Merhabete woreda Livestock and Fisheries Resources Development Office

Merhabete woreda Livestock and Fisheries Resources Development Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Merhabete woreda Livestock and Fisheries Resources Development Office, Government Organization, North shewa, `Alem Ketema.

ወጣቶች በሌማት ቱሩፋት የልማት ስራዎች እንዲሳተፉ በማድረግ የበኩላችንን እንወጣ       እነሆ  ነዋሪነቱ በታች ቤት ንዑስ ወረዳ በፌጥራ ከተማ የሆነው ወጣት ብሩክ ዘርጋባቸው መንግስት ባመ...
31/12/2025

ወጣቶች በሌማት ቱሩፋት የልማት ስራዎች እንዲሳተፉ በማድረግ የበኩላችንን እንወጣ

እነሆ ነዋሪነቱ በታች ቤት ንዑስ ወረዳ በፌጥራ ከተማ የሆነው ወጣት ብሩክ ዘርጋባቸው መንግስት ባመቻቸለት በተዘዋዋሪ ብድር አቅርቦት አማካኝነት በአንድ ቀን ጫጩት እርባታ ስራ ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ ወጣት ነው፡፡
ስለሆነም ማንኛውም ወጣቶች በመንግስት አንዱ የኢኒሼቲቭ የስራ ዘርፍ በሆነው በዶሮ እርባታ ለመሰማራት የሚፈልግ ሁሉ ወጣት ብሩክ ዘርጋባቸውን በማነጋገር ተሞክሮ መቅሰምና እያሣደገ ያለውን የአንድ ቀን ጫጩት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የአንድ ጫጩት ዋጋ ብር 350 ሲሆን በጅምላ ለመግዛት ለሚፈልግ ደግሞ የአንድ ጫጩት ዋጋ 330 ብር መሆኑን ስንገልፅ በደስታ ነው፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ወጣት ብሩክ ዘርጋባቸው አሁን ስራውን የሚያከናውንበት የመስሪያና መሸጫ ቦታ /ሸድ/ መስተካከል እንዳለበትና ውሃና የመብራት ችግር ስላለበት ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ስጥተው ችግሬዐ እንዲፈታልኝ በማለት የወጣቱ ጥያቄው በቅንነት ተቀብሎ ለችግሩ መፍትሄ በመፈለግ ትብብር ቢደረግለት መልካም ነው እንላለን፡፡
አድራሻ ፌጥራ ከተማ ስልክ ቁጥር 0902337136 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

22/04/2018ዓ.ም በወረዳው በማር   ምርት  1487 እርሶ አደሮችና ወጣቶች  ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለፀ።በሰሜን ሸዋ ዞን በመርሐቤቴ ወረዳ  በሚገኙ ቀበሌዎች 1487 እርሶ አደሮችና  ወጣ...
31/12/2025

22/04/2018ዓ.ም

በወረዳው በማር ምርት 1487 እርሶ አደሮችና ወጣቶች ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለፀ።

በሰሜን ሸዋ ዞን በመርሐቤቴ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች 1487 እርሶ አደሮችና ወጣቶች በማር ምርት ተጠቃሚ መሆናቸውን የመርሐቤቴ ወረዳ እንስሳት ሃብት ጽህፈት ቤት የእንስሳት እርባታና መኖ ልማት ቡድን መሪ አቶ ሰብስብ ታደሰ ገለፁ።

እንደ ቡድን መሪው ገለጻ በወረዳው 23 የገጠርና በ3 የከተማ ቀሌዎች በንብ ማነብ ስራ ተሰማረተው የሚሰሩ ወጣቶችና አርሶ አደሮች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ በዚህም የማር ምርት በማግኘት ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ ከማር ምርት 65 ቶን ለማግኘት ታቅዶ እስከ አሁን 71.5 ቶን ማምረት መቻሉን አቶ ሰብስብ ተናግረዋል።

በአጠቃላይ በማር ምርት 1202 አርሶ አደሮች እና 285 ወጣቶች ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል።

