Bole woreda 4 job and skill office

Bole woreda 4 job and skill office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bole woreda 4 job and skill office, Government Organization, Addis ababa, Ababa.

የወረዳ 04 የስራ ና ክህሎት ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ ስራ አስፈፃሚ  የ6 ወር የጽ/ቤቱ ራፖርት ና የመማክርት ጉባኤው ከተቋቋመበት ዕለት አንስቶ  የተሰሩ ስራዎችን በጥል...
01/01/2026

የወረዳ 04 የስራ ና ክህሎት ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ ስራ አስፈፃሚ
የ6 ወር የጽ/ቤቱ ራፖርት ና የመማክርት ጉባኤው ከተቋቋመበት ዕለት አንስቶ የተሰሩ ስራዎችን በጥልቀት በመገምገም ። በጠንካራ ጉን የታዩ ነገርዎች እንዲ ቀጥሉ ና በደካማ ጉን የታዩ ነገርዎች ደግሞ እንዲሻሻሉ አስተያየት በመለዋወጥ ለቀጣይ የመማክርት ጉባኤው ትኩረት የሚያደርግበትን የአገልግሉት ዘርፍ በመለየት በትኩረት እንዲሰራበት የጉባኤው ሰብሳቢ አቶ አብርሃም ሽመልስ በተደረገውየ የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ አሳስበዋል ።

በቀን 11/04/2018 በቦሌ ወረዳ 04 ስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት የከተማ ምግብ ዋስትናና ሴፍትኔት ተጠቃሚዎችን የሚለዩ የልየታና ቅሬታ ኮሚቴ ምርጫ ተካሄደ===========።➻ በዝቅተኛ የኑ...
20/12/2025

በቀን 11/04/2018 በቦሌ ወረዳ 04 ስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት የከተማ ምግብ ዋስትናና ሴፍትኔት ተጠቃሚዎችን የሚለዩ የልየታና ቅሬታ ኮሚቴ ምርጫ ተካሄደ===========።
➻ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የወረዳው ነዋሪ ከሆኑት ውስጥ 1230 ተጠቃሚዎችን በ2017 በጀት አመት ተጠቃሚ የተደረገ ሲሆን በ2018 የልየታ ስራ የሚሰሩ እና ቅሬታ የሚቀበሉ ኮሚቴዎች በህዝብ እንዲመረጥ ተደርጓል። መድረኩን የመሩት በየቀጠናው አስተባባሪ አመራሮችና የፅ/ቤቱ ባለሙያዎች ሲሆኑ ግልጽ፣ነጻና ገለልተኛ ምርጫ መስፈርቱን በጠበቀ መልኩ እንዲካሄድ በማድረግ ተጠናቅቋል።

02/12/2025

✨ክፍት የሥራ ቦታ!

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንበሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS በኩል ከታች በተዘረዘሩት የሞያ ዘርፎች አመልካቾችን በቋሚ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

📌ሁለገብ የጥገና ሰራተኛ ➾ ብዛት ፦ 1
📌የአቤቱታና ቅሬታ ማስተናገጃ ባለሙያ ➾ ብዛት ፦ 2
📌የአገልግሎት አሰጣጥ ሱፐርቫይዘር ➾ ብዛት ፦ 4
📌ከፍተኛ የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ግምገማ ባለሙያ ➾ ብዛት ፦ 2
📌ኤሌክትሪሺያንና ሊፍት ኦፕሬተር ➾ ብዛት ፦ 1 📌ደረጃ 4 ነርስ ➾ ብዛት ፦ 1
📌የሰው ኃይል አስተዳደር ቡድን መሪ ➾ ብዛት ፦ 1
☝️ከላይ በተጠቀሱት የሞያ ዘርፎች ለመወዳደር በቅድሚያ lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ ባለ ወረዳ/ቀበሌ የአንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር/ labor ID/ ይዛችሁ

👉በhttps://forms.lmis.gov.et/mesob-civil-services/ ማስፈንጠሪያ በመግባት ትክክለኛ የትምህርት፣ የልምድ፣ የስራ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎቻችሁን በማሰገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

📆አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከህዳር 23/ 2018 ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ጥያቄ እና አስተያየት ካሎት በ9138 ይደውሉ። https://t.me/bequelmis1/550

አስቸኳይ ጊዜያዊ የስራ ማስታወቂያየምዝገባ ቦታ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅአ/አበባ
25/11/2025

