዎች ከልብ እናመሠግናለን ሲሉ ወ/ሮ ቅድስት ገልፀዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በፕሮግራሙ ማስጀመሪያ እንደተናገሩት ቴክኖሎጂ ተገልጋዩ በማንኛውንም ቦታ ሆኖ አገልግሎት ማግኘት የሚችልበትና መረጃ እንዲያገኝ ከማድረግ በላይ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን የሚያዘምንና ብልሹ አሰራርን የሚቀርፍ ይሆናል በማለት ገልፀዋል።

ወ/ሮ አበባ እሸቴ አያይዘው በወረቀት የሚሰጥ አገልግሎትን ወደ ሲስተም በማስገባት በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ወደ ቴክኖሎጂ መቀየሩን ይፋ አድርገዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ሀላፊ አቶ ደምስ በየነ እንደገለፁት በሲስተሙ 4021 የጋራ ቤቶችና 22243 የመንግስት መኖሪያና ንግድ ቤቶች ማስገባት መቻሉን ገልፀው ቤቶች አስተዳደር የተለያዩ አገልግሎቶችን ለተገልጋዮች በቴክኖሎጂ ለመስጠት ያስችላል ያሉት ሀላፊው ሲስተሙ የስም ዝውውሮችንና ለውጦችን ፣ የቤት አገልግሎት ለውጦች በአግባቡ ለመቅቆጣጠርና ስርዓት ለማስያዝ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ይፈጥራል በማለት ገልፀዋል።

Address

ልደታ, ልደታ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛጉዌ ህንፃ አጠገብ ልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ላይ ምድር ላይ በስተቀኝ በኩል
Addis Ababa
0115515500

Telephone

+251115515500

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lideta Sub City Housing Adminstration Office /የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share