የማር ምርቱ የተገኘው ከ3ቱም የቀፎ አይነቶች ማለትም ከባህላዊ፣ ከሽግግር እና ከዘመናዊ ቀፎ የተገኘ መሆኑንም አንስተዋል።
አክለውም ከአመልድ ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በመተባበር ለስራ አጥ ወጣቶች እና ለንብ አናቢዎች ሰፊ ስራ እየተሰራ ነውም ብለዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርትና ቴክኒካል ስልጠና ተሰጥቷል ሲሉ ገልጸዋል።

በቀጣይ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ ነው ያሉት ቡድን መሪው ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በመስራት ህብረተሠቡ በልማቱ ተጠቃሚ እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል ።

በንብ ማነብ ስራ በዋናነት ያጋጠሙ ችግር ይላሉ አቶ ሰብስብ የፀረ አረም መደሃኒት ኬሚካል ርጭት ለንቦች እንቅፋት ፈጥሯል ሲሉ አብራርተዋል ።
በመጨረሻም ስራው በትንሽ ቦታ ፣ ካፒታል እና ውስን የሰው ጉልበት የሚሰራ በመሆኑ የወረዳችን ወጣቶች በዘርፉ ቢሰማሩ ውጤታማ ስራ እንደሚሰሩም ቡድን መሪው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

02/04/2025
10/03/2025
05/03/2025
25/06/2017ዓ.ም      በወተት ላም እርባታ የተሰማሩ   ወጣቶች ውጤታማ  መሆናቸውን  ተናገሩ ።  በሰሜን  ሸዋ ዞን በዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ በወተት ላም እርባታ የ...
04/03/2025

25/06/2017ዓ.ም

በወተት ላም እርባታ የተሰማሩ ወጣቶች ውጤታማ መሆናቸውን ተናገሩ ።

በሰሜን ሸዋ ዞን በዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ በወተት ላም እርባታ የተሰማሩ ወጣቶች በዘርፉ ውጤታማ መሆናቸውን ተናገሩ ።
በወትት ላም እርባታ ከተሰማሩት ውስጥ አቶ ታዱ ተከተል አንዱ ሲሆን በ2013 ዓ.ም ከዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር ስራና ስልጠና ጽህፈት ቤት 220 ካሬ ሜትር ቦታ ተመቻችቶለት ወደስራ የገባ መሆኑን ጠቅሶ፤ መነሻ ከፒታል በ70 ሺህ ብር ስራውን የጀመሪ ሲሆን አሁን ላይ ከ400 ሺህ በላይ ካፒታል እንዳለው ገልጿል።
በተመሳሳይ በወተት ላም እርባታ የተሰማሩት አቶ ይልማ ጌታቸው ፣ አቶ ቴድሮስ ተሰማ እና አቶ ደረጀ ዳምጠው ሲሆኑ ከከተማ አስተዳደር ለእያንዳቸው 2ሺ ካሬ ሜትር ቦታ ተሰጥቷቸው ወደስራ መግባታቸውን ጠቁሞው ፤ አሁን ላይ የተሻለ ካፒታል ያስመዘገቡ መሆኑን ተናግረዋል።

በዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶች እንዳሉት ስራው ውጤታማ መሆኑን አንስተው ፤ የመኖ እና የገበያ ትስስር እጥረትም እንዳለ ገልጸዋል።

የመርሐቤቴ ወረዳ እንስሳት ሃብት ጽህፈት ቤት ባደረገው ክትባት ዝርያ ማዳቀል እና መሰል የሙያ ድጋፎችም እጅግ አመስግነዋል።
የመርሐቤቴ ወረዳ እንስሳት ሃብት ጽህፈት ቤት የዝርያ ማሻሻል ባለሙያ አቶ ተክለዮሐኒስ ፁዱ እንዳሉት በዘርፉ ለተሰማሩ ወጣቶች ጽህፈት ቤቱ የተሻለ ክትትልና ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው ፤ በቀጣይም ሙያዊ ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
በዘርፉ የተሰማሩ ሰዎች ጥሩ የተሻሻሉ ጦጆች ማግኘታቸውን ጠቁመው አንድ ከተሻሻለ ዝርያ ላም በአማካኝ በቀን ከ10_12 ሊትር ወተት እንደሚያገኙ ባለሙያው ገልጸዋል።

