11/04/2026
የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት እየሰሩ ይገኛል -አቶ አብዲ አወል
ሚያዝያ 03/2018 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ
በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ሴቶችና የፍትህ አካላት የጋራ ፎረም የ2018 ዓ.ም የ9ወር ዕቅድ አፈፃፀምን በዛሬው ዕለት ገምግሟል።
መድረኩን የመሩት የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ፍትህ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዲ አወል እንዳሉት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን በማንሳት ይህ ስራ በቀሪ ጊዜያት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የፎረሙ አባል ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ9 ወር አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱም የሴቶችና ህጻናት ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ማስከበርና የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ከማስቀረት ባሻገር፣ የሴት ተማሪዎች መጸዳጃ እና የሴቶች ንጽሕና መጠበቅያ ቁሳቁሶች ተደራሽነት አንጻር የተሠሩ ስራዎች አበረታች እንደሆኑ ተገምግሟል።
ከጤና ጋር ተያይዞ የእናቶች ፎረም ከማስኬድ ጋር ተያይዞ፣ ከቅድመ ወሊድ ክትትል አንፃር በአልትራሳውንድ የተደገፈ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ እና ከማህጸን ጫፍ ካንሰር ምርመራ ጋር የተጀመሩ ስራዎችና በከተማው የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ አምራች ግለሰቦችን ማበረታታቱ በጥንካሬ ተገምግሟል።
ፍትህ ተቋማትን በተመለከተም በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ከማስቀረት እና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ከማስከበር አንጻር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተቀምጧል።
በመጨረሻም የዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት በቀሪ ጊዜያት ሁሉም ባለድርሻ ሴክተሮች እና ከሴቶች አደረጃጀቶች ጋር ተያይዞም ግንዛቤ መፍጠር ፣ ፈጣንና ተደራሽነት ያለው አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በሰፊው ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።
በመርሃ ግብሩ የሴቶችን ንፅህና ለመጠበቅ በኬራቴ ከተማና ኬራቴ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን የፎረሙ አባላት ምልከታ አድርገዋል።
መረጃው የሁልባራግ ወ/መ/ኮሙኒኬሽን ነው!