Ethiopian Geological Institute

Ethiopian Geological Institute የሃገር ውስጥ የምርምር አቅም እንዲጠናከር በማድረግ፣ በተለያዩ የሥነ-ምድር ጥናት ዘዴዎች ምርምር ማካሄድ::

የኢትዮጵያ ጂኦሎጅካል ኢንስቲትዩት ከቼክ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።(GIE) # # # # # # #(ሚያዝያ 14/2018 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ጂኦሎጅካል...
22/04/2026

የኢትዮጵያ ጂኦሎጅካል ኢንስቲትዩት ከቼክ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

(GIE)
# # # # # # #

(ሚያዝያ 14/2018 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ጂኦሎጅካል ኢንስቲትዩት ከቼክ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ እና የቼክ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ምክትል ዳይሬክተር ፔትር ሚክሳ ናቸው::

ስምምነቱ በኢትዮጵያ የጂኦሎጂካል ካርታ ዝግጅት ፣ ማዕድንና የጂኦተርማል ኢነርጂ ሀብት ፣ በጂኦሎጂካል ካርታ ዝግጅትና በስነ-ምድር አደጋ ጥናትና ምርምር ላይ ያተኮረ ነው::

ሁለቱ ወዳጅ ሃገራት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በጋራ እንደሚሰሩ የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ ስምምነቱ ለማዕድኑ ዘርፉ ከሚያበረክተው አስተዋፆ ባሻገር የትብብር ግንኙነታቸውን ለማጠናከርና ለጋራ ተጠቃሚነታቸው ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልፀዋል።

ይህ ስምምነት ከአውሮፓ ህብረት የሚደገፉ ፕሮጀክቶችን እንደ TAEIX እና PANAFGEO ጋር ተባብሮ ለመስራት ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

በዛሬው እለት በተደረገው የስምምነት መርሐ-ግብር የሁለቱ ሀገራት የዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/GIE2023E
Website:- https:www.gie.gov.et/
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

11/04/2026
ኢንስቲትዩቱ በአየር ወለድ ጂኦፊዚክስ ዙሪያ ከውጭ አገራት ጋር የምክክር አውደ ጥናት አካሄደ፡፡(GIE) # # # # # # #(መጋቢት 24/2018ዓ.ም) የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት በ...
02/04/2026

ኢንስቲትዩቱ በአየር ወለድ ጂኦፊዚክስ ዙሪያ ከውጭ አገራት ጋር የምክክር አውደ ጥናት አካሄደ፡፡

(GIE)
# # # # # # #
(መጋቢት 24/2018ዓ.ም) የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት በአየር ወለድ ጂኦፊዚክስ ከኬንያ እና ከካናዳ ከመጡ እንዲሁም በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች በሃገር አቅም እንዴት መሰራት እንደሚቻል የምክክር አውደ ጥናት አካሂደዋል፡፡

አሁን ላይ ተቋሙ በሃገራችን የአየር ወለድ (Airborne) ጂኦፊዚክስ ሥራን እውን ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል። በዚህ ረገድ ከካናዳ እና ኬንያ የዘርፋ ከፍተኛ ተመራማሪዎች እንዲሁም በሃገራችን ስመጥርና አንጋፋ ምሑራን በመጋበዝ ዘለግ ያለ የልምድ ልውውጥ ተደርጓል።

ጎረቤት ሃገር ኬንያ ስኬታማ ከሆነችባቸው ሥራዎች እንዱ የአየር ወለድ ጂኦፊዚክ ተጠቃሽ ነው፡፡ በጥናት ላይ የተደገፈ መልካም ተሞክሯቸዉን እንዲሁም ምን አይነት መሳሪያዎችን እንደተጠቀሙ ገለፃ አድርገዋል::

በሌላ በኩል ከካናዳ የመጡት ባለሙያዎች በመሳሪያ አጠቃቀም ስልጠና ከሰጡ በኋላ ማንኛዉንም ሙያዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል::

በተጨማሪም ሃገር በቀል የሆነው ናሽናል አቬሽን ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል::

ከተለያዩ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት እና ከግል ሴክተር የመጡ ሙሑራን የተለያዩ ምክረ ሃሳቦችን አንስተዋል:: ኢንስቲትዩቱን በሙሉ አቅም ለማገዝ ያላቸውን ተነሳሽነት አሳይተዋል።