አክለውም በወረዳውም ይሁን በከተማው የተመጣጠነ የመኖ እና የወተት ማቀነባበሪያ አለመኖር ፣ የገበያ ትስስር እጥረት መኖሩንም ጠቅሰው በዘርፉ ውጤታማ ስራ ለመስራት ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት አለበት ብለዋል።

የመርሐቤቴ ወረዳ እንስሳት ሃብት ጽህፈት ቤት የዝርያ ማሻሻል ባለሙያ አቶ ጌታው መርግነህ በበኩላቸው በዘርፉ የተሻለ የዝርያ ማሻሻል ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተው በቀጣይም ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ተሰማርተው እየሰሩ መሆኑ ተገለፀዓለም ከተማ፤ መ/ወ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት (ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም)በሰሜን ሸዋ ዞን በዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር በከተማ ግብርና ተሰማር...
27/04/2024

በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ተሰማርተው እየሰሩ መሆኑ ተገለፀ

ዓለም ከተማ፤ መ/ወ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት (ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም)

በሰሜን ሸዋ ዞን በዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር በከተማ ግብርና ተሰማርተው በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ተሰማርተው እየሰሩ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ስራ ዕድል ፈጠራ የተመላሽ ሰራተኞች ክትትልና ድጋፍ ባለሙያ አቶ ምንሊክ ሙሉጌታ ተናገሩ።

እንደ ባለሙያው ገለፃ በከተማ አስተዳደሩ በሶስቱም ቀበሌዎች በከተማ ግብርና የዶሮ ዕርባታ፣ የእንቁላል ጣይ ዶሮ፣በከብት ድልብና በበግ ዕርባታ ተሰማርተው እየሰሩ እንደሆነ የገለፁት ባለሙያው በበጀት አመቱ 681 ለሚሆኑ ሰዎች የስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ገልፀዋል።

በበጀት ዓመቱ የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች 63፣ ሴት 117 እንደሆኑ የገለፁት ባለሙያው በመንግስት ስራ፣በከተማ ግብርና፣ በማንፋክቸሪንግ አገልግሎት ፣በቋሚነትና በጊዜያዊነት በአአጠቃላይ 681 ለሚሆኑ ሰዎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ በቋሚነት የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ወንድ 205፣ ሴት 304 በድምሩ 172 እንደሆኑና ቀሪዎቹ በግዜያዊነት የስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸውም አክለው ገልፀዋል።

በሶስቱም ቀበሌዎች የከተማ ግብርና ላይ ተሰማርተው በከብት ድልብ፣ በበግ ዕርባታና በዶሮ ዕርባታ እንቁላል ጣይ የዶሮ ዕርባታ ተሰማርተው እየሰሩ ከሚገኙት መካከል በ3 ቀበሌ ተገኝተን ያነጋገርንው የባህርዳር ዩንቨርሲቲ የቴክስታይል እንጂነሪንግ ምሩቅ ዲያቆን አብረሀም አሸናፊ ሳዶር የዶሮ ዕርባታ ህብረት ሽክና ማህበር የዕንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታው ውጤታማ እንዳደረገው ገልፆ በወቅታዊ ሀገራዊ ችግር ምክንያት የመኖ እጥረት እንደገጠመውና የሚጠበቀውን ያክል እንቁላል መጣል እንዳልቻሉ አንስቷል።

ዕንቁላል ጣይ ዶሮዎቹ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የገለፀው ወጣቱ ነፃ ክትባት በወረዳው ግብርና ጽ/ቤት እንዳገኙ ገልፆ ለተደረገለትም ድጋፍ የወረዳውን ግብርና ጽ/ቤት አመስግኗል።

በግሉ ጎግልን በመጠቀም ጤናቸውን ለመጠበቅና ጤንነታቸውን ለመለየት ጥረት እያደረገ እንደሆነ የገለፀው ወጣቱ እንኩቤተር የዕንቁላል ማስፈልፈያና መኖ ለማምረት የመብራት እጥረት በመኖሩ የመብራት ቆጣሪው ወደ ስሪ ፌዝ እንዲያድግ ጠይቋል።