አስቸኳይ ጊዜያዊ የስራ ማስታወቂያ
የምዝገባ ቦታ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ
አ/አበባ

22/11/2025
የስራ ባህል እና ምርታማነት በሚል ርዕስ ከስራ ፈላጊ ወጣቶች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡======በቦሌ ክ/ከተማ ወረደ 04 አስተዳደር በስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት የወጣቶችና ሴቶች የግንዛቤ ፈጠራ...
22/11/2025

የስራ ባህል እና ምርታማነት በሚል ርዕስ ከስራ ፈላጊ ወጣቶች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
======በቦሌ ክ/ከተማ ወረደ 04 አስተዳደር በስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት የወጣቶችና ሴቶች የግንዛቤ ፈጠራ ንቅናቄ መድረክ በሁሉም ብሎኮች እየተካሄደ ነው፡፡
በወረዳው የወጣቶችና ሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራታን ለማከናወን በርካታ ስራዎች እየተሰራ ሲሆን በዚህም የስራ ፈላጊውን የስራ ባህል ለማዳበርና ምርታማነትን ለመጨመር የግንዛቤ ፈጠራ ውይይት በየብሎኩ ተካሂዷል፡፡
** ቦሌ ወረዳ 04 ስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት
** ህዳር 13/03/2018

በቀን 25/2/2018 ከክ/ከተማ በመጡ የባለሙያ ቡድን ድጋፍና ክትትል ተደረገ።=== በድጋፍና ክትትሉ  የ1ኛ ሩብ ዓመት  አፈጻጸም የታየ ሲሆን ነሀሴ 12/12/2017 በተደረገው ክትትል የ...
04/11/2025

በቀን 25/2/2018 ከክ/ከተማ በመጡ የባለሙያ ቡድን ድጋፍና ክትትል ተደረገ።
=== በድጋፍና ክትትሉ የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም የታየ ሲሆን ነሀሴ 12/12/2017 በተደረገው ክትትል የታዩ ክፍተቶች የተስተካከሉበትን አግባብም ገምግሟል። በተጨማሪም የ2ኛ ሩብ ዓመት ጅምር ስራን በማየት በሰነድና በመስክ የማረጋገጥ ስራ ከተሰራ በኋላ የድጋፍ ቡድኑ መስተካከል ያለባቸውን ተግባሮች በማጠቃለያው አሳይቷል። በመጨረሻም ድክመት ተብለው በተነሱት ላይና አጠቃላይ ስለ ድጋፉ በሁሉም ቡድን መሪዎች አስተያየት ሰጥተው የወረዳው ም/ዋና ስራ አስፈጻሚና የጽ/ቤቱ ሀላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሱላሞ በሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብ ድጋፍና ክትትሉ ለቀጣይ ስራ መነቃቃት የፈጠረ እንደሆነ በመስማማት ተጠናቋል።

03/11/2025

✍️ የተቋሙ
ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴት

➻ የሥራና ክህሎት ቢሮ ተልዕኮ፤
ክህሎት መር የውጤት ተኮር የስልጠና ስርዓት በመዘርጋት ብቁ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ የሰው ኃይል በማፍራት፣ ለኢንተርፕራይዞች ድጋፍ በማድረግ ማልማት እንዲሁም ውጤታማ የሆነ የስራ ስምሪት አገልግሎት በመስጠትና የኢንዱስትሪውን ሰላም በማረጋገጥ፣በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ኑሮ በማሻሻል፣ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነትን ጤናማ በማድረግ፣የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ የሚያስችል ተቋም በመገንባት፣ ዘላቂ የስራ እድል እንዲፈጠር ማድረግ።
➻ የሥራና ክህሎት ቢሮ ራዕይ፤
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2022 ዓ.ም ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት ምቹ የስራ ሁኔታ የተረጋገጠበት ዘላቂ የስራ ዕድል ተፈጥሮ ማየት፡፡
➻ የሥራና ክህሎት ቢሮ እሴቶች
የስራ ባሕል ማዳበር፤
ሙያዊ ልህቀት፤
ጥራትና ተደራሽነት፤
አዳዲስ ፈጠራ ማመንጨት፤
ለለውጥ ዝግጁ መሆን፤
አካታችነት፤
አገልጋይነት፤
ታማኝነት፤

Address

Addis Ababa
Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole woreda 4 job and skill office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share