በመጨረሻ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ ባስተላለፋት መልዕክት ኢንስቲትዩቱ ዘርፉን ለመደገፍ ፋና ወጊ የሚሆኑ አበይት ተግባር በመፈፀም ይታወቃል:: ኢትዮጵያ ከሁለቱ ሃገራት ጋር ያላትን የቆየና የጠነከረ አጋርነት ለማስቀጠል በሁለንተናዊ አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሻገር እንደሚቻል ገልፀዋል:: አክለውም ትኩረት የሰጧቸው ጉዳዮች ወደ ተጨባጭ ውጤት እንዲቀየሩ ተቋማዊ ግንኙነቶችን ይበልጥ ለማሳደግ ተቀራርበው መስራት አለብን ብለዋል::

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/GIE2023E
Website:- https:www.gie.gov.et/
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

በአይነቱ ልዩ የሆነው ዘመናዊ የጂኦሣይንስ ላቦራቶሪ ማዕከል ግንባታ ከመቶ 70% ያህሉ መጠናቀቁ ተገለፀ፡፡(GIE) # # # # # # #(መጋቢት 12/ 2018 ዓ.ም) ኢንስቲትዩቱ ከሚያከናው...
21/03/2026

በአይነቱ ልዩ የሆነው ዘመናዊ የጂኦሣይንስ ላቦራቶሪ ማዕከል ግንባታ ከመቶ 70% ያህሉ መጠናቀቁ ተገለፀ፡፡

(GIE)
# # # # # # #
(መጋቢት 12/ 2018 ዓ.ም) ኢንስቲትዩቱ ከሚያከናውናቸው የፕሮጀክት ሥራዎች አንዱ የሆነው የጂኦሣይንስ የላቦራቶሪ ማዕከል መልሶ የማደራጀት ግንባታ 70% ያህሉ መጠናቀቁን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ ገለፁ፡፡

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩቱ የጂኦሣይንስ መረጃን ለማመንጨት እና የተለያዩ የአለት ናሙናዎችን ለመመርመር እንዲያስችል የጂኦሣይንስ ላቦራቶሪ ማዕከል መልሶ ለማደራጀት መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ/ም ከኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር የስምምነት ፊርማ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

ይህ ዘመናዊ እና በአይነቱ ልዩ የሆነው ደረጃውን የጠበቀ ላብራቶሪ ማዕከል የግንባታ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ በተለምዶ መካኒሳ ተብሎ በሚጣራ አካባቢ ሲሆን ማዕከሉ ሲጠናቀቅ ቀደም ሲል ሲሰጣቸው ከነበረው የምርመራ አገልግሎት በተጨማሪ ከተለያዩ ሃገራት ዘመናዊ ማሽነሪዎችን በማስገባት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እንደሚያከናውን እና በሀገርአቀፍ ደረጃ ብሎም ለውጭ ሃገራት ምርመራ ያደርጋል፡፡

በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ለማዕድኑ ዘርፉ ከሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባሻገር በኢትዮጵያ የወጣቶች ሥራ አጥነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ መንግስትም ትኩረት ከሰጠባቸው አጀንዳዎች መካከል የወጣቶችና አጠቃላይ የሥራ እድል ፈጠራ ማሳደግ ይገኝበታል፤ ለዚህም መልካም ዕድል ይዞ እንደመጣ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡

የጂኦሳይንስ ላብራቶሪ ማዕከል የማዕድን ፍለጋን ፣የአካባቢ ክትትልን፣ የጂኦቴክኒካል ምህንድስናን እንዲሁም ሳይንሳዊ ምርምርን ለመደገፍ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው የሚታመንበት ነው፡፡ በዚህ ረገድ ማዕከሉ ዘመኑ በዋጁ መሳሪያዎች በመታገዝ እንደ ጂኦኬሚስትሪ እና ሚኒራሎጂ ቴክኒኮችን በመጠቀም የሥነ ምድር ሀብቶችንና አደጋዎችን በቀላሉ ለመገምገም አስቻይ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

እንደ አቶ ኢጃራ ገለፃ ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ሰዓት የግንባታው ፕሮጀክት ከመቶ 70% ያህሉ መጠናቀቁን እና ተጨማሪ የላብራቶሪ መሣሪያዎች ግዥ በሂደት ላይ ነው፡፡