የሼድ እጥረቱ እንደተቀረፈ ጠቁሞ የወቅታዊ ችግር ባያጋጥም አዋጭ መሆኑን አንስቶ የገበያ ትስስርን ለማጠናከርና ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማሰራጨት ቋሚ ቦታ አለመኖሩንም አንስቷል።

ለሶስት ሰዎች የስራ ዕድል እንደፈጠረ የገለፀው ዲያቆን አብረሀም አሸናፊ የሊዝ ፋይናንስ ትስስር ፣ ቆጣሪው ስሪ ፌዝ ቢሆንና በእንኩቤተር እንቁላል ማስፈልፈል፣ መኖ ማምረት እንደሚቻልም ገልጿል።

የገበያ ትስስር ለመፍጠር በንግድ ጽ/ቤት በኩል ድጋፍ እንዲደረግለት የጠየቀው ዲያቆን አብረሀም ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ለመሸጥና ለማሰራጨት እንደሚቻል አንስቶ በውሃ ጽ/ቤት በኩል የውሃ ችግር እንዳለና ችግሮቹ መቀረፍ ቢችሉ ውጤታማ ሊያደርገው እንደሚችል አንስቷል።

ሁሉም ሼዶች በስራ ላይ እንደሆኑ የገለፀው ወጣቱ የዶሮ ዕርባታውን ለማዘመን ወቅታዊ ችግር ባይኖር ከቴክኒክና ሙያ ጋር በመሆን መስራት እንደሚቻልም አያይዞ ገልጿል።
ዘገባው የመ/ወ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

ቀን 03/05/2015 ዓ/ምበወረዳው ለሚገኙ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎችየበግና ፍየል ደስታ መሰል /PPR/በሽታን ለማስወገድ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደበሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ...
10/02/2023

ቀን 03/05/2015 ዓ/ም
በወረዳው ለሚገኙ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች
የበግና ፍየል ደስታ መሰል /PPR/በሽታን ለማስወገድ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ

በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ እንስሳት ዓሳ ሐብት ልማት ጽ/ቤት የበግና ፍየል ደስታ መሰል /PPR/በሽታን ለማስወገድ በወረዳው ለሚገኙ ቀበሌዎች የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ የካቲት 03/2015 ዓ/ም አካሄደ።

በመድረኩ የሰሜን ሸዋ ዞን የእንስሳት ሐብት ኃላፊ አቶ ኃይለመስቀል ክፍሉ፣ የመርሐቤቴ ወረዳ እንስሳት ኃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ የዛላወርቅ ሐብታሙ፣ የPPR ሒደት አስተባባሪ አቶ ሰይድ መሐመድና በወረዳው የሚገኙ የቀበሌ እንስሳት ጤና ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።

የPPR ሒደት አስተባባሪ አቶ ሰይድ መሐመድ ስለPPR የበግና ፍየል በሽታ ሰፊ ማብራሪያና ግንዛቤ ለባሙያዎች ሰጥተዋል።

የመርሐቤቴ ወረዳ እንስሳት ኃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ የዛላወርቅ ሐብታሙ የPPR በሽታ ለውጭ የምናቀርበውን የእንስሳት ሐብት ምርት ሀገራችን ማግኘት ያለባትን ሐብት እንዳታገኝ አድርጓታል ብለዋል።

በበግና ፍየል ላይ እየተሰራጨ ያለውን የPPR በሽታ ለማስወገድ ክትባት የማድረግ ስራ ከባለሙያው የሚጠበቅ ስራ መሆኑን አንስተው ለዚህም ከአመራሩ ጋር በመናበብ ባለሙያው ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አያይዘው ገልፀዋል።

ከእንስሳት ጤና ባለሙያ ከተነሱ ሐሳብ አስተያዬቶች መካከል ፦
- የPPR በሽታ የተዳከመ እየመሰለ እየሰፋ በመሄዱ ክትባቱ እስከ መጨረሻ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ፤

-የበሽታው ችግር አስከፊ መሆኑን አንስተው ክትባቱ ከመሰጠቱ በፊት ከተበጠበጠ በኋላ ለ20 ደቂቃ ያክል መቆየት አለበት፤

-በየቀጠናው የእንስሳት ቁጥር በማጣራትና በመመዝገብ ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ ፤
- የመድሐኒት ብክነት እንዳይፈጠር አርሶ አደሩ እንስሳቱን በአካል ይዞ መገኘት አለበት፤

-የPPR በሽታን ምንነት ማወቅና ለአርሶ አደሩ ማስገንዘብና ወደስራ መግባት አለብን፤

-የመርሐቤቴ ወረዳ እንስሳት ጤና ባለሙያ እንደወረዳ መብቱ እየተከበረ አይደለም፤
-አንቲኦቲክ የወሰዱት እንስሳት በድጋሚ ክትባት መውሰድ ይችላሉ? አይችሉም?

