08/02/2026
" ሳይጀምር የተሸነፈው የሞንጆሪኖ-ህግደፍ ሚስጥራዊ እና ወታደራዊ የጦርነት እቅድ ‼️
------------------------------
ህግደፍ እና የሞንጆሪኖ ቡድን "የፌደራል መንግስት ሳያጠቃን ልናጠቃው ይገባል" በሚል ውሳኔ በቅርብ ቀናት በሁሉም አቅጣጫ ጦርነት ለመክፈት የወሰኑ ሲሆን፤ የጦርነቱን አሰላለፍ በሚመለከት ሚስጥራዊ ሰነድ እንደሚከተለው ይፋ እናደርጋለን፦
🔵 አርሚ 24 ቀደም ሲል በሟቹ ጉዑሽ ገብረ እግዛብሄር ሲመራ የነበረ ሲሆን በዚህ ሳዓት ደግሞ በኮሎኔል ካህሳይ መኮነን (ንእሽተይ ሸሪፎ) ስር የወደቀችው አርሚ 24 በጮቢ በር አቅጣጫ እንዲያጠቃ ተመድቧል።
🔵 በዘነበ ክፍለ የሚመራው አርሚ 31 ከአርሚ 24 ጋር በተደራቢ እንዲያጠቃ፣ እና ከአርሚ 24 ጋር እየተቀናጀ እስከ ወልዲያ የመቆጣጠር ግዳጅ ተሰጥቷታል።በዚህ መሰረት የተወሰኑ የአርሚ 31 ክፍለ ጦሮች በውቅሮ ከተማ ወታደራዊ ኦሬንቴሽን ተሰጥቷቸው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
🔵 በትንሳኤ ብርሃነ (ወዲ ብርሃነ) የምትመራው አርሚ 43 የራያ ጨርጨርንና ከያሎ ወረዳ ጋር የሚዋሰነውን የቢሶበር ግንባር እንዲሰማራ ተመድቧል።
🔵 በተጋዳላይ ገ/ዩሃንስ አባተ (ወዲ አባተ) ሲመራ የነበረው አርሚ 44 ፣እና አርሚ 22 በአሁኑ ሰዓት የራያ ህዝብ ጨፍጫፊ በሆነው ገ/ፃዲቅ አስረሳሃይ ስር የወደቀችው አርሚ 44 በወጀራት አቅጣጫ ጥቃት እንዲሰነዝር፣ በከዳተኛውና በሞንጆሪኖ አሽከር ገ/ስላሴ ቁጥሚ የምትመራው አርሚ 22 ደግሞ ከአርሚ 44 ጋር ተደራቢ ጥቃት እንዲከፍት ተመድቧል።
🔵 የታጠቀ የፋኖ ቡድን
የታጠቀ ፋኖ ከአርሚ 24 እና 31 ጋር በመቀናጀት በመርዋ አቅጣጫ ጥቃት እንዲሰነዝር ተመድቧል።
🔵 በከበሮ መቺው ሓጎስ ገብረ የሚመራው አርሚ 26 እና የራያ ህዝብ ጨፍጫፊ በሆነው ወልደ ጅወርግስ ተኽላይ (ሸሪፎ) የሚመራው አርሚ 33 የተወሰኑ ክፍሎች በጋራ የዶግዓ ራያ አካባቢዎችን እንዲያጠቃትዕዛዙን ተቀብሏል።
🔵 በዋነኛው እና በታማኝ የሞንጀርኖ አገልጋይ አብርሃ ተስፋይ (ዱንኩል) የሚመራው አርሚ 42 እና በጀግናው ጀነራል ጉዑሽ ገብረ ስትመራ የነበረችው እና በዚሁ ሳዓት ደግሞ መዓሾ በሚባል በሞንጆሪኖ ካድሬ የምትመራው አርሚ 15 በህግደፍ እየተመሩ እና እየተገረፉ በኤርትራ አቅጣጫ ወደ ምዕራብ ዞን ለመግባት በሚል ሽፋን ወደ ኤርትራ እንዲገቡ ታዘዋል።
🔵 ራስ ወዳዱና ተንኮለኛው ሻዕቢያ፣ ትግራይን የመካከለኛ ግንባር በማድረግ የጦርነቱን ሂደት እያየና እየገመገመ ወደ ትግራይ ለመግባት ዝግጅቱን አጠናቋል።
የሰላም አማራጭ የሚይፈልገው የህወሃት ቡድን የትግራይን ህዝብ ወደ ዳግም ጦርነት ለማስገባት የጀመረውን ትንኮሳ የትግራይ ህዝብ እና ወጣቶች ልያስቆሙት ይገባል።በኢትዮጵያ ለሚፈጠር ዳግም ጦርነት ተጠያቂው ህወሃት ብቻ መሆኑን ተገንዝቦ የትግራይ ህዝብ ህወሃትን ቀድሞ በቃህ ልለው ይገባል።የኢትዮጵያ መንግስትም በህወሃት በኩል ለሚፈጠሩ ትንኮሳዎች የቅድመ መከላከል ስራ ሊሰራ ይገባል እንላለን። "