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/GIE2023E
Website:- https:www.gie.gov.et/
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።GIE # # # # # # #መጋቢት 10/2018 ) የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተ...
19/03/2026

ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

GIE
# # # # # # #
መጋቢት 10/2018 ) የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢጃራ ተስፋዬ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆናችሁ ወንድም እህቶቻችን እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሃገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ በአለም አቅፍ ደረጃ ትኩረት እየሳበች ያለችው ባሏት የማዕድን ተፈጥሯዊ ፀጋዋ ነው። በዚህም ወደ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚ እና ዘመናዊ ኢንደስትሪ በምታደርገውን ሽግግር የሚያሳልጥ ዜጋ እንፍጠር ብለዋል።

በዓሉ በመተባበር የደስታ ብርሃን የሚንፀባረቅበት፣ሕይወት በበጎነት የምንደምቅበት ይሁንልን ይሁንላችሁ!
እንኳን ለዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ዒድ ሙባረክ!

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/GIE2023E
Website:- https:www.gie.gov.et/
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

የወርቅ ገበያው አዲስ ገጽታ(መጋቢት10/2018ዓ.ም) በአዲሱ የዓለም የንግድ ሥርዓት ውስጥ የብሪክስ አባል ሀገራት የሚጫወቱት ሚና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎላ መጥቷል። ወርቅ ከጥንት ጀምሮ የሀብ...
19/03/2026

የወርቅ ገበያው አዲስ ገጽታ

(መጋቢት10/2018ዓ.ም) በአዲሱ የዓለም የንግድ ሥርዓት ውስጥ የብሪክስ አባል ሀገራት የሚጫወቱት ሚና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎላ መጥቷል። ወርቅ ከጥንት ጀምሮ የሀብትና የግርማ ሞገስ መገለጫ ብቻ ተደርጎ ቢወሰድም አሁን ባለው ዓለም አቀፋዊ የጂኦ-ፖለቲካ ሽኩቻ ውስጥ ግን ትልቅ የስትራቴጂ መሣሪያ ሆኗል። በተለይም አሜሪካ ዶላርን እንደ ማዕቀብ መሣሪያ በምትጠቀምበት በዚህ ዘመን የብሪክስ ሀገራት ወርቅን እንደ መከላከያ ጋሻ በመጠቀም የኢኮኖሚ ነፃነታቸውን ለማረጋገጥ እየተጋሉ ይገኛሉ። ይህ የታሪክ ሽግግር የወርቅ ገበያውን መልክ በሚከተሉት ምሰሶዎች ላይ ተመሥርቶ እየለወጠው ይገኛል።

የመጀመሪያው ክስተት በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ማዕከላዊ ባንኮች ወርቅን ለማከማቸት የሚያደርጉት ከፍተኛ ፉክክር ነው። ቻይና እና ሩሲያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወርቅን በብዛት በመግዛት ቀዳሚዎቹ ሀገራት ሆነዋል። የዚህ ጥረት ዋና ዓላማ በዶላር ላይ ያለባቸውን ጥገኝነት በመቀነስ የሀገራቸውን የውጭ ምንዛሬ ክምችት በማንኛውም ምዕራባዊ ኃይል ትእዛዝ ሊታገድ ወይም ሊታሰር በማይችል አስተማማኝ ሀብት መተካት ነው። ይህም ለብሪክስ አባላት ዘላቂ የኢኮኖሚ ዋስትናን የሚሰጥ ስልታዊ እርምጃ ነው።

ሁለተኛው ለውጥ የወርቅ ዋጋ ተመን ማዕከል ከምዕራብ ወደ ምስራቅ መሸጋገሩ ነው። ለዘመናት የወርቅ ዋጋ የሚወሰነው በለንደን እና በኒውዮርክ የገበያ ማዕከላት ቢሆንም አሁን ግን ይህ የበላይነት እየተሸረሸረ ይገኛል። ቻይና የራሷን የሻንጋይ ወርቅ ገበያ በማጠናከር ዋጋው በዩዋን እንዲተመን እያደረገች ነው። ከዚህም ባለፈ አባል ሀገራቱ የራሳቸውን የጋራ የወርቅ ንግድ መድረክ ለመፍጠር ማሰባቸው የምዕራባውያንን የገበያ ተጽዕኖ በእጅጉ የሚቀንስና የምስራቁን ዓለም የገበያ መሪ የሚያደርግ ክስተት ነው።