የመርሐቤቴ ወረዳ የእንስሳት ጤና ቡድን መሪ አቶ ምሳው ቅጣው ባለሙያው የመድሐኒት አጠቃቀሙን በትኩረት ተገንዝቦ መስራት እንደሚገባ አሳስበው አንቲኦቲክ የወሰዱ እነሰስሳት የPPR በሽታ መድሐኒት መውሰድ እንዳለባቸውና ባለሙያው ለስራው ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባም አንስተዋል።

በመጨረሻም የመርሐቤቴ ወረዳ እንስሳት ሐብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ የዛላወርቅ ሐብታሙ ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን የእንስሳት ሐብት ኃላፊ አቶ ኃይለመስቀል ክፍሉ፣ የPPR ሒደት ስተባባሪ አቶ ሰይድ መሐመድ ከባለሙያው ለተነሱ ሀሳብና አስተያዬት ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተው ባለሙያና አመራሩ በመናበብ እስከ 20 ቀናት በሁሉም ቀበሌዎች በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባና አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈው፤ መድረኩ መጠናቁን የመርሐቤቴ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ከስፍራው ዘግቧል።

ፍየል፣ በግና የቀንድ ከብትን ጨምሮ ከ198 ሺህ በላይ  በወረዳው እንዳሉ ጽህፈት ቤቱ አስታወቀ። በሰሜን ሸዋ ዞን በመርሐቤቴ ወረዳ ፍየል፣ በግና የቀንድ ከብትን ጨምሮ ከ198 ሺህ  በላይ ...
12/01/2023

ፍየል፣ በግና የቀንድ ከብትን ጨምሮ ከ198 ሺህ በላይ በወረዳው እንዳሉ ጽህፈት ቤቱ አስታወቀ።

በሰሜን ሸዋ ዞን በመርሐቤቴ ወረዳ ፍየል፣ በግና የቀንድ ከብትን ጨምሮ ከ198 ሺህ በላይ በወረዳው እንዳሉ የወረዳው እንስሳት ሀብት ተጠሪ ጽህፈት ቤት የእንስሳት እርባታ ቡድን መሪ አቶ ሰብስብ ታደሰ ገለጹ።
እንደ ቡድን መሪው ገለጻ በወረዳው በግ 18ሺህ 850 ፣ፍየል70 ሺህ 163 እና የቀንድ ከብት 109 ሺህ 258 እንዳሉ ጠቅሰዋል።
ህብረተሠቡ የእንስሳት ጤንነትን ለመጠበቅ በሽታ ከመከሰቱም በፊት ሆነ ምልክቶቹን ሲያዩ በአቅራቢያው በሚገኝ የእንስሳት ጤና ክሊኒክ በመውሰድ ማስከተብ እንዳለበት አሳስበዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር አቶ ሀይለመስቀል  ክፍሉን  የሰሜን ሸዋ ዞን እንሰሳት ሀብት ተጠሪ ጽ/ቤት ሀላፊ አድርጎ ሾመ።መልካም የስራ ዘመን
31/12/2022

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር አቶ ሀይለመስቀል ክፍሉን የሰሜን ሸዋ ዞን እንሰሳት ሀብት ተጠሪ ጽ/ቤት ሀላፊ አድርጎ ሾመ።

መልካም የስራ ዘመን

የብዙዎችን ኑሮ የለወጠው የሥራ መሥክ!ደብረብርሃን:ታኅሣሥ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን ትርፍ አምራች ከኾኑት አካባቢዎች  ሞረትና ጅሩ ወረዳ አንዱ ነው። ወረዳው ከሰብል ልማ...
21/12/2022

የብዙዎችን ኑሮ የለወጠው የሥራ መሥክ!

