Team Of Dr.Abiy Ahimed Ali

Team Of Dr.Abiy Ahimed Ali odeeffannoo dhugaa ummataan gahuudha

19/02/2023
21/11/2022

ለዜጎች ክብር የሚሰጠው ብልፅግና ፓርቲ
ዜጎቿን ያላከበረች አገር በሌሎች ልትከበርና ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ ሊኖር አይችልም፤ ዜጎቿን በሁለንተናዊ መልኩ ማክበር የቻለች አገር ግን ለዜጎቿ በሰጠችው ክብር ልክ ከፍ ብላ ትታያለች፣ ሉዓላዊነቷም ተከብሮ ትኖራለች፡፡ አገር ዜጎቿን ትመስላለች የሚባለውም ለዚህ ነው፤ ዜጎችም የአገራቸው ገጽታዎች ናቸውና፡፡

ብልጽግና ፓርቲ በመደመር መስመር መዳረሻውን በሁለንተናዊ ብልጽግና ለማሳካት ጉዞ የጀመረው የዜጎችን ክብር በማስቀደም ነው፡፡ ብልጽግና የዜጎች ወይም ሰዎች ክብር በአገር፣ በቡድንና በግለሰብ ደረጃ የሚገለጽ መሆኑን በማመን እንዲሁም የአገር ክብር የግለሰቦች የወል ክብር መሆኑን በጥልቅ በመረዳት ኢትዮጵያዊያን የሚመኙትንና ሁልጊዜም እየፈለጉና እየሞከሩ በሚፈልጉት ልክ ያላገኙትን ሰው በመሆን የሚቀድም አብሮነት እውን ለማድረግ እየሰራ ያለ የህዝብ ፓርቲ ነው።

ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ለረጅም ዓመታት እየፈተናቸው ያለውን ጉድለትና ጉድለቱን ሞልቶ ወደ ብልፅግና ለማሸጋገርም ቀዳሚው ጉዳይ የዜጎች ክብርን ማረጋገጥ በመሆኑ ለዜጎች ክብር የትኛውንም አይነት ዋጋ በመክፈል ብልፅግናን ለማረጋገጥ ቆርጦ ተነስቷል።

በብልጽግና እምነት ሰዎች ወይም ዜጎች ሁልጊዜም ወደ ግብ መቅረቢያ መንገድ ሳይሆኑ ራሳቸው ግብ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ሰዎች አንድን ነገር ለማግኘት ወይም ለማሳካት ሲባል ብቻ የሚያስፈልጉ፣ አለያም ገሸሽ የሚደረጉ አይደሉምና፡፡ ይልቁንም ዜጎች በራሳቸው ከሁሉም ነገር ቀድመው የሚቀመጡ፤ የሚከበሩ፣ በማንነታቸውም ሳይሸማቀቁና ሳያፍሩ ቀና ብለው መሄድ የሚችሉ መሆናቸውን ማመን ይገባል፡፡

ብልጽግና ስለ ዜጎች ክብር መናገር ብቻ ሳይሆን፤ የተናገረውንና ያመነበትን እየተገበረ ያለ ፓርቲ ነው፡፡ በዜጎች መከበር ውስጥ የአገር ክብርና ሉዓላዊነት እውን እንደሚሆንም በጥልቅ ያምናል፡፡ እምነቱን እውን ለማድረግም ገና ከጥንስሱ በለውጥ ማግስት ያከናወናቸው ዜጋ ተኮር ተግባራትና በአገር ውስጥና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን በአደባባይ የገለፁት እምነትና ያሳዩት ተስፋ ህያው ምስክር ነው፡፡

በዛሬው ዕለት እንግልት ውስጥ የነበሩ ከሳውዲ የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ብቻ ሳይሆን ተመላሾችን በማደራጀትና መስራት የሚፈልጉትን በተለያዩ ዘርፎች በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በማደራጀት የራሳቸውን ስራ ፈጥረው እንዲሰሩ ለማድረግ በብልጽግና ፓርቲ በሚመራው መንግስት የተለያየ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

14/11/2022

ኢትዮጵያ ከፈተናዎች በላይ ናት!

ዚያድ ባሬ በኢትዮጵያ ላይ ወረራ በፈጸመበት ጊዜ ምዕራባውያን ሚዲያዎች ልክ ባለፉት ሁለት ዓመታት እንዳደረጉት ሁሉ "አጥቂውን እያሞገሱ ተጠቂውን ይኮንኑ ነበር ። "ኢትዮጵያ አለቀላት! ተበተነች! ጠፋች!" እያሉ ይጽፉና ያወሩ ነበር " ሌ/ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህ።
ኢትዮጵያ ግን ከፈተናዎች በላይ እንደሆነች ትላንትም ዛሬም አስመስክራለች።

Address

Addis Abeba
Adama
04

Telephone

+251906182085

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Team Of Dr.Abiy Ahimed Ali posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Team Of Dr.Abiy Ahimed Ali:

Share