ሦስተኛውና እጅግ አነጋጋሪው ጉዳይ ወርቅን ለአዲሱ የጋራ መገበያያ ገንዘብ እንደ መሠረት የመጠቀም ሐሳብ ነው። ብሪክስ የጋራ ገንዘብ ለመፍጠር በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ገንዘቡ በወርቅ ዋጋ ላይ የተደገፈ እንዲሆን ሰፊ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ። ይህ ከሆነ አዲሱ ገንዘብ እንደ ዶላር በቀላሉ የማይዋዥቅና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው የእሴት መለኪያ ይሆናል። በዚህም ወርቅ በሀገራቱ መካከል ለሚደረግ ግዙፍ የንግድ ልውውጥ እንደ ዋጋ መለኪያ በማገልገል የዶላርን የሰማንያ ዓመታት የበላይነት ሊተካ ይችላል።

ኢትዮጵያ የራሷ የወርቅ ምርት ያላት ሀገር እንደመሆኗ ይህ አዲስ የወርቅ ፖለቲካ ትልቅ ዕድል ይዞላታል። የሀገሪቱ ብሔራዊ ባንክ የወርቅ ክምችቱን በማሳደግ የኢኮኖሚ ጥንካሬውን ማሳየት የሚችልበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል። እንዲሁም በብሪክስ በኩል የሚፈጠሩ አማራጭ የገበያ መድረኮች ኢትዮጵያ ምርቷን በተሻለ ዋጋና በተረጋጋ ሁኔታ እንድትሸጥ ትልቅ እገዛ ያደርጋሉ።

አዲሱ የዓለም ወርቅ ገበያ ከንግድ እንቅስቃሴ ባለፈ የዓለም የኃይል ሽግግር ማሳያ ነው። ብሪክስ ወርቅን እንደ አዲስ የገንዘብ ሥርዓት መሠረት በማድረግ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታቸውን ለማወጅ እየተጠቀመበት ይገኛል።

ዛዲግ አብርሃ
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት

ኢንስቲትዩቱ በ1:50,000 መስፈርት 8 የጂአሎጂ ካርታዎችና 4 ገላጭ ሪፖርቶች ማዘጋጀቱን ገለፀ፡፡(GIE) # # # # # # #(የካቲት 2018 ዓ/ም) በኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ...
04/03/2026

ኢንስቲትዩቱ በ1:50,000 መስፈርት 8 የጂአሎጂ ካርታዎችና 4 ገላጭ ሪፖርቶች ማዘጋጀቱን ገለፀ፡፡

(GIE)
# # # # # # #

(የካቲት 2018 ዓ/ም) በኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ከሚያከናውናቸው አበይት ተግባራት አንዱ የሆነው የሥነምድምር ካርታ ዝግጅት የሰራ ክፍል በ2017ዓ.ም. 6000ካ.ኪ.ሜ (8 ሰብ ሽቶች * 750ካ.ኪ.ሜ) በሚሸፍን ቦታ ላይ ጥናት በማካሄድ በ1:50,000 መስፈርት 8 የጂአሎጂ ካርታዎችና 4 ገላጭ ሪፖርቶች ማዘጋጀቱን ገለፀ፡፡

የኢንስቲትቱ የሥነ ምድር ካርታ ዝግጅት ኃላፊ የሆኑት ሲሳይ ደጉ ዶ/ር እንደገለፁት በሃገሪቷ የተለያዩ ስፍራዎች የተካሄደው ጥናት በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ፣ ቦረና እና ጅማ ዞኖች ፣ በሶማሌ ብሔራዊ ክልል ፋፈን፣ ሲቲ እና ዳዋ ዞኖች፣ በሀረሬ ሕዝብ ብሔራዊ ክልል፣ በድሬድዋ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም በማዕከላዊ ፡ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ እና የም ዞኖች በተለያዩ አከባቢዎችን በሚሸፍኑ በአራቢ፣ ጭናክሰን፣ ድሬ-ዳዋ፣ገርባኖ፣ ሌይ፣ አርደር፣ ኩምቢና አበልቲ ሰብ ሽቶች ተዘጋጅተው መጠናቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡

እነዚህ በተሻለ ዝርዝር መስፈርት የተዘጋጁ የጂኦሎጂ ካርታዎች ስለ አለት ዓይነቶች (lithologic units) እና ስነምድር አወቃቀር (geologic structure) በተጠኑት አካባቢዎች ለማንኛውም የሥነምድር ጥናት ለሚከናወኑ የማዕድን ፍለጋ፣ ለግንባታ፣ ለግብርና፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለስነምድር አደጋዎች መከላከል፣ እንዲሁም ለጥናትና ምርምር ስራዎች መሰረታዊ መረጃዎችን የያዙ በመሆናቸዉ ሰፊ እና ወሳኝ አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸውን አክልዋል፡፡

በዚህ ረገድ ጥናቶቹ ለግንባታ (ሳንድስቶን፣ግራናይት፣ባሳልት)፣ለኢንዱስትሪ (ላይምስቶን፣ ኳርትዝ፣ ማይካ፣ ክሌይ ፣ግላውኮናይት)፣ በተጨማሪም ለወርቅ እና ለከበሩ ድንጋዩች የክምችት ቦታዎች ለመለየት የሚረዱ መሆናቸውን ጥናቱ ያመላክታል፡፡

ይህ ጥናት በ2013ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን እስከ አሁን 33,000ካ.ኪ.ሜ. ወይም ከሀገሪቱ የቆዳ ሽፋን 2.9% የተጠናቀቀ ነው፡፡ ከ2013ዓ.ም እስከ 2016ዓ.ም የተካሄደዉ ጥናት የተቀናጀ የጂኦሎጂካልና ጂኦኬሚካል ማፒንግ እንደሆነ ጥናቱ ያመላክታል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በ2018 በጀት አመት በዕቅዱ መሰረት ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/GIE2023E
Website:- https:www.gie.gov.et/
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

የወርቅ እና የብረት ማዕድናት ምርት ፈቃድ ረቂቅ ስምምነቶች ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ  አሳለፈ፡፡ (GIE) # # # # # # #( የካቲት 23/2018 የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ...
02/03/2026

የወርቅ እና የብረት ማዕድናት ምርት ፈቃድ ረቂቅ ስምምነቶች ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

(GIE)
# # # # # # #
( የካቲት 23/2018 የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 53ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 53ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። ምክር ቤቱ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች አንዱ የወርቅ ማዕድን እና የብረት ማዕድን ምርት ፈቃድ ረቂቅ ስምምነቶች ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቷል፡፡ ለምክር ቤቱ የቀረቡት ሁለት ረቂቅ ስምምነቶች የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ከማሳደግ፣ ለዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠር፣ ለኢኮኖሚያችን አዎንታዊ ሚና ከመወጣት አንጻር ትልቅ ጠቀሜታ ያላቸውና ከአካባቢ ጥበቃና ከማህበረሰብ ተጠቃሚነት አንጻርም የመንግስትን የፖሊሲ አቅጣጫ የተከተሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ የማዕድን ሚኒስቴር ስምምነቶቹን እንዲፈራረምና ወደ ስራ እንዲገቡ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ይሁንታ ሰጥቷል፡፡

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/GIE2023E
Website:- https:www.gie.gov.et/
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

የአፍሪካውያን የነፃነት ግርማ!የኢትዮጵያውያን የአንድነት አርማ!የማይደበዝዝ ደማቅ ታሪክ አድዋ!(GIE) # # # # # # #(የካቲት 23/2018ዓ/ም)እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል ...
02/03/2026

የአፍሪካውያን የነፃነት ግርማ!
የኢትዮጵያውያን የአንድነት አርማ!
የማይደበዝዝ ደማቅ ታሪክ አድዋ!

(GIE)
# # # # # # #
(የካቲት 23/2018ዓ/ም)

እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ለመላው የጥቁር ሕዝብ እንዲሁም የአፍሪካ ቀንዲል ኩራት ለሆነው የዓድዋ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል!
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/GIE2023E
Website:- https:www.gie.gov.et/
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

Address

9. 0154525, 38. 8237591
Addis Ababa
486

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 00:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Geological Institute posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share