ደብረብርሃን:ታኅሣሥ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን ትርፍ አምራች ከኾኑት አካባቢዎች ሞረትና ጅሩ ወረዳ አንዱ ነው። ወረዳው ከሰብል ልማት ባለፈ በከብት ማድለብም በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ ነው። በዚህም የጅሩ ሰንጋ በ2006 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ልዩ እውቅና ተሠጥቶታል።

የአካባቢው ሰንጋ እውቅና ካገኘ ጀምሮ የገበያ ትስስሩ በመሻሻሉ በከብት ማድለብ ሥራ ተጠቃሚ መኾናቸውን በማድለብ ሥራ የተሰማሩ አድላቢዎች ነግረውናል።

በማድለብ ስራ ላይ የተሰማሩት አያል አበበ በመጀመሪያ ዙር የማድለብ ሥራ ባገኙት ገቢ አኹን ላሉበት ሥራቸው መሠረት እንደኾናቸው ነግረውናል።

በቀጣይ መንግሥት የመኖና የብድር አቅርቦት ቢያመቻችላቸው ከዚህ በተሻለ መንገድ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ወጣት ፍቅሩ ሙሉጌታ ደግሞ ከግብርናው ጎን ለጎን የከብት ማድለብ ሥራ በማከናወን ነው ወላጆቹን የሚያስተዳድረው። የጅሩ ሰንጋ ብራንድ ማግኘቱን ተከትሎ በተፈጠረው ገበያ ከሚያደልባቸው ሰንጋዎች የተሻለ ገቢ ማገኘቱን ነግሮናል።
በዚህም ዘመናዊ ቤት ገምብቷል፤ ዳቦ በመጋገር ለገበያ ያቀርባል። የእንስሳት የመኖ ችግሮች ሊፈቱ እንደሚገባም ጠይቋል።

የሞረትና ጅሩ ወረዳ እንስሳትና አሣ ሃብት ልማት ተጠሪ ጽሕፈት ቤት የእንስሳት እርባታና መኖ ልማት ቡድን መሪ መዝገቡ ጌታቸው እንዳሉት የጅሩ ሰንጋን የገበያ ችግር ለመቅረፍና የሰንጋው ሥጋ ካለው ጣዕም አኳያ እውቅና እንዲሰጠው ተደርጓል። እውቅና ማግኘቱን ተከትሎ በተፈጠረው የገበያ ትስስር በአንድና ሁለት በሬዎች የማድለብ ሥራ ተሰማርቶ የነበረው አርሶ አደር አኹን ላይ በተናጠልና በማኅበር በመደራጀት እስከ 10 በሬዎችን የማድለብ ሥራ ላይ ተሠማርቷል።

በዚህ ዓመት በዩኒቨርሲቲዎችና በኮሌጆች የተመረቁ፣ በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወጣቶችንና አካል ጉዳተኞችን በማድለብ ሥራ ለማሳተፍ የልየታ ሥራ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

የተመጣጠነ መኖን ከአምራች ከፋብሪካዎች በመረከብ በወረዳው በሚገኙ ሰባት አድላቢ ቀበሌዎች እየተከፋፈለ እንደኾነ አንስተዋል። ይሁን እንጅ ከኢንዱስትሪ ተረፈ ምርት ውድነት ጋር ያለውን ችግር መፍታት አለመቻሉን ነው ያነሱት።

አኹን ላይ በወረዳው፦
👉ከ86 ሽህ 200 በላይ የዳልጋ ከብቶች ይገኛሉ።
👉 ከ12 ሺህ 800 በላይ አድላቢ አርሶ አደሮች ይገኛሉ።
👉እስከ አሁንም 36 ሺህ 826 በግ፣ ፍየልና የዳልጋ ከብቶች በመድለብ ላይ ይገኛሉ።
👉ከ12 ሺህ 600 በላይ የቀንድ ከብቶች ለገናና ፋሲካ እየደለቡ ይገኛል።

የሰሜን ሸዋ ዞን እንስሳትና አሣ ሃብት ልማት ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ተወካይ ኃላፊ ዘንባባ ተሊላ እንዳሉት ተቋሙ በሠራው ሥራ የጅሩ ሰንጋ ለማድለብ እስከ ስድስት ወር ይወስድ የነበረውን ጊዜ በዓመት ሥስት ጊዜ በማድለብ ለገበያ እንዲያቀርቡ ተደርጓል።

ተምክሮውም ወደ ሲያደብር፣ እንሳሮ፣ ባሶና ወራናና አንጎለላና ጠራ ወረዳዎች የማስፋት ሥራ መሠራቱን ገልጸዋል።
የተከሰተውን የመኖ ውድነት ለመቀነስ በዞኑ የሚገኘው ዩኒየን የተመጣጠነ መኖ ለአርሶ አደሮች እንዲያቀርብ እየተሠራ ይገኛል። ዩኒየኑ ወደ ሥራ ሲገባም ጥራት ያለውና የተመጣጠነ መኖ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://

ወጣት ጌቱ ላቀ ይባላል ነዋሪነቱ  በዓለም  ከተማ  ከተማ  አስተዳደር ቀበሌ 01 ሲሆን ራሱን በኢኮኖሚ ለመገንባትና ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ለመላቀቅ ባለው ፅኑ ፍላጎት በአንድ ወር የዶሮ ጫጩት ...
21/12/2022

ወጣት ጌቱ ላቀ ይባላል ነዋሪነቱ በዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 01 ሲሆን ራሱን በኢኮኖሚ ለመገንባትና ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ለመላቀቅ ባለው ፅኑ ፍላጎት በአንድ ወር የዶሮ ጫጩት እርባት ስራ ተሰማርቶ ለህብረተሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
ወጣት ጌቱ ላቀ ለአመታት ያህል በደቡቡ የአገራችን ክፍል በተለያ ቦታዎች በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርቶ ሲሰራ ቢቆይም በወቅታዊው በአገራችን በተፈጠረው ብሔርን ያነጣረ ግድያና ማፈናቀል ሴራ ወደ ትውልድ አካባቢው በመምጣት ከላይ በተጠቀሰው የአንድ ወር የዶሮ ጫጩት ርባታ ስራ በመሰማራት ለአካባቢው ማህበረሰብ በማሰራጨት ላይ ነው፡፡
ወጣቱ ይህን ስራ ሲሰራ ከግለሰብ በአንድ መቶ ብር አስር ብር ሂሳብ ወለድ ለመክፈል በተበደረው ሰማኒያ ሽህ / 80.000 / ብር ተከራይቶ በሚኖርበት የግለሰብ መኖሪያ ቤት ሲሆን ለሌሎች ስራ አጥ የህብረተሰብ ክፍሎች መልካም አርአያ በመሆንና ለአካባቢው ህዝብ የዶሮ እርባታ ፍላጎትን ለማሟላት በቅርበት በማቅረብ በኩል እሰው የሚያስብል ተግባር በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ ወጣት ጌቱ የጀመረውን ስራ በብቃትና በስኬት ለመከወን የመስሪያና መሸጫ ቦታ ችግር እንዳለበት ይናገራል፡፡
የመርሐቤቴ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የአቅም ግንባታ፣ ህዝብና ሚዲያ ግንኙነት ቡድን ባለሙያዎች የወጣቱን ችግር በመያዝ ወደ ዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የቴክኒክና ሙያ እንተርፕራይዝ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አጥላባቸው ፈለቀ በመቅረብ ያነጋገሩ ሲሆን እሳቸውም የወጣቱን ጥረትና ተነሳሽነት በሚገባ በመረዳት ችግሩን በፍጥነት ለመፍታት እየሰሩ መሆናቸውን አረጋግጠውልናል፡፡
የመርሐቤቴ ወረዳ እንስሳት ሀብት ተጠሪ ጽህፈት ቤትም ለወጣቱ የሙያ ምክርና ድጋፍ እያደረገለት እንደሚገኝ የጽህፈት ቤቱ የአንስሳት ሀብት ርባታ ባለሙያ ወ/ሮ ይመኙሻል ምታው አስረድተውናል፡፡

Address

North Shewa
`Alem Ketema

Telephone

+251111321041

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Merhabete woreda Livestock and Fisheries Resources